የምዕራባዊያን ውሸት በኤርትራዊ ሥኬት ሲጋለጥ

   ~ የአሥመራ Development Book ~

አብዲዋሐብ ሼክ አብዲሰመድ✍️ #የዓባይልጅ

ቀይ ባህር ላይ ስትራቴጂክ ቦታ ላይ በምትገኘው ኤርትራ በቅርቡ ያደረገው ጉብኝት በአስደሳች ውበት እና ሰላም የተሞላ ነበር ሲል የሆርን አፍሪካ ስትራቴጂክ ጥናት ተቋም ሊቀመንበር ፅሁፋቸውን ይጀምራሉ። የተቋሙ ሊቀመንበር አብዲወሃብ ሼክ አብዲሰመድ ኤርትራ አለም አቀፍ ማእቀብ ሳይበግራት በራሷ አቅም ያሳካችው የምግብ ዋስትና ውጤት ለመላው አፍሪካዊ ሀገራት ትምህርት ሰጪ ሆኖ አገኘሁት”” ብለዋል።

“ምእራባዊያን ስለ ኤርትራ የሚነዙትን ትርክት ትልቅ ውሸት መሆኑን እንድታዘብ አድርጎኛል።” በማለት አድናቆታቸው ገልፀው ከኤርትራ ተሞክሮው ሌሎችም ይማሩ ዘንድ አብዲወሃብ ሼክ አብዲሰመድ የከተቡትን አጋራኋችሁ ✍️

ሰባት ሚሊዮን ገደማ ሕዝብ ያላት ኤርትራ የተረጋጋ ፖለቲካ የሰፈነባት ከሞላ ጎደልም ከወንጀልና ሙስና የጸዳች ነች። ዜጎቿ እስከ ዩኒቨርሲቲ የሚደርስ ትምህር እና የጤና ክብካቤ በነፃ ያገኛሉ። በሀገራቸው የሚኮሩ ኤርትራውያን፣ ሌሎች አፍሪካዊ ሀገራትን ያጠፋውን የውጭ ተጽዕኖ በተሳካ ሁኔታ ተቋቁመውት ይገኛሉ።
ምእራባዊያን ካቀረቡላት ቀንበር ይልቅ ሉአላዊነቷን በማስቀደሟ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ድጋፍ በነፈጓት ወቅት ካጋጠሟት ጣጣዎች መትረፍ ችላለች። ይህ ኤርትራዊ የስኬት ታሪክ ለአፍሪካ ሀገራት ተስፋ ነው። የኤርትራውያን የፅናት መንፈስ የተቀሩት አፍሪካውያን የልማት አቅጣጫ እናስምርላችሁ የሚሏቸውን አለም አቀፍ ኃይሎች እንዴት መቋቋም እንደሚችሉ የሚያስገነዝብ መማሪያ መጽሐፍ ነው።

ከዓመታት በምዕራባውያንና በአሜሪካ የሚደገፈው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አስተዳደር በኤርትራ አውዳሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት አደረገ። ሊሰብሯቸው በቆረጡ አለም አቀፍ ድርጅቶች ድርጊት እና የተባበሩት መንግስታት ለአመታት ሲነዛው በነበረው ውሸት የተነሳ ኤርትራዊያን ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። በኤርትራ የሥርዓት ለውጥ እንዲመጣ ወይም ደግሞ ቢያንስ አመጽ እንዲቀሰቀስ ብሎም አስመራ ከኢኮኖሚው ተጠቃሚነት ተነጥላ አጠቃላይ ቀውስ ለመፍጠር አበክረው ቢሰሩም ያ ሁላ የተቀናጀ ሴራ አሁን ላይ ከሽፏል። ይህ የምዕራቡ ዓለም ሴራ መጀመሪያ ላይ ሚሊዮኖች ኤርትራዊያን ዘንድ የፈጠረው ፈታኝ ሁኔታ የታቀደውን ቁጣ ከመቀስቀስ ይልቅ በተቃራኒው በረከት ያለው ስራ ይጀመር ዘንድ ሰበብ ሆነ። የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አስተዳደር ኤርትራን ራሷን የምትመግብ ለማድረግ መርሃ ግብራቸውም አስጀመሩ። ይህ ጥረት የታለመለትን ሀገራዊ ግብ ለመምታት ከጫፍ ደርሷል። በቀጣይ ጥቂት አመታት ውስጥም ኤርትራ ህዝቦቿን በመመገብ ሰብአዊ ርዳታ ላይ የማትጠብቅበት ስኬታን ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅታለች።

በጉብኝቴ ያገኘኋቸው የኤርትራ ግብርና ሚኒስትር አረፋይነ በርሄ ሀገራቸው ዜጎቿን በራሷ ለመመገብ የሚያስችል የግብርና መሰረተ ልማት መገንባቷን ይናገራሉ። የግብርና ሚኒስቴሩ ካሳዩኝ ሰነድ እንደተመለከትኩትም 220 ሚሊየን ዶላር የተበጀተለት የአምስት አመት እቅድ ነድፋለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ 18.4 ሚሊዮን ሰዎች ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ተጋልጠዋል። ይህ አሃዝ እስከ ወርሃ መስከረም 20 ሚሊየን ሊደርስ ይችላልም ብሏል።
የተባበሩት መንግስታት እና የምዕራባውያን ማዕቀቦች ከአስር ዓመታት በላይ ቢጣሉባትም ችግሩን ተቋቁማ አሁን ላይ 500,000 ሄክታር መሬት በጥሩ ሁኔታ በጥቅም ማዋል ችላለች።
ይህ ስኬቷ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲሁም አለም አቀፍ የሰብአዊ ርዳታ ድርጅቶች ምግብ ዋስትናን በተመለከተ ቀላል፣ ወጪ ቆጣቢ እና ግልፅ የሆነ አሰራርን ከኤርትራ መዋስ ይችላሉ።

በግብርና ሚኒስቴር የእቅድና ስታስቲክስ ዲቪዥን ዳይሬክተር አቶ በረከት ፀሃዬ በቅርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ በኤርትራ የፍራፍሬ ምርት በ 71 እጥፍ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ደግሞ በ 6 እጥፍ ገደማ ጨምሯል። ባሳለፍነው የፈረንጆች 2021 ላይም ኤርትራ ከምግብና ደረጃ ተላቃ ‘ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ እና አልሚ ምግብ ዋስትና’ ተሻግራለች።
ኤርትራ አሁን ላይ 785 ኩሬዎችና ግድቦች አሏት። ከሰላ አመት በፊት ራሷን የቻለች ሀገር በሆነችበት ወቅት የነበሯት 138 ኩሬዎችና ግድቦች ነበር።

በፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግስት ከተመዘገቡት ሌሎች ስኬቶች መካከል የኤርትራ በግብርና ላይ ያከናወኗቸው ተግባራት ጥቂቱ ነው። የቀጠናው ኤክስፐርት እና የኬንያ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የነበሩት ፋራህ ማሊም ኤርትራ ከዕዳ ነፃ የሆነች፣ በቴክኖሎጂ የዳበረች፣ በምግብ ምርት ራሷን የምትችል እና ወደ ጤናማ መሠረተ ልማትና ደህንነት እንዲህ ስታመራ ማየት አስደሳች ነው ብለዋል። ግዛት – ምንም እንኳን ምዕራቡ ልማቱን ለማደናቀፍ ሁሉንም ነገር ቢያደርግም በጉብኝቴ ወቅት የመንግስት ባለስልጣናት ቀላል አኗኗር ትኩረቴን ስቦ ነበር።
የአፍሪካ አገሮች ከኤርትራ የልማት መጽሐፍ አንድ ገፅ ማውጣት በርግጥም ይችላሉ።

first published on the star website ?

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories