አለምአቀፍ የመረጃ ተመራማሪው አሮን ኦኔል በሌሎች መድረኮች በቀላሉ የማይገኙ አስተማማኝ መረጃዎችን በማውጣት ይታወቃል።
የሀገራችን ኢኮኖሚን በተመለከተ በሜይ 2022 ያወጣውን መረጃዎች Statitsta ድህረ ገፅ ላይ የቀረበውን በአጭሩ እናሳያለን።
እ.ኤ.አ. ከ1987 እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ የሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 2027 ድረስ ያለውን ይህን ይመስላል። ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) በማንኛውም አመት ውስጥ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚመረተውን ሁሉንም አገልግሎቶች እና እቃዎች አጠቃላይ ዋጋ የሚያሳይ ነው።
የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ሃይል አስፈላጊነትን አመላካች ነው።
የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት እንደ እ.ኤ.አ በ2016 ከነበረበት 72.12 ቢሊዮን ዶላር ወደ በ2021 99.27 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም በ5 አመት ውስጥ 27.35% ማደጉን ያሳያል። (Statista)