የካይሮው ተኩላ | የኢትዮጵያ ጎረቤቶችን የማማለል ዘመቻ

first published oct 2020

Esleman Abay

ኢሳያስ በኢትዮጵያ ጂኦ-ፖለቲካ ላይ ቁልፍ ሰው? ወይስ የኛ ተመፅዋች? ይህን በውል ለመገንዘብ ኢሳያስ በካይሮ ገበያ ዋጋው ስንት ነበር? ብለን ማሰላሰሉ የተሻለ ነው።

1, አስመራ ለካይሮ ምን ነበረች?

ፕሬዘዳንት ኢሳያስ የሕዳሴ ግድባችንን እና አየርሃይሉን መጎብኘታቸው ለፎቶ ፍጆታ እንዳልሆነ የሚያስገነዝቡን በርካታ እውነቶች አሉ። ጉብኝቱን በተመለከተ የግብፅ ሚዲያዎች ዝምታን ነበር የመረጡት። ከ 10 ቀናት በኋላ አል-ሞኒተር አፈነዳው። ካይሮና አስመራ ኮንትራታቸውን እንዳቋረጡ።

በወቅቱ የሚያስገርሙ ግጥምጥሞሾችም ተከስተዋል። የበርካቶች እምነት የነበረው ከኢትዮ-ኤርትራ እርቅ ወዲህ ኢሳያስ ከግብፅ ጋር የነበረውን ትስስር እንደበጠሰ ነበር። የህወሃት ጠብ ከኢሳያስም ከአብይም ጋር መሳ ለመሳ መጓዙ ደግሞ እንደ ሁነኛ አስረጂ ይወሰድ ነበር። እውነታው ግን እስካለፈው የኢሳያስ ጉብኝት ድረስ ኢሳያስ የካይሮ ኮንትራቱ አምሳ-አምሳ ነበር ወይም ደግሞ እንደቀጠለበት ነበር።

አዚጋ ኤርትራ አቋሟን ወደ ኢትዮጵያ ሳታደርግ፣ የግብፅ አጋር በነበረችበት ጊዜ የነበረውን እንይ።
ከሁለት ወራት ቀደም ብሎ ሐምሌ ላይ ኢሳያስ ካይሮ ነበሩ። ጉብኝቱ በግድቡ ዙሪያ ዋና አጀንዳ የያዘ ነበር። የሁለት ቀናት የካይሮ ጉብኝቱ ከተጠናቀቀ ከ 3 ቀናት በኋላ የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር የሚከተለውን ይፋ አደረገ። “
“የኤርትራና ኢትዮጵያ ዕርቅ አስመራ የጠበቀችውን አላመጣም። የኢትዮጵያ ጦር ግዛታችን እንደሰፈረ ነው። በንግድና ኢኮኖሚው ሊደረጉ የነበሩ ስራዎችም የረባ ነገር አላመጡም” መግለጫው አስመራ ከካይሮ አለመፋታቷን ያሳውቃል። ኤርትራ ለግብፅ ምን ያህል ጠቀሜታ እንደነበራት የሚነግረን የካይሮ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሠር በወቅቱ ለአል ሞኒተር የሰጡት አተያይ ነው። የፖለቲካል ሳይንስ ፕሮፈሠሩ አብደል-ራህማን ሀሠን “በኢሳያስ የስልጣን ዘመናት ውስጥ በአፍሪካ ቀንድ የሐይል ቀመር ላይ ቁልፍ ተዋናይ ነች። የኤርትራ ጂኦ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ለዚህ ረድቷታል። ኢሳያስ አፈወርቂም የቀጠናውን ቀውስ ለጥቅማቸው ማዋልን ተክነውበታል” ነበር ያሉት። ምሁሩ አክለውም “የዋሽንግተኑ የግድቡ ሶስትዮሽ ድርድር ያለ ውጤት መቋጨቱን ተከትሎ ኢሳያስ በጉዳዩ ላይ ለግብፅ ነው የወገኑት። ኤርትራ ለገልፍ አገራት ያላት ጆግራፊያዊ ቅርበት በተለይም ከሳዑዲና ኢምሬትስ ጋር ያላት ቅርብ ትስስር ለግብፅ መልካም ፋይዳ ፈጥሯል። በተለይም በወሳኝ ጊዜያት” ሲሉ አብራርተዋል።

ኤርትራ ለግብፅ የጦር ሃይል ግዛቷን ስለመፍቀዷም በወቅቱ ሲወራ ነበር። ምንም እንኳን በካይሮ የኤርትራ አምባሳደር ፋሲል ገብረ ስላሴ ቢያስተባብሉትም።

“የግድቡን አለመግባባት ግብፅ በጦር ሃይል ጫና ለመፍጠር ከፈለገች ኤርትራ የሚኖራት ጠቀሜታ መተኪያ የሌለው ነው” የሚለው በ Al-Ahram Center for Political and Strategic Studies ምሁር የሆኑትን ግብፃዊ ሐኒ ረስላን ንግግር እዚጋ ማስታወስ አስመራ ለካይሮ ምን ያህል ተስፋዋ እንደነበረች ያስረግጥልናል።
(ልብ እንበል! ይህ የሆነው ከኢሳያስ የግድቡ ጉብኝት በፊት ነበር)
……….
2, የኢትዮጵያ ጎረቤቶችን ለመያዝ የግብፅ አዲስ ዘመቻ

ከ 3 ቀን በፊት አል ሲሲ የደ.ሱዳን መስኖና ውሃ ሃብት ሚኒስትርን ወደ ካይሮ ለስብሰባ ጠርተዋል። በዚህም

የደ.ሱዳንና ካይሮ ከፍተኛ ጥምር ኮሚቴ ባስቸኳይ እንዲመሠረት ግብፅ ዕቅዷን ገልፃለች።

ኮሚቴው የተያዘው 2020 ሳያልቅ የመጀመሪያ ስብሰባ እንዲያደርግ ታቅዷል

የግብፅ ማዕከላዊ ባንክ CBE በጁባ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ እንዲከፍት

ግብፅ ለደ.ሱዳን በውሃና መስኖ ለምትሻው ድጋፍ አለንሽ ብለዋታል

ደ.ሱዳን ጋር ምክክር ካደረጉ ከአንድ ቀን በኋላ ደግሞ አልቡርሃን ወደ ካይሮ አቀኑ።

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሌትናንት ጀነራል አብዱል አልፋታህ አል ቡርሃን ለአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት ወደ ግብጽ ያቀኑት በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነበር።

በጉብኝቱ የሱዳን የደህንነት ሹም ሜጀር ጀነራል ጀማል አብዱል መጅድ አብረው ነበሩ።

ሱዳናዊ ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ወደ ካይሮ ያቀኑበት ምክንያት ምን እንደሆነ መግለፅ አልተፈለገም።

ሱዳንና ግብፅ በባቡር መሠረተ ልማት እንዲተሳሰሩ መስማማታቸውን የግብፅ ሚዲያዎች ዛሬ ዘግበዋል።

ሱዳን እንዳዲስ በተጀመረው የግድቡ ድርድር ላይ አዳዲስ ጥያቄዎች ማንሳት መጀመሯንም ታዝበናል።

3, በኢትዮጵያ በኩል

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል እንዲመሠረት የታቀደው ከሁለት አመት በፊት ነበር። በወቅቱ በ 100 ቀን ውስጥ ወሳኝ ጉዞ እንዲኖረም ተነግሮ ነበር። ይሁንና በተያዘው አመት እንደሚቋቋም በይፋ የተነገረው ግብፅ ኢሳያስ አቋሙን ቀየረብኝ ባለችበት ፕሬዘዳንቱ ግድቡን በጎበኙበት ሰሞን ነው።

የኤርትራ የኢትዮጵያና ሶማሊያ ደህንነት ሹሞች በአዲስ አበባ ተገናኝተው መምከራቸውን Horn daily የዘገበው ከቀናት በፊት ነው።(ከሌላ ምንጭ ማረጋገጥ ባልችልም)
………….

በመጨረሻም፦
የግብፅ ተኩላዎች የአፍሪካ ቀንድ አዲስ ዘመቻ ፍፁም እንግዳ ክስተት ባይሆንም ጎረቤት አገራት ከጃችን እንዳይወጡ የቤት ስራ እንደሚጠብቀን ይጠቁመናል።

ለግብፃዊው ተኩላ ምሱ የውስጥ አለመግባባታችንና ግጭታችን መሆኑን የምናውቀው ነው።

የዓባይ ልጅ | እስሌማን ዓባይ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

2 thoughts on “የካይሮው ተኩላ | የኢትዮጵያ ጎረቤቶችን የማማለል ዘመቻ”

  1. Getachew HailMichael Goshu

    በቅድሚ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በተከታታይ በተለያዩ media platform ለምታቀርባቸው ዘግባዎች እና ወቅቱን የጠበቁ ትንተናዎች ትልቅ ክብር አለኝ :: ይህ ፅሑፍ የ 5ወር ቆይታ ቢኖረውም በድህረ ግፁ ላይ ሳነበው የተሰማኝ ነገር ቢኖር ለ አለፉት ተከታታይ ወራት የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካ በሚገርም ፍጥነት ተገለባባጭ መሆኑን ነው :: እነዚህ ፅሑፎች ዛሬ ላይ ታሪክ ናቸው በተለያየ ግዜ የፃፍክካቸውን ዞር ብለን ብንመለከት እና የየእለቱን ሁኔታ እንደሚከታተል ሰው የሆነ ህልም ነው የሚመስሉ ሁኔታዎች ውስጥ እንደነበርን ተጨባጭ መረጃዎች ናቸው :: እነዚ ህ ዘገባዎች ሳይሸራረፉ ወደፊት በአንድ መፅሐፍ በደንብ ተሰንደው ይወጣሉ ብዬ አምናለው :: ትውልዱም ለዛሬ ማንነታችን እና ለነገዋ ኢትዮጵያ በታሪካዊ ጠላት እና ወዳጆቻችን የመጣንበትን የፖለቲካ ፍዳ በደንብ እንዲያውቅ አስተዋጾ ይኖረዋል ባይ ነኝ ::

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories