የሐብታሟ አፍሪካ ልጆች ደሀ ናቸውሳ!

ይህን ካነበቡ በኌላ ‘አፍሪካ ደሃ ናት’ የሚል አመለካከትዎን በርግጠኝነት ይለውጣሉ!

በያመቱ 161 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ወደ አፍሪካ ይገባል። ይህ በርዳታና በውጭ ሚኖሩ እፍሪካውያን በሬሚታንስ የሚልኩት ነው።

በተቃራኒው 203 ቢሊዮን ዶላር በያመቱ አህጉሪቷን ትተው ይወጣሉ። በህገ ወጥ መንገድ እንዲሸሽ የሚደረግው መሆኑ ነው። ገንዘቡ በተለያየ መንገድ ይሸሻል። ለምሳሌ አለማቀፍ ኩባንያዎች ህጋዊ መስለው ነገር ግን ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር የሚያሸሹት ብቻ በያመቱ 68 ቢሊዮን ዶላር ነው። ይህ አሃዝ ብቻ የአህጉሪቷን አጠቃላይ አመታዊ ምርት 6 በመቶ በላይ ይሸፍናል።

የውጭ ኩባንያዎች በአፍሪካ ያተረፉትን 30 ቢሊዮን ዶላር (በአመት) ወደ አገራቸው በመውሰድ ያስቀምጣሉ።

በህገ ወጥ አሳ ማስገርና እንስሳ ንግድ ደግሞ በያመቱ 29 ቢሊዮን ዶላር ከአፍሪካ ይዘረፋል። አፍሪካ ያደጉት አገራት በካይ ጋዝ በማህበረሰቡና ኢኮኖሚዋ ላይ ለሚያደርሰ ጉዳት ካሳ 36 ቢሊዮን ዶላር በያመቱ እንዲደርሳት ከአመታት በፊት ቢወሰንም እስካሁን የሰጣት የለም። ገንዘቡን መቀበል ይቻል ዘንድ በተጨባጭ የሰራ የለምም።

አፍሪካውያን አገራት በብድር የሚቀበሉት ዶላር ለአህጉሪቱ እንደሚጠቅም ቢታሰብም መሪዎች በተገቢው ሰርተውና አስተዳድረው በወቅቱ ስለማይመልሱት በያመቱ 50 ቢሊዮን ዶላር ያልተከፈለና ድርብርብ ወለድ ይለወጣል። በዚህ ጦስ ጋና በያመቱ ከምትሰበስበው ገቢ ውስጥ 30 በመቶውን የዞረ እዳና የዕዳዋን ወለድ ክምችት በመመለስ እንድታውለው ተገዳለች። በሞዛምቢክ ደግሞ በተከማቸው ያልተመለሰ የብድር ወለድ ሳቢያ በእያንዳንዷ የ 1 ፓውንድ ብድር 23 ፓውንድ እጥፍ እየውከፈለችና አሁንም እየተጨመረባትም ነው የምትገኘው።

165,000 አፍሪካውያን ቱጃሮች በድምሩ 860 ቢሊዮን ዶላር አላቸው። ይህን ገንዘብ የት እንደሚያሰቀምጡ በቅጡ አለመታወቁና ሰርተውበትም የተቀረውን አፍሪካዊ መጥቀም አልቻሉም ይላል አልጄዚራ africa investigates በተሰኘ የምርመራ ዘገባው። በ 2014 በተደረገ ጥናት መሰረትም እነዚሁ ሃብታም አፍሪካውያን 500 ቢሊዮን ዶላር ታክስ አጭበርብረዋል አሽሽተዋል። ምእራባውያን ተመልሶ የሚሸሽ የይስሙላ ርዳታና ብድር ከመስጠት ይልቅ ሃብት ማሸሽን መቆጣጠር ላይ ከልብ ቢሰሩና እዠአፍሪካም ሃብቷን እንድትጠቀምበት በሲስተም ዝርጋታ ላይ ቢያግዟት የተሻለ ይሆናል የሚባለውም ለዚህ ነው። በኢንቨስትመንት ሰበብ ዜጎችና ደሃ አገራት ካደጉት ጋር የማይችሉትን ፉክክር እንዲጋተሩት ከማስገደድ ኢንቨስትመንቱን በራሳቸው መንገድ እንዲመሩት ቢፈቅዱላቸው።

Al-Jazeera, africa investigates ምርመራው ላይ ያነጋገራቸው በብሪታኒያ Global Justice Now የተባለ ተቌም ዳይሬክተር ኒክ ዲርደን “ስለ ድህነትና ድህነት ወለድ ስለሆኑ ዘገባዎች ነበር ስለ አህጉሪቱ የምንሰማው። አፍሪካ ደሀ ናት ብለን እናስብም ይሆናል። ነገር ግን ይህን አስተሳሰብ መለወጥ የግድ መሆኑ ነው እውነታው። አፍሪካ ደሃ አይደለችም፤ እኛ አደኸየናት እንጂ፤ ዘረፍናት እንጂ” ነበር ያሉት።

ምክንያቱም ቆንጆዎቹ ልጆቿ በበቂ መጠን ገና አልተወለዱም

የዓባይ ልጅ | እስሌማን ዓባይ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories