የካይሮ አዲስ ሸለምጥማጣዊ ጉዞ በግድቡ ዙሪያ

satellite image of GERD

በህዳሴ ግድቡ ደህንነት ላይ የውሃው ዘርፍ ምሁራንና የአሜሪካውን የጥናት ተቋም ጨምሮ አለማቀፍ አካላትን ያካተተ ጥናት አካሂጃለሁ እያለች ትገኛለች፤ ግብፅ።

የግብፁ አልሹሩቅ የወሬ ምንጭ፣ በዘርፉ የምሁራን ቡድን የተዘጋጀ በማለት ባስነበበው ፅሁፉ ጥናቱን ያደረጉት የግብፅ ውሃ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር፣ ዶር መሐመድ አብደል አቲ፣ በአሜሪካ በሻምፓኝ ዩኒቨርሲቲ የሪሞት ሴንሲንግ እና የስርዓተ ምድር ሳይንስ ፕሮፌሰር እና በመስኖ ሚኒስቴር የዓባይ ጥበቃ ክፍሉ አምር ፋውዚ መሆናቸውን ጠቅሷል።

ጥናታዊ ሪፖርት ነው ሲል በቀረው ሐተታ ላይ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ከተውጣጡ 4 ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በራዳር ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከታህሳስ 2016 እስከ ሐምሌ 2021 ድረስ 109 ምልከታዎች ተደርገው ተንትነዋል የሚለው ይገኝበታል።

Al sisi

የኢትዮጵያዊያን ዲጂታል ትግል ትኩረት ፀረ #TPLF ዘመቻ ላይ መሆኑ ለካይሮ መልካም አጋጣሚን የፈጠራላት ነው የሚመስለው። ግብፅ የግድቡን አጀንዳ ቀጣናዊ የደህንነት ጉዳይ እንዲሁም አረባዊ ገፅታ አላብሰው አለም አቀፋዊ ይዞታ ለመስጠት ስለማቀዳቸው ከሰሞነኛ ተግባሮቻቸው መታዘብ ይቻላል።
ለምሳሌ ያህል የዓረብ ሊግ የሊግ ዋና ፀሐፊው ግብፃዊ “በህዳሴ ግድቡ የግምባታ ሂደት እስራኤልና ኢትዮጵያ በትብብር እየሰሩ ነው” የሚለው ሰሞንኛ ንግግሩ ናይልን አረባዊ ገፅታ በማላበስ ለዘመናት ሲገለገሉበት የቆየውን ትርክት መልሰው ለማንሳት እየሞከሩ መሆናቸውን ይጠቁማል።

የግብፁ መስኖ ሚንስቴር ሞሐመድ አብደል-አቲ በበኩላቸው “ኢትዮጵያ በግድቡ ጉዳይ ስምምነት ለማድረግ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የላትም። ስለ ሙሊቱም የተሳሳተ መረጃ ነው እያደረሰችን ያለው። አስገዳጅ ውል ካልፈረመች ለሚፈጠሩ ችግሮች ሃላፊነት ትወስዳለች” ሲሉ ነው በቴሌቪዥን ቀርበው ማብራሪያ የሰጡት።

ፕሬዝደንት አል-ሲሲ አማርኛን ጨምሮ በ 20 ቋንቋዎች አስር ያህል የራዲዮ ጣቢያዎች በመክፈት የራዲዮ ዲፕሎማሲና ፀረ-ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳን በስፋት ለማከናወን ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው የተሰማውም በዚሁ ሳምንት ነው።

የግብፅ ብዙሃን መገናኛዎች ከትላንትናው ዕለት ጀምረው ( ዓርብ መስከረም 24 እኤአ)፣ አጀንዳ ማድረግ የጀመሩት ጉዳይ ደግሞ “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኗል” የሚለው ጥናት-ወለድ ዘገባ ነው።

በግድቡ መዋቅራዊ ክፍል ላይ ሊከሰት የሚችለው ተፅዕኖ በበቂ ሁኔታ ሳይታወቅ የግድቡ ሙሌት በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የገለፀው ይኸው ሪፖረት ሙሌቱ በተያዘለት መርሃግብር ከቀጠለ የናይል ተፋሰስን የውሃ ይዞታና ፍሰት ሃይድሮሎጂ ብቻ ሳይሆን፤ አደጋው በተለይም በሱዳን 20 ሚሊዮን ዜጎች ላይ ትልቅ አደጋ ደቅኗልም ብለዋል።

በአሜሪካ የሪሞት ሴንሲንግና ስርዓተ ምድር ሳይንስ ፕሮፌሰር ዶር ሂሻም አል-አስካሪ በጥናቱ ግምባር ቀደም ተመራማሪ ስለመሆናቸው ያስነበበው ፅሁፉ በሁለቱ የግድቡ ዘርፎች ያለው መዋቅራዊ ሚዛን አስተማማኝነት ጎድሎት ተመልክተናል ብሏል።

የርቀት ዳሰሳ ሳይንስ ፕሮፌሰሩ አል-አስካሪ “ጉዳዩ አደገኛ ነው እና “ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም” ስለማለታቸውም ሰፍሯል።
ጥናታዊ ግኝት ነው ያሉት ሪፖርት ሙሌቱ ምን ያህል ደረጃ ላይ ሲደርስ ጉዳት ሊያመጣ እንደሚችል በገለፀበት ሐተታው ግድቡ ከ 25 እስከ 30 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ይዞታ ላይ በሚደርስበት ጊዜ “ችግሮች” መከሰት ይጀምራሉ ነው ያለው። በዚህ ረገድም ሱዳን ዜጎቿን ከአደጋ እንድትጠብቅ ለማድረግ ምክረ ሀሳብ የምናቀርብላቸው ይሆናልም ብለዋል።

ፕሮፌሰር አልአስካሪ ግድቡ ቢፈርስ የጣሊያን ኩባንያ ሳሊኒ የሚጠብቀውን ሕጋዊ ኃላፊነት እስከ ምን ድረስ እንደሆነ የማሳሰብ ተግባርም ስለመኖሩ ከካይሮ ሰዎች ድርሳን ላይ ሰፍሮ ይገኛል።
Esleman Abay የዓባይ ልጅ

ተጨማሪ ከዚህ ሊንክ ያግኙ ➷
https://eslemanabay.com/?p=1742&amp=1

#GERD #Ethiopia

Sudan #Egypt

የዓባይልጅ #eslemanabay

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories