የአሜሪካ ማዕቀብና ጫና – የካይሮ ቀሪ ተስፋ

    ▪️የዓባይልጅ ✍️

የአንድ ሀገር ህገ መንግስት ተፈፃሚነት በግዛቷ ውስጥ የተገደበ ቢሆንም የውጭ ግንኙነት ላይም ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው። Foreign policy is a reflection of domestic policy እንደሚባለው።
ናይል የሚለው ስም 7 ጊዜ የተጠቀሰበት የግብጽ አዲስ ህገ-መንግስት መግቢያው ላይ “ግብፅ የናይል ስጦታ ነች እንዲሁም የግብፃውያን ስጦታ ለሰብዓዊነት” ይላል፡፡ ይህ የማይካድ ቢሆንም ሆን ብሎ የተተወ ሀቅ መኖሩንም እዚጋ ልብ ይሏል። ሳይንሳዊ ግኝቶል ይፋ እንዳደረጉት ግብፅ ያለ ዓባይ ለ500 ዓመታት የሚበቃ የከርሰ ምድር ውሃ ባለቤት ናት፡፡

የአረብ ፀደይ አብዮትን ተከትሎ የሆስኒ ሙባረክ መንግስት ሲወገድ የተተካው የሞሐመድ ሞርሲ መንግስት ስለ ናይል ያንፀባረቀው ነባሩን ፈርኦናዊ አቋም ነበር። ይኸውም “የደም ጠብታችን ወይም የናይል ውሃ” የሚል ሲሆን የሙርሲ አስተዳደር ግን ብዙም ሳይቆይ በሀይል ተወግዷል።
ከሞርሲ በኋላ የነበረው የግብፅ የሽግግር መንግስት ህገ-መንግስቱን የማሻሻል ስልጣን የተሰጠው ሲሆን፤ ሃምሳ አባላት ያለው ኮሚቴው አጠናቅቆ ለፕሬዝዳቱ የህገ መንግስቱን ረቂቅ ማስረከቡ ይታወሳል፡፡
ረቂቅ ህገ-መንግስቱ በጥር 14 እና 15 2013 እኤአ ቀርቦ በ97 በመቶ ድጋፍ ማፅደቃቸውን ተናግረዋል፡፡ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 44 ስለ ዓባይ ውሃ ያስቀመጠው ድንጋጌ የግብፅን ጥንታዊ ግትርነት በተለዬ ያስረጠ ነበር።

በግብፅ ህገ-መንግስት አንቀጽ 44 “መንግስት የናይልን ወንዝ ለመከላከል፣ እንዲሁም የግብፅን ታሪካዊ መብት ለማስጠበቅ፣ ጥቅሞቹንም ለማሳደግ እና ለማረጋገጥ፣ ውሃውንም ከብከነት እና ከብክለት ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው፡፡…. (The state commits to protecting the Nile River, maintaining Egypt’s historic rights.. ይላል፡፡
“…የግብፅን ታሪካዊ መብት ለማስጠበቅ…” የሚለው ድንጋጌ ግብፅ በቅኝ ግዛት ዘመን በእንግሊዝ የተፈረመውን የ1929 “ስምምነት” እና 1959 በግብፅ-ሱዳን የተደረገውን ነው፡፡ “ስምምነቶቹ” ግብፅ የላይኛው ተፋሰስ የሚኖሩ የውሃ ፕሮጀክቶችን የመቆጣጠር፣ የመፍቀድና የመከልከል መብት የሚሰጡ ነበሩ፡፡
ስምምነቱ የሚጠቅሰው የውሃ ድርሻም ለላይኛው የናይል ተፋሰስ ሀገራት አንድም ጠብታ ውሃ የማይሰጥ ነበር፡፡ ሀገራቱም አልተሳተፉበትም።
ግብፅ “ታሪካዊ መብቴ” የምትለው ይህን ፈርኦናዊ ስምምነት ነው፡፡ በወቅቱ ኢትዮጵያ ስምምነቱ ሲፈረም በይፋ በዓለም መድረክ ተቃውሞዋን ያሰማች ሲሆን፤ ኢትዮጵያን ያላማከለ ማናቸውም የናይል ስምምነት ዋጋ የሌለው እንደሆነ በቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ መግለጫና በካይሮ ዲፕሎማቶቿ 1957 ላይ አወጃለች፡፡ ማንኛውም ያልተሳተፈችበት ውል የዓባይን ውሃ ከመጠቀም እንደማያግዳትና የዜጎቿን ፍላጎት ለማሟላት ሀብቷ የሆነውን ውሃ እንደምትጠቀም ይፋ አድርጋለች፡፡
በወቅቱ በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ ሀገራትም ነፃ በወጡ ማግስት መሰል የቅኛ ገዢ ስምምነቶችን ውድቅ አድርገዋል፡፡ (የኔሬሬ ዶክትሪን ለዚህ አንዱ አብነት ሊሆን ይችላል።)

በዓለም አቀፍ የውሃ ህግጋት ውስ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል ወጥ ድንጋጌ ባይኖርም ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች በተለያዩ ክስተቶች ላይ ያሳለፏቸው ውሳኔዎችና ወሰን ተሸጋሪ ወንዞች ላይ በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት ወደ ልማዳዊ ህግነት ያደጉ መርሆች አሉ፡፡ የሆነ ሆኖ ታሪካዊ መብት በሚል ዓለምአቀፍ ህግ የሚያውቀው መርህም ሆነ ድንጋጌ የለም፡፡ “ታሪካዊ መብት” “ቀድሞ የመጠቀም፣ የቆየ መብት” በሚል ሲጠቀስ ቢታይም ከስም ያለፈ ሚና የለውም።

በዚህም ግብፅ ዓለም አቀፋዊ የህግ መሰረት የሌለውን “ታሪካዊ መብት” የሚል ድምጋጌ በህግ-መንግስቷ ማካተቷ የሚያስገኝላት ህጋዊ ውጤት የለም፡፡ ይልቁንም የናይልን ውሃን በተመለከተ ለሚደረጉ ውይይቶች ፍቃደኛ አለመሆኗን ድጋሚ ያስረገጠ ነው።

ከቀናት በፊት በዋሽንግተን የግብፅ አምባሳደር “ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ወደ ድርድር እንድትገባ ማበረታታት ፣ ማስገደድ እና ኢትዮጵያ በግድብ ስራው የምታካሂደውን የአንድ ወገን (የብቸኝነት) እርምጃ እንድታቆም ፣ አሜሪካ ተፅዕኖ የማድረግ አቅም አላት።” ስትል የገለፀችው ከህጋዊ መፍትሄ ይልቅ አማራጯ በጫና ይሳካ እንደሆነ ለመሞከር ነው።

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories