የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የግጭቶችን ባህሪ የለየ ዘላቂ መፍትሔ ያስፈልጋል”

በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ፣
  አቶ ወንድወሰን ንጉሴ

አቶ ወንድወሰን ንጉሴ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአገርን ሰላምና አንድነት ለማረጋገጥ የግጭቶችን ባህሪ መለይ ብሎም እንደየባህሪያቸው ዘላቂ መፍትሄን ማበጀት ይጠይቃል።

ግጭት በተለያየ አጋጣሚ ይከሰታል ያሉት አቶ ወንድወሰን፤ ትልቁ ችግር የግጭት አፈታት ሂደቱ ነው:: የግጭት አፈታት ሂደቱንም በኃይል ሳይሆን በመግባባት ላይ የተመሰረተ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚሞከረው ደም አፋሳሽ በሆነ ጦርነት በመሆኑ ከባድ የሆነ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ ውድመት ያስከትላል ሲሉ ተናግረዋል።

መንግሥት የግጭቶችን ምንነት በመለየት እንደየ ችግሮቹ ባህሪያት ለይቶ የጸጥታ ኃይሉንና በየደረጃው ያሉ አካላትን በማስተባበር እልባት መስጠት እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል።

ሕዝቡን በማሳተፍ በአጥፊዎች ላይ ጠንካራ ርምጃ ስለማይወሰድ ሌሎች ግጭት ቀስቃሾች የሚበረታቱበት ሁኔታ እየታየ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ወንድወሰን፤ ግጭቶች ከተከሰቱ በኋላም በአጥፊዎች ላይ ግልጽና ተጨባጭ እርምጃ ያስፈልጋል።


ሙሉውን ለማንበብ በሊንኩ ⬇️
https://www.press.et/?p=72367

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories