የኢትዮ-ራሺያ ልብ፡ለልብ

  እስሌማን ዓባይ

ለትላንቱ ተአምራዊ ድል አንዱ ሚስጥር ከዚህ ብሶት ጋር የተያያዘ ይሆን? በሩሲያ መስኮብ ከተማ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የነበሩ ምሁር ከአራት አስርት አመታት በፊት ስለ ዓባይ እና ግብፅ ተከታዩን ተናግረው ነበር፦

“..በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠር ሰብዓዊ ፍጡር በሀገሪቱ በደረሰው ረሀብ እንደ ዝንብ ሲረግፍ፤ የሌላ ባዕድ ሀገር ህዝብ የረሀብ ሰለባ እንዳይሆን በዬአመቱ በብዙ ቢሊዮን ሜትር ኩብ የሚገመት የውሃ ሀብቷ ጥሏት ሲጓዝ ኢትዮጵያ በጥሞና ሁኔታውን መመልከት ይከብዳታል። በሌላ በኩል በወንዙ ግርጌ የሚገኝ ሀገር ሳያቋርጥ በሚፈስለት ውሃ የሚገለገል፤ ይህን የመሰለ መአት እየተመለከተ ጉዳዩን እንደራሱ ችግር አድርጎ ካልቆጠረ፤ ይህ ሀገር (ግብፅ) ከወንዙ በላይ ባለው ሀገር ምንም አይነት ወቀሳ ለማቅረብ የሞራል ኃይል ፈፅሞ ሊኖረው አይችልም።”
▪️የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩት ዶክተር ንጉሴ አየለ በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ስለ ዓባይ ጉዳይ የተናገሩት፤ ወርሀ ነሐሴ 1986 ዓ.ም
~ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በኢምፔሪያሊስቶች ሴራ የተነሳ ተመሳሳይ የስቃይ ታሪክ አላቸው። በህዳሴ ግድቡ ጉዳይ በተጠራው የተ.መ.ድ ፀጥታው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ሩሲያ ለኢትዮጵያ የቆመችው ከወቅቱ ትዝብቷ ላይ ብቻ ተመስርታ ሳይሆን ዘመናት ያስቆጠረውን የጋራ ህመማቸውንም ከማገናዘብ የመነጨ ነበር – የኢትዮ-ራሺያ ልብ፡ለልብ!
🔹 #የዓባይልጅ

ዋቢ
▪️Ashok Swain, “Ethiopia, the Sudan, and Egypt: The Nile River Dispute”. The Journal of Modern African Studies, 1997

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories