የሠራዊቱ ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የሕወሐትን ፕሮፓጋንዲስቶችን ሟርት አምክኗል

የሰብአዊ ርዳታና መሠረታዊ አገልግሎቶችን ስለማስቀጠል፣
ከመንግስት ኮሙኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ

▪️የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተሞች ጦርነት እንዳይደረግ በተከተለው ጥብቅ ዲሲፕሊን፣ በሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጓል፡፡

▪️ሰራዊቱ ከተማ ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ሽሬ፣ አላማጣና ኮረም ከተሞችን ለመቆጣጠር ችሏል። ይህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከተለው ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የሕወሐትን ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋቡ የነበሩ አካላትን ሟርት ያመከነ ነው።

▪️ከዕርዳታ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት፣ መከላከያ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ርዳታ በተቀላጠፈ መንገድ እንዲደርስ መንግሥት በቂ ዝግጅት አድርጓል። ይሄም የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያን ተጠቅሞ ርዳታ ማድረስን ይጨምራል።

▪️መንግሥት ከሰብአዊ ርዳታ ተቋማት ጋር በተቀናጀ አሰራር ሰብአዊ ርዳታ የሚደርስባቸውን መንገዶች በማስፋፋት በሰሜን ጎንደር በኩል ወደ ሽሬ የሚወስደውን እና ከኮምቦልቻ – ደሴ ወልድያ ቆቦ አላማጣ ያለውን መንገድ ለመክፈት እየሠራ ነው።

▪️ይህንኑ ሥራ የሚያሣልጥ ኮሚቴ ከሚለከታቸው አካላት ተወጣጥቶ ሥራ የጀመረ ሲሆን እነዚህ ሥራዎች ቴክኒካዊ የሆኑ ጥናቶችን እና ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር የሚያስችሉ መሠረታዊ ሥራዎችን ይጨምራል።

▪️የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተወሰኑ የትግራይ ክልል ከተሞችን መቆጣጠሩ ተከትሎ ከተሞች የጦርነት ቦታ እንዳይሆኑ የጥንቃቄ አካሄድ እንደሚከተል
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በቅርቡ ባወጣው መግለጫው ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

በኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
FDRE Government Communication Service
ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories