የዓባይ፡ልጅ▪️እስሌማን፡ዓባይ
ህወሃት ጦርነቱን (ነሐሴ 17 ንጋት) ላይ ከመክፈቱ በፊት ጀምሮ ነበር tigray under attack በሚለው ሀሽታግ በመቶ ሺዎች የሀሰት መረጃ ትዊተር ማሰራጨት የጀመረው። በሳምንቱ ሰባት ቀናት ብቻም ከ 475 ሺህ በላይ ትዊቶች ሲያሰራጭ ከዚህ ውስጥ ከኢትዮጵያ በሚገኙ አካውንቶች የተሰራጨውም ሀሰተኛ መረጃም በመቶ ሺዎች ሆኗል።
አዲስ አበባ ትግራይ እና አማራ ክልሎች የህወሃቱ ሀሽታግ ከተሰራጨባቸው አካባቢዎች ሆነዋል።
በሳምንቱ ውስጥ በተጠቀሰው ሀሽታግ ከ129 ሺህ በላይ ትዊቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የትዊተር Users የተሰራጩ ሲሆን ሶስቱ ቦታዎች የነበራቸው ድርሻ የሚከተለው ነው።
▪️አዲስ አበባ 112 ሺ የትዊተር መልእክቶች በሳምንቱ
▪️ትግራይ ክልል ውስጥ 15,800 ሺህ ትዊቶች በሳምንት
▪️አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች (ከመቶ በታች ትዊቶች ቢሆኑም)
⏯ በሳምንቱ #TPLFisTheCause የሚለው ሀሽታግ በህወሃቱ Tigray Under Attack ሐሽታግ ከ 30,000 በላይ ትዊቶች ብልጫ ተወስዶበት ይታያል።
ይህም በመዲናዋ በሚኖሩ አፍቃረ ህወሃቶች ባሰራጩት የ 88 በመቶ የትዊተር ስውር ዘመቻ የተተገበረ መሆኑ ነው።
1 thought on “የህወሃት ስውር የዲጂታል ልዑካን በአዲስ አበባ”
ከህያዊያን የኢትዮጵያ ፈርጥ አርበኞች አንዱ በመሆንህ ክብር ይገባሃል🙏❤🙏