የኢማራት-እስራኤል ስምምነት ከኢትዮጵያ አንፃር

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና እስራኤል ሙሉ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመጀመር ስምምነት ፈርመዋል። በርካታ ሚዲያዎች የሰላም ስምምነት ቢሉትም አገራቱ ግን የጦርነት ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

ከእስራኤል ጋር መሠል ግንኙነት ያላቸው አረብ አገራት ሁለት ነበሩ። ከግብፅና ዮርዳኖስ በመቀጠልም UAE ሶስተኛ ሆናለች።

ለኢትዮጵያ ምን አንድምታ ይኖረው ይሆን?

ስምምነቱን ለወሳኝ የዲፕሎማሲ ውጤት መጠቀም እንችላለን ባይ ነኝ። ይኸውም አገራችን በቀደሙት ጊዜያት በእስራኢልና ፍልስጤም ጉዳዮች ላይ ያራመደቻቸውን አቋሞችና ያተረፈቻቸውን የዲፕሎማሲ ድሎች ያስታውሳል። የአረቡን አለምና ምዕራቡን ባማከለ አካሄድ ውጤታማ እንደነበርን አምባሳደር ዘውዴ ረታ ከትበውታል።

ሌላው የ UAE ርምጃ ግብፅ ለፋይዳዋ እንዳታውለው መስራት ነው። የትራምፕን deal of the century ለማሳካት ግብፅ የተቀረውን አረብ አገር ታሳምን ዘንድ ለተሰጣት የቤት ስራ እንደ ስኬት ለማስቆጠር ስምምነቱን የኔ ስራ ውጤት ነው ማለቷ አይቀሬ ነው። ስምምነቱን አል-ሲሲ በማሞካሸታቸው በአገር ውስጥ ከፍተኛ ትችት እየቀረበባቸው ነው። ፍልስጤምን ለፖለቲካህ ስትል ክደሃታል፤ ሸጠሀታል በማለት። በአንፃሩ ቤንያሚን ናታንያሁ ግብፅ፣ ዮርዳኖስና አሜሪካን ለአበርክቷችሁ አመሰግናለሁ ብለዋል። ይህም ከግድቡ በድርድር ላይ የሚኖረውን አንድምታም እንድናጤን ያደርጋል።

ይሁን እንጅ ስምምነቱ ለአመታት ግብፅ ሞኖፖሊ ተይዞ የነበረውን የአረቡ አለምና አሜሪካ ድልድይነት ይቀንሰዋል እላለሁ። በተለይም ግብፅ የእስራኤልን የሀይል ይዞታዎች ማካለል ተፈፃሚነት በመደገፏ ነበር አሜሪካ በግድቡ ጉዳይ እንድትጫነን ስትሞክር የቆየችው። እንደ መልካም አጋጣሚ ግን በ UAE-እስራኤል ስምምነት ቴላቪቭ የይዞታ ማካለል እንቅስቃሴዋን እንድታቆም ተደርጓል። ይህ ለአል ሲሲ ኪሳራ ነው።

UAE ከቁጥር ያለፈ ሚና ይኖራታል የሚለው የበርካቶች ምልከታ ሆኗል–የእስራኤሉ haritez እንዳስቀመጠው። አሜሪካም ሰፊ የትብብር ማዕቀፍ ለ UAE ማዘጋጀቷ በስፋት ተወርቷል። የግብፅ ብቸኛ ተጫዋችነት እምብዛም እንደማይሆን ይሠማኛል።

ከዱባይ ጋር የጀመርነውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ግብፅን ለማምከን ይጠቅማል። ግብፅና ዱባይ በሊቢያና በፀረ ኤርዶጋን አቋም በአንድ የቆሙ ናቸው። ይሁንና የፋይናንስ ድጋፎች ከ IMF እና WORLD BANK እንዳይስተጓጎል UAE አሁናዊ ሚናዋ ወሳኝ ነው። ሌሎች አረብ አገራትም የ UAE ን መንገድ ለመከተል እያማተሩ መሆናቸውም ዋሽንግተንን ጮቦ አስረግጧልና።

ዛሬ በወጣ ዘገባ ደግሞ UAE እና እስራኤል በቀይ ባህር የጋራ ጦር ለማቋቋምና በደህንነት ረገድም በመተባበር ለመስራት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ይህ የ UAE ን የአፍሪካ ቀንድና የባብ-ኤል-ማንዴብ ተፅዕኖ ያሳድጋልም ተብሏል።

ሌላው በእስራኤል ጉዳይ የተለወጠው የአረብ ሊግ አቋም ነው። አሁን እንደ ድሮው አይደለም። ለዘብተኛ ሆነዋል። ስምምነቱ በፍልስጤም ኢራን፣ ቱርክና ኳታር ተወግዟል። ጠቅላይ ምኒስትር አቢይ የስምምነቱን ተገቢነት ደግፈዋል። አሁናዊውን የአረብ ሊግ አቋም ያገናዘበ ይመስላል፤ የአቢይ አቋም።

ስምምነቱን ከደገፈችው ሱማሌላንድ ጋር ዱባይ ቁልፍ ወዳጅ ሆናለች። በወደብና መሠረተ ልማት ኢትዮጵያ ከዱባይና ሀርጌሳ ጋር በሶስትዮሽ ተወዳጅተዋል። ሌላኛው አጋጣሚ መሆኑ ነው።

በአንክሮ ታይቶ በብስለት መከወን ያለበት የዲፕሎማሲ የቤት ስራችን ተቀናቃኝ ጎራዎችን እንዴት አጣጥመን ወይም መርጠን እንይዛለን? የሚለው ነው። ከ UAE ጋር ያለን ትብብር በተቃራኒ ካሉት ነገር ግን ከአገራችን ጋር የትብብር ግንኙነት ካላቸው ከነ ኳታርና ቱርክ መሠል አገራት ጋር ባልተፃረረ እንዴት እንጓዝ? ቁልፍ ጥያቄ ነው። ገለልተኛ በሆነ አቋም ሁለቱንም ጎራዎች በአንፃራዊ አወንታ መያዝ ቢቻልም የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ትኩሳት ግን መርጦ መያዝና መጣልን አስገዳጅ የሚያደርግ ሁኔታ እየመጣ ነው።

የሩቁን አስቦ ጠቃሚውን የዲፕሎማሲ አቋሞ ቀርፆ መዘጋጀት ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው እላለሁ።

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories