የናይል ተፋሰስ ሀገራት ከግብፅ ጎን እንዲሆኑ ዓለም አቀፍ ጫና ይደረግልን: ካይሮ

          የዓባይ:ልጅ

በ UN የውሃ ኮንፈረንስ ላይ የተገኙት የግብፅ መስኖ ሚኒስትር በዓባይ ጉዳይ ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ህግና መርሆዎችን ጥሳለች በማለት ምዕራባዊያን ድጋፍ እንዲያጠናክሩላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም የአረብ ሀገራትን የውሃ ችግር ለመቅረፍ ግብፅ በትኩረት እየሰራች መሆኑን እወቁት ያሉ ሲሆን፤ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት በግብፅ ስትራቴጂ መሰረት ተገዢ እምዲሆኑም አለም አቀፉን ማህበረሰብ በአፅንኦት ጠይቀዋል። የግብፃዊው ምኒስትር አበይት መልዕክቶች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፦

▪️ውሃ በሰው ልጅ ሕልውና ላይ ከምንተነፍሰው ኦክሲጅን ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ የውሃ ሰብአዊ መብት መሟላት የሰው ልጆችን በህይወት የመኖር መብትንም ሆነ ለትኛውም አይነት ሰብአዊ መብቶች መከበር ውሃ ቅድመ ሁኔታ ነው።

speech by egypt minister of irrigation

▪️ዓለማችን ለተደቀነባት የውሃ አቅርቦትና የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎች ግብፅ ዋነኛ ምሳሌ ሀገር ስትሆን፤ በሀገሯ ከሚፈጠሩ ተግዳሮቶች ብቻም ሳይሆን በተቀሩት የተፋሰሱ አገሮች ያሉ ሁሉም ተግዳሮቶች በኛ ላይ አደጋ የጋረጡ ናቸው።
▪️ከግብፅ ታዳሽ የውሃ አቅርቦት 98 በመቶው በዓባይ ወንዝ ላይ የተመሰረተው ሲሆን፤ 50 በመቶው የምግብ አቅርቦቷንም ከዚሁ በናይል ውሃ ከሚለማ እርሻ ነው የምታገኘው።
▪️ከግብፅ ሕዝብ ግማሹ የሚተዳደረውም በናይል ውሃ ላይ በተመሰረተ ግብርና ላይ ነው።
▪️የተጋረጠባትን የውሃ እጥረት ከግምት በማስገባት በውሃ አቅርቦት ልማት ላይ በከፍተኛ መጠን ኢንቬስት ማድረግ የጀመረችው ግብፅ ባለፈው የአምስት ዓመት እቅዷ 10 ቢሊዮን ዶላር በጀት ነው ዪደበችው። ይህም ግብፅ ከዓመታዊ ወጪዋ ከፍተኛው የሆነውን የምግብ ግዢ ከውጭ ለማሟላት 15 ቢሊዮን ዶላር በየአመቱ እንድታወጣ ትገደዳለች።
▪️ከነዚህ አደጋዎች አኳያ ውጤታማ የወሰን ተሻጋሪ ወንዝ የውሃ አጠቃቀም ትብብር ለግብፅ የህልውና ጉዳይ ሲሆን፤ ትብብሮቹ ስኬታማ እና ጠቃሚ እንዲሆኑ የጀመርነው የተቀናጀ የውሃ-ሀብት አስተዳደር ስራችን በተቀሩት የተፋሰሱ ሀገራት ደረጃም በተመሳሳይ ተፈፃሚ እንዲሆን ድጋፍ እንፈልጋለን።
ይህም የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች የውሃ ትብብር አለም አቀፍ ህግና መርሆዎች ሳይንሳዊ ጥናቶችን መሰረት ባደረገ ምክክርና ትብብር አንድ ባንድ ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል። በዚህም ፍትሃዊ የአጠቃቀም መርሆዎችን ተፈፃሚ በማድረግ ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ የሚለውን መርሆ ለማስከበርም በጣም አስፈላጊ ነው።
▪️ከዓለም አቀፍ ሕግ ዋነኛ መርሆዎች የሚጣረስ የአንድ ወገን ርምጃ አደጋ እንደሚያስከትል ግልጽ መሆን የሚገባው ሲሆን፤ “የዚህ ዋነኛ ማሳያ ደግሞ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲሆን፤ ይህም ግንባታው በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የሚያደርሰው አካባቢያዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ያልተፈተሸ በመሆኑ የሚከሰት ነው።”
▪️የግድቡ ግንባታ አጀማመርና የውሃ ሙሌት በአንድ ወገን ተጀምሮ እየቀጠለ መሆኑ የ 2015 የመርሆዎች መግለጫ ስምምነትን ጨምሮ አለም አቀፍ ህግን ይጥሳል። የመስከረም 2021ዱን የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንታዊ መግለጫም ውድቅ ያደረገ ነው። ይህ የአንድ ወገን አካሄድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ግብፃዊያንን ስራ አጥ የሚያደርግና፤ 15%ውን የግብፅ የእርሻ መሬቶች ከጥቅም ውጭ አድርጎ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥረቶች መባባስ እንዲሁም የሕገ-ወጥ ስደት አደጋዎችን የሚጨምር ይሆናል።

speech by egypt minister of irrigation

▪️ግብፅ በቀጣናዊ ጥረቶቿ የአፍሪካ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት – AMCOW ሊቀ-መንበር በመሆኗ ኩራት የሚሰማት ሲሆን ጅምሩን ከአፍሪካዊ አጋሮች ጋር ለማንቀሳቀስ የፋይናንስ አቅርቦት ወሳኝ መሆኑን እናሳውቃለን።
▪️በሁሉም አይነት አለም አቀፍ የውሃ ጉዳይ ርብርቦች ውስጥ ጥረት የጀመረችው ግብፅ በተመድ የውሃ ጉዳዮች ልዩ ልዑክ መሾምን ጨምሮ በአጠቃላይ የጀመረቻቸው ቁልፍ ሚናዎቿን የምታጠናክር ይሆናል።
በተጨማሪም በአረቡ አለም ያለውን ፈታኝ የውሃ እጥረት ችግር ለመቅረፍ የሚደረጉ ጥረቶች እንዲጠናከሩም ግብፅ በትኩረት እየሰራች ነው።
▪️በተመድ የውሃ ኮንፈረንስ UN Water Conference ላይ ግብፅ ትልቅ ተስፋ መጣሏን ስገልፅ፤ ኮንፈረንሱ ከውሃ እጥረት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቋቋም ግልጽ የድጋፍ መንገዶችን እንደሚቀይስም ባለ ሙሉ ተስፋ ነን። በጉባዔው የተነሱትን ታላላቅ ሀሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ የሚወሰዱ ፈጣን ርምጃዎችንም በደስታ እንቀበላለን።

Esleman Abay #የዓባይልጅ

#UNWaterConference2023 #UNWaterConference #ኢትዮጵያ #sudan #Egypt

#Nile #bluenile #Ethiopia #NileBasin

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories