የካይሮ ሀይማኖታዊ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ

ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ድሮኖች መሬቱ ቤተ ሙከራ፤ የህወሃት ታጣቂዎች ደግሞ እንደ ጊኒ ፒግ የላብራቶሪ ቫይረስ ያህል ነበር ያገለገለው፤” አንድ የህወሃት ወራሪዎች መሪ በቅርቡ የሰጠው አስተያየት ነበር። በአማራና አፋር ውጊያዎች የገጠማቸውን ከባድ ምት ተከትሎ ይህን አስተያየት ከሰጡ ቀናትና ሳምንት አለፉ።
ከሰሞኑ ደግሞ ሀይማኖታዊ መልክ የተሰጣቸው የግጭት ክብሪቶች ሲዘዋወሩ ይታያሉ። ሙከራዎቹ ሁለቱንም እምነቶች ማለትም እስልምናንም ክርስትናንም የሚተናኮሱ ናቸው።
የምራባዊያኑ ወታደራዊና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ህወሃትን ከሽንፈት አላደነውምና የተራረፈው ሀይል ወደ ትግራይ መመለሱን የሰማችው ካይሮ በፅኑ ስትንገበገብ ነበር። የሀይማኖት መልክ በያዙት ሰሞነኛ ሴራዎች ውስጥስ የካይሮ እጅ ይኖር ይሆን? በርግጥም፣ ካይሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትያንም ሆነ እስልምናን የተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ስትንቀሳቀስ ነው የቆየችው።

በያዝነው አመት በወርሃ መስከረም በግብፅ የአሌክሳንደሪያ ኮፕቲክ እርቶዶክስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስ፣ ታዎድሮስ 2ኛ፣ የሕዳሴ ግድቡ ግብፅ ላይ የደቀነውን ስጋት ቤተክርስቲያኒቱ ሚና አላት ሲሉ መግለጫ ሰጡ። “ቤተክርስትያኗ እንቅስቃሴ እንደምታደርግና በናይል ወንዝ ዙሪያ አቋማችንን ግልፅ ለማድረግ እየሞከርን ነው፣ ነገር ግን ጉዳዩ 100 በመቶ ፖለቲካዊ መልክ ይዟል” ያሉት ፓትሪያርኩ ሲቀጥሉም “እስከ 1959 ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በግብፅ ስር ነበረች። ጳጳሳት የሚላኩት ከግብፅ ነበር። በ1959 ጀምሮ ነው አፄ ኃይለ ሥላሴ በግብፅ ይሰየም የነበረ ጳጳስ እንዲቀር ያደረጉት። በዘመነ ደርግ ደግሞ የኮሙኒዝም ርዕዮተ አለሙ ለሃይማኖታዊ ተሳትፏችን ፍፁም የማይመች ነበር። አሁን ላይ ግን ያሉ አጋጣሚዎችን ሁሉ የምንጠቀም ይሆናል” ብለዋል።

አልሞኑተር ባቀረበው በዚሁ ሪፖርት ላይ የአል-አህራም የፖለቲካና የስትራቴጂ ጥናት ማእከል የአፍሪካ ጉዳዮች ኤክስፐርት አማኒ አል-ታዊል ለአል እንደተናገሩት “መንግስት በአፍሪካ ሀገራት ተጽእኖ ያላቸውን ሁሉንም የ Soft power አማራጮች በተለይም የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ቢጠቀምባት ያተርፍበታል” በማለት ተናግረዋል። በተጨማሪም “የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአፍሪካና በናይል ተፋሰስ ሀገራት ውስጥ የምታደርጋቸው ፕሮጀክቶች ካይሮ በአፍሪካ የነበራትን ተሰሚነትና ሚና ለመመለስ ላቀደችው ተግባራዊነት ዲፕሎማሲያዊ ምቹ ሁኔታዎች ይፈጥራሉ። በቀጥታ ጣልቃ መግባት ከባድ ቢሆንም ነገር ግን፣ ቤተ ክርስቲያኗ የምትፈጥረው ሕዝባዊ የሀገራቱ ሕዝቦች የግብፅን አቋም እንዲደግፉ ሊያደርጋቸው ይችላል፤›› ብለዋል።

ጳጳሱ አክለውም “2015 ላይ ኢትዮጵያን በጎበኘሁበት ወቅት አቀባበሉም ሆነ የሰጡኝ ቦታ ሊገለጽ የማይችል ነበር። እስክንድርያ እናታችን ናት፣ የግብፅ ፓትሪያርክ ደግሞ አባታችን ናቸው” የሚል አገላለጽ ሲጠቀሙ አድምጫለሁ። ነገር ግን የቤተ ክርስቲያኒቱ ተጽእኖ እንደቀድሞው ሊሆንልን አይችልም። በኢትዮጵያ እና በአካባቢው አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ከ 1959 ጀምሮ ፓትርያርኮቹ በአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች ናቸው። የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በተመሳሳይ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። እናም በዚህ ውስጥ ምን ሊኖር እንደሚችል አስቡት” ሲሉ ገለፃ አደረጉ።

በዛሬው ዕለት ደግሞ የግብፁ ጋዜጣ አል አሕራም ህወሃት እስልምናን ከአረቡ አለም ድጋፍ መሰብሰቢያ ለማድረግ ማሰቡን በይፋ አስነብቧል። አህራም እንዳሰፈረው “የትግራይ አማፂያን ዐረብኛ ቋንቋን በመጠቀም ክልሉ ከእስልምና ያለውን ታሪክ የተመለከቱ መረጃዎችን በማሰራጨት ከኢትዮጵያ መንግስት ለሚያካሂዱት ጦርነት የሙስሊሙን አለም አጋርነት ለማግኘት አቅደው ተነስተዋል” ሲል ዘግቧል።

የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ 115 ሚሊዮን ህዝብ አንፃር ጥቂቶችና ስድስት በመቶ መሆናቸውን የጠቀሰው አህራም
ህወሃቶች የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀምን ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው ሲል ፅፏል። የኢትዮጵያ መንግስት ኃይሎች ጋር ለሚደረገው ውጊያም የትግራይ ሙስሊሞች የሆኑ የህወሃት ደጋፊዎች ከተቀረው የኢትዮጵያም ሆነ የሌላው አገር ሙስሊሞች ድጋፍ እንደሚያገኙ ተስፋ አላቸው ነው ያለው።
የህወሃት የዲጂታል ሰራዊት በአረብኛ ሲጽፉ ክልሉ የመጀመሪያዎቹን እስላማዊ ስደተኞች የተቀበለ መሆኑን ለአረቡ አለም ለማስረዳት ጥረት ያደርጋሉ ብሏል።

በአረብኛ የሚፅፉበት “ትግራይ in Arabic” የተባለ የትዊተር አካውንት በወራት ውስጥ ከ40,000 በላይ ተከታዮችን ሰብስቧል ያለው የአህራም ዘገባ ሲሆን አካውንቱ በዛሬው ዕለት 34 ሺ ተከታዮች ነው ያለው። ከአካውንቱ ጋር ከፍተኛ መስተጋብር በመፍጠር ገፁ ላይ የተዘረዘሩት ግብፃዊ አረቦች መሆናቸውንም መመልከት ይቻላል።
የትግራይ ተወላጆች ይህንን ታሪክ ተጠቅመው በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚገኙ 300 ሚሊዮን የሚገመቱ አረቦችን ለመድረስ እየሞከሩ ነው።” አህራም እንዳለው።

የእስልምና እና ክርስትና ምዕመናን ወቅቱንና ካይሮን መጠንቀቃቸው አገራቸውን ብቻ ሳይሆን እምነቶቻቸውንም ለመጠበቅ ያስችላቸዋል። የሁለገብ ችግሮቻችን መነሻዋ ግብፅ እነሆ አሁንም ጉድጓድ ትቆፍራለች፤ ይህ በቤተ እምነት ውስጥ የጀመረችው ደግሞ አሁናዊ መልኩ ሆኗል።
ካይሮ እና ህወሃት በስመ-እስልምናም ሆነ በስመ-ክርስትና የሚሞካክሩት ርኩስ-ጥምረት የሁለቱንም ፀረ-ሀይማኖትነት ድጋሚ ከማረጋገጥ ያለፈ ዋጋ እንዳይኖረው ማድረግ የሚቻል ሀቅ ነው። በእጃችን ያለውን የመፍትሄ ቁልፍ እስከተጠቀምንበት ድረስ ማለቴ ነው።
ሁለቱም የመስጂዶችና የቤተክርስትያናት ጠላት ሆነው እያለ፤ ነገር ግን ለአመታት ቤተ-እምነቶቹን ስለ ፖለቲካ ነግደውባቸዋል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ቀድመን ከነቃን፣ ነቅተንም በሚበጀን ጉዳይ ላይ ህብረት ከፈጠርን ካይሮና ህወሃት ፈጥነው ከከሳሪዎች ጎራ ሲገቡ የምናይ ህዝቦች እንሆናለን።

Esleman Abay

References

https://www.al-monitor.com/originals/2021/10/egypt-strengthens-influence-africa-through-church

https://english.ahram.org.eg/News/454303.aspx

https://www.google.com/amp/s/www.thejakartapost.com/amp/paper/2021/12/29/ethiopias-tigray-taps-muslim-past-in-propaganda-push.html

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories