
ግብፅ፦ በአፍሪካዊ ወጣቶችና ጋዜጠኞች የኢትዮጵያን ጉዳይ የማራገብ አህጉር-አቀፍ ዘመቻ
የዓባይልጅ ✍️ እስሌማን ዓባይ
ግብፅ ለዲጂታል ፕሮፓጋንዳ አላማ በተፋሰሱ ሀገራት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚሰራጩ የራዲዮ ጣቢያዎች የመክፈት ስራዎችን ባሳለፍነው አመት መጀመሯን የምናስታውሰው ነው። በዚህ አመት ከወሰደችው ርምጃ ውስጥ ዋነኛ የሚባለው የሀገሪቱን የሚዲያ ጥናትና ስልጠና ኢንስቲትዩት በግብፅ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር ማድረግ ነበር። ይህን Center for Training and Media Studies በአዲሱ ተጠሪ ተቋም ስር ይሆን ዘንድ የአልሲሲ ትእዛዝ ሲሆን አቅጣጫውን በይፋ የሰጡት ደግሞ የግብፁ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፤ ጊዜውም በ 16/2 2022 እኤአ። ይህን ተከትሎም ግብፅ በአፍሪካ ትልቁ ነው የተባለውን አህጉራዊ የጋዜጠኝነት ስልጠና በነገው እለተ እሁድ ይፋ እንደምታደርግ ሰምተናል።
የግብፁ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ እና የግብፅ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊቀመንበር ካራም ጃብር ይከፍቱታል ተብሏል። በሚዲያ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የግብፅ አንገብጋቢ በተባሉ ጉዳዮች ዙሪያ አውደ ጥናቶች የሚካሄዱበት ነው። ሲደረጉ እንጂ በሽፍንፍን መግለጫቸው በውል ያልተጠቆሙ ድብቅ አጀንዳዎች እንደተጠበቁ ሆነው በሰማነው ደረጃ ራሱ በዋነኛነት “የግብፅ የናይል ጥቅምና አፍሪካዊ የዲፕሎማሲና የግጭት ትርክት” የሚሉ አጀንዳዎችን ጨምሮ ተከታዮቹ የተካተቱበት ይሆናል፦
▪️በካይሮ እና ካርቱም መካከል የጋራ የሚዲያና ፕሬስ ራዕይ መንደፍ
▪️ማህበራዊ ሚዲያ በመገናኛ ብዙሃን ላይ ስላለው ተፅእኖ
በማህበራዊ ሚዲያና መገናኛ ብዙሃን እንዴት መዋጋት እንደሚቻል
▪️ግብፅ በናይል ወንዝና በተፋሰስ ሀገራቱ ላይ የሚኖራትን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ጥቅም እንዴት ማስረፅ እንደሚቻል።
▪️አመጽ እና ግጭት ባለባቸው ቦታዎች ትርክትን እንዴት ማስኬድ እንደሚቻል የሚደረግ የውይይት መድረክ፣
▪️በአፍሪካ የውሃ ሃብቶችና የጎርፍ ስጋቶች ዙሪያ
▪️የዲጂታል ኃይሎች በአለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ እንዲሁም በብሔራዊ ደህንነት ላይ የሚኖራቸውን ሚና የተመለከተ ስልጠና
በዚህ የስልጠና መርሃግብር ሰልጣኞቹ ከበርካታ ግብፃዊና አለም አቀፍ ከሆኑ ባለሙያዎች፣ ምሁራንና የግብፅ ሚዲያ መሪዎች ጋር ይገናኛሉ። የጥንቷና የአሁኗ ግብፅ ሀውልቶች በርካታ ውይይቶችና ትምህርታዊ ብሎም የመዝናኛ ጉብኝቶችን የተካተቱበትም ነው። በአፍሪካ ደረጃ ትልቁ የተባለው ስልጠና መርሃ ግብር የሚከተለውን ይመስላል።
▪️የአፍሪካ ሚዲያ የሥልጠና The African media training program ከ 14/8/2022 እስከ 9/8/2022 ለሱዳን ለሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች ስፔሻላይዝድ የተደረጉ 10 የሥልጠና ኮርሶች ለ 4 ሳምንታት
▪️ለወጣት አፍሪካዊያን ለ (3 ሳምንታት) የሚሰጠው ስልጠና ከ9 ወይም 10 ጀምሮ እስከ 29/9/2022 ታቅዷል።
▪️በመቀጠልም ለእንግሊዘኛ ተናጋሪ አፍሪካዊ ብሮድካስተሮች መሰረታዊ ኮርስ ሲሆን ለ 4 ሳምንታት የሚቆይ ነው።
▪️በመቀጠልም ስፔሻላይዝድ የእንግሊዘኛ ኮርስ ከኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስልጠናዎች በተመረጡ ዘርፎች ይከተላል ይህም ከ6/11 እስከ 17/11/2022..።
▪️ለደቡብ ሱዳን ጋዜጠኞች በልዩ የተዘጋጀው ስልጠና ከ20/11 እስከ 15/12/2022 ለ4 ሳምንታት ይቀጥላል።
▪️ለፈረንሳይኛ ተናጋሪ አፍሪካውያን ጋዜጠኞች የመሠረታዊ የሥልጠና ኮርስ ተግባራት ከ12/25 እስከ 19/1/2023 የሚቆይ ሲሆን በመቀጠልም ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ ልዩ ኮርስ በተመረጠ ዘርፍ የመረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና ይሰጣል።
▪️ለአረብኛ ተናጋሪ አፍሪካዊ ጋዜጠኞች ለአንድ ወር የሚቆይ ስልጠና ከ5/2/2023 እስከ 2/3/2023
▪️የአረብኛ ስፔሻላይዝድ ስልጠና ከ5/3 ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ ይሆናል።
▪️የአፍሪካ የሚዲያ ስልጠና መርሃ ግብር ሲጠናቀቅ የወጣት አፍሪካውያን ጋዜጠኞች ስልጠና ለሳምንታት ከ6/5 እስከ 25/5/2023 የሚቆይ ይሆናል።
ይህ እንደ አፍሪካ የጀመረችው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ መነሻውም ሆነ መድረሻው የዓባይ ጉዳይ ነው። የህዳሴ ግድቡን ምንም ማድረግ ባትችልም ኢትዮጵያዊያኑን በመረጃ ጦርነት ማናከስና ማመሰቃቀል ግን ቀሪ አማራጯ የሆነ ይመስላል። ለዚህ ደግሞ በኢትዮጵያ ስር እየሰደዱ የሚታዩት የጥላቻ ንግግሮችና ግጭቶች አመቺ ሆኖላታል።
ይህ የካይሮ የፕሮፓጋንዳ ጦርነት እንደ ሀገር ሁሉንም ባለድርሻ ያቀናጀ አፋጣኝ ዝግጅት የሚጠይቀን ነው።
የዓባይልጅ
Source
https://eslemanabay.com/%d9%88%d8%b2%d9%8a%d8%b1-%d8%a7%d9%84%d8%ae%d8%a7%d8%b1%d8%ac%d9%8a%d8%a9-%d9%88%d8%b1%d8%a6%d9%8a%d8%b3-%d8%a7%d9%84%d8%a3%d8%b9%d9%84%d9%89-%d9%84%d9%84%d8%a5%d8%b9%d9%84%d8%a7%d9%85-%d9%8a%d8%b4/