የካይሮ ትልቅ “ዜሮ” – ሱዳናዊ የህዳሴው ግድብ ተደራዳሪ


የዓባይ፡ልጅ

ሱዳናዊው በገለፁት ድምዳሜ ልጀምር። ዶ/ር አህመድ አል-ሙፍቲ ሱዳናዊ አለም አቀፍ የውሃ ምሁር ናቸው። ስለ ህዳሴ ግድቡ እና በሱዳንና ግብፅ የጋራ አቋም ዙሪያ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ “ግብፅ ከህዳሴ ግድቡ ድርድር እስካሁን ያገኘችው ትልቅ የሆነ ዜሮ ብቻ ነው።” ይላሉ። “አሜሪካና አውሮፓ ህብረት ሳይቀር የተለያዩ የውጭ ፓርቲዎች የገቡበት የግብፅና ሱዳን የድርድር ጥረት ያተረፈው ነገር ቢኖር ትልቅ ዜሮ ብቻ” ሲሉ ድምዳሜያቸውን ሰጥተዋል ምሁሩ።
“ግብፅ እና ሱዳን የናይል ውሃ መብታቸውን ለኢትዮጵያ የሰጡት በራሳቸው እጅ ነው።” የሚሉት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር የቀድሞ የሱዳን ተደራዳሪ ዶክተር አህመድ አልሙፍቲ ይህን ያሉት የአረብኛ ጋዜጣ ከሆነው አል-ኢስቲቅላል ጋር የዛሬ ወር ላይ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። እንደሳቸው አባባል “ግብፅ እና ሱዳን በአለም አቀፍ ህግ የተሰጣቸውን ነባር የናይል ውሃ ባለቤትነት ችላ ብለው ከ2011 ወዲህ የናይል ውሃቸውን አሳልፈው የሰጡት ራሳቸው ተስማምተው ነው።” ማለታቸው ተፅፏል።

አል-ሙፍቲ አክለውም “ኢትዮጵያ በግብፅ የነበረውን የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲሁም በካርቱም የታጠቁ ሀይሎች እንቅስቃሴዎች የፈጠሩትን ቀውስ ተጠቅማ ሁለቱ ሀገራት ንብረታቸው በሆነው የናይል ውሃ ላይ ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመለሱ አድርጋቸዋለች።
“ግብፅ እና ሱዳን በናይል ውሃ ላይ ያላቸውን ታሪካዊ ድርሻ ለማስጠበቅ ከፈለጉ ወደ ድርድር ጠረጴዛው መመለስ የለባቸውም” ሲሉም ለአል-ኢስቲቅላል አስረድተዋል። ወደ ድርድር መመለስ ያለባቸው ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነት ከፈረመች እና ሁሉንም የግንባታ እንቅስቃሴዋን ካቆመች ብቻ ነው።”
ጋዜጣው “በኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት በግድቡ ግንባታ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ ምንድነው?” ሲል ጠየቃቸው።
▪️ዶክተር አልሙፍቲ ሲመልሱ “በአብይ መንግስትና በህወሃት መካከል ጦርነትና ፍጥጫው በበረታበት ወቅት እንዲሁም ግጭቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ወቅት እንኳን የህዳሴ ግድቡ ግንባታ እንደቀጠለ ነበር። ለማጠናቀቅም ስራዋን አላቆመችም።” ሲሉ መለሱ።

“ትልቁ ዜሮ”
አል-ኢስቲቅላል “ካርቱም እና ካይሮ አዲስ አበባን ግራ በማጋባት የግድቡን ስራ ለማደናቀፍ ባደረጉት ጥረት ለምን አልተሳካላቸውም?
▪️ዶክተር አልሙፍቲ “ሱዳንና ግብፅ መፍጠር ከቻሉት ጫና ሁሉ በላይ የኢትዮጵያውያን ቁርጠኝነት የበለጠ ጠንካራ እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። ካይሮና ካርቱም አዲስ አበባን ለማደናቀፍም ሆነ ለማዘናጋት ያደሩጉት ጥረት ግድቡን ስራ ከመጀመር አላቆመውም። ኢትዮጵያ በተፋጠነ ሁኔታ ወደ ማጠናቀቁ ተቃርባለች።”

የህዳሴ ግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ ካርቱም እና ካይሮ ከውሃ ችግር ጋር ይጋፈጣሉ ማለት ነው?
▪️ዶክተር አልሙፍቲ “ካይሮ እና ካርቱም የባህር ውሃ የማጣራት፣ ፍሳሽ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል እና የመሳሰሉ መፍትሄዎችን ተጠቅመው ችግሩን ያቃልላሉ ይሆናል። ነገር ግን አይፈቱትም። አማራጫቸው ከኢትዮጵያ ውሃ መግዛት ብቻ ይሆናል። ሌላ ምንም መንገድ የላቸውም። ምክንያቱም ግድቡ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ትልቅ የውሃ ቦምብ ባለቤት ስለምትሆን።”

ኢስቲቅላል ጋዜጣ “በግብፅና በሱዳን መካከል በሀላይብ እና ሸላጢን መሬቶች ያለው የድንበር ግጭት በህዳሴ ግድቡ ጉዳይ ላይ ያለው አንድምታስ?
▪️ሱዳናዊው ዶ/ር አልሙፍቲ “የሃላይብ መሬት ጉዳይ ከህዳሴው ግድብ ድርድር ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ይህንንም ሱዳን ከ 1950ዎቹ ጀምራ በጥበብ ስትመራበት የሚገኝ ጉዳይ ነው።”

ኢስቲቅላል “ግብፅና ሱዳን የናይል ውሃ ታሪካዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ የተባበረ ግንባር መፍጠር አንድ መሆን ይኖርባቸው ይሆን?
▪️”አሁንም የሚፈለገው ካይሮና ካርቱም ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ ላይ የተባበረና ጠንካራ ግንባር መፍጠር ነው። ውሃን በተመለከተ የሚኖራቸው እጣ ፈንታ የተሳሰረ ነው። ያኔ በኢንቴቤ ድርድር ላይ ሁሉ የሁለቱ አቋም አንድ ነበር።”

ኢስቲቅላል ጋዜጣ “ካይሮ እና ካርቱም በአባይ ውሃ ውስጥ ታሪካዊ ድርሻቸውን እንዲጠብቁ ምን ዕድሎች አሏቸው?”
▪️ዶ/ር አልሙፍቲ “ግብፅ እና ሱዳን በናይል ውሃ ላይ ታሪካዊ ድርሻቸውን ማስጠበቅ ከፈለጉ ወደ ድርድር ጠረጴዛው መመለስ የለባቸውም። አስገዳጅ ስምምነት ላይ እስኪደረስ እና ኢትዮጵያ ሁሉንም የግንባታ እንቅስቃሴዋን ካላቆመች በስተቀር።

🔹ኢትዮጵያዊያንም ይላሉ፣ “የካይሮ ትልቁ ዜሮ የመጣው ላለመስማማት ወስና የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ይከበሩልኝ ከሚለው ዜሮ አቋሟ ጋር ተባዝቶ ነው። ውጤቱ የዜሮ ስሌት የሆነው።
Esleman Abay #የዓባይልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories