የካይሮ የውክልና ጦርነት በድንበር ግጭት ውስጥ

egyptian proxy war on ethiopia

Esleman Abay

ኢጂፕሺያን ጋዜቲ የአረብ ሊግ ዋና ፀሐፊ የሆኑት ግብፃዊ ማህሙድ ሬይድ የሊጉ አባል አገራት ለሶማሊያ ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ዘገበ። በየካቲት 1978 ደግሞ ፕሬዘዳንት አንዋር ሳዳት ሶማሊያ ኢትዮጵያን መውረሯን ተከትሎ ለሶማሊያ ድጋፍ እያደረገች መሆኗን በይፋ ገለፁ

ብፅ በኢትዮጵያ የድንበር ግጭቶች ላይ በውክልና ጦርነት ደጋግማ ተሳትፋለች። በኢትዮ ሶማሊያ ግጭቶች ውስጥ የነበራት ተሳትፎ አይነተኛ ማሳያ ነው። በ 1960 እና 64 ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር በነበረው ግጭት ውስጥ ካይሮ እጇን ለመክተት አልዘገየችም። በወቅቱ ሶማሊያ ከሶቬት የነበራት ግንኙነት ተቋርጦ ነበር። ሶማሊያ ወረራ እንደጀመረችም ግብፅ ከእስራኤል ለምታደርገው ውጊያ ከሩሲያ ካስገባቻቸው የጦር መሳሪያዎች መካከል ከፍተኛ መጠን ያለውን በይፋ ለሶማሊያ ሰጥታለች።

“ታላቋ ሶማሊያን እመሰርታለሁ” በሚል አላማ የሞቃዲሾ መንግስት ሐምሌ 23 1977 ላይ መደበኛ የጦር ሃይሉንና አየር ሃይሉን አቀናጅቶ መጠነ ሰፊ ዘመቻ በአገራችን ላይ ጀመረ። የሞቃዲሾ ስሌት የነበረው ጦርነት በ 1977 የሚፈነዳ ከሆነ የኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግሮች ጥሩ አጋጣሚ ናቸውና ሶማሊያም አጋጣሚውን ተጠቅማ ድል ታደርጋለች። በዚህም አንድ አምስተኛውን የኢትዮጵያ ክፍል በቁጥጥሯ ስር በማዋል “የታላቋ ሶማሊያ” ቅዠታዊ ህልም እውን ይሆናል የሚል ነበር።
ጥር 22 1978 ዓ.ም የግብፁ ኢጂፕሺያን ጋዜቲ የአረብ ሊግ ዋና ፀሐፊው ማህሙድ ሬይድ (ግብፃዊ) የሊጉ አባል አገራት ለሶማሊያ ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ዘግቧል።
በየካቲት 1978 ደግሞ የግብፁ ፕሬዘዳንት አንዋር ሳዳት የሶማሊያ ወረራን ተከትሎ በሚካሄደው ጦርነት ውስጥ ግብፅ ለሶማሊያ ድጋፍ እያደረገች መሆኗን በይፋ ገለፁ። ተጨማሪ ጦርና መሳሪያ እንደሚልክም አስታወቀ።
የኬኒያ ዜና አገልግሎት ያደረሰውን መረጃ ጠቅሶ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቲት 1978 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የግብፅ ቦይንግ 707 አይሮፕላን ከ 20 ቶን በላይ ፈንጂ እና የመድፍ ዛጎሎች ጭኖ ወደ ሶማሊያ ሲበር በኬኒያ አየር ሃይል ተገዶ በናይሮቢ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ እንዲያርፍ ተደርጓል።
በየካቲት 1978 ሳዳት ለአሜሪካ በላከው ደብዳቤ “አሜሪካ የጦር መሳሪያ ከወታደሮች ጋር ወደ ሶማሊያ እንድትልክ እፈልጋለሁ። ሶቬት በኢትዮጵያ የምታደርገው እንቅስቃሴ ወደ የላይኛው ዓባይ ወደሚፈስበት ወደ ሱዳን ሊስፋፋ ይችላል። ይህ ደግሞ ግብፅ ማለት ነው። ውሃ ለአገሬ ህዝብ ሕይወት ነው፤ እናም ይህን መስፋፋት ልከላከለው ይገባል” ሲሉ ጠይቀዋል። ካይሮ በሶማሌ ወረራ ጅማሮ ሰሞን ላይ ሶማሊያን የምትደግፈው እንደ አረብ አገር አጋር ለመሆን ነው በማለት የአረብ ሊግን ለማሳመን ሞክራ ነበር። ነገር ግን ምክንያቷ የዓባይ ውሃ ጉዳይ ስለመሆኑ የማታ ማታ በራሱ በሳዳት ደብዳቤ ይፋ ሆኗል።
በምላሹ ኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ ባወጣው ፅሑፍ ግብፅ ሶማሊያን መደገፏን ካላቆመች ኢትዮጵያ በዓባይ ፍሰት ላይ ጣልቃ ልትገባ እንደምትችል ሳዳትን እንደሚከተለው አስጠንቅቋል፦
(ሳዳት) ውኃ ለሕዝቡ ሕይወት በመሆኑ ምክንያት የዓባይ ተፋሰስን ለመጠበቅ የሚሞክር ከሆነ፣ ከዓባይ ምንጮች መካከል አንዱ የሚገኘው እርሱ (ሳዳት) ሊያጠፋት በሚፈልጋት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ መሆኑን በሚገባ ማወቅ አለበት። በግብፅ ገበሬዎች ዘንጅ በጣም ተወዳጅ የሆነው ጥቁር ደለል የሚሄደው ከዚሁ ነው። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ ለህዝቧ ህይወት የሚያስብ ርዕሰ ብሔር አላት።

ይሁንና ግብፅ እንደፈለገችው የኢትዮ ሶማሊያ ጦርነት ሶማሌ ከተመኘችው ተቃራኒ ሆነ። የተራዘመም ሳይሆን ቀረ። ምስጋና ለጀግናው ሰራዊታችን ይሁንና በመጋቢት 1978 ኢትዮጵያ ሁሉንም የኦጋዴን ወታደራዊ ሰፈሮችና የአስተዳደር ማዕከላትን ዳግም በቁጥጥሯ ስር አዋለች። ሶቬት፣ ኩባ እና ደቡብ የመን ኢትዮጵያን ደግፈዋል።
በዓባይ ፖለቲካ ውስጥ ካይሮ የሶማሊያን ካርድ ለመጫወት ያደረከችው ሙከራም ከቸፈ።

ካይሮ የድንበር ግጭት ውስጥ እጇን ለማስገባት አሁንም እየተንቀሳቀሰች መሆኑ አያጠራጥርም። በአልፋሻጋ እና ሌሎች የሱዳን አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ግጭቶች እየተከሰቱ ነው። ስለ ግጭቱ የአል ሲሲ አጋር የሆነው የሱዳን ጦር ነገሩን ለማጦዝ ይሞክራል። ዲፕሎማቲክ አቋም ያላቸው አብደላ ሀምዶክ ችግሩን ስለ መፍታትና ለኢትዮጵያ ወቅታዊ ቀውስ አጋርነታቸውን እየገለፁ ናቸው።

በኢትዮ ሱዳን ድንበር አካባቢ ሰርገው ለመግባት የሞከሩ ሃይሎች የግብፅ ይሁኑ አይሁኑ ማረጋገጥ ባይቻልም የተወሰኑ ነጭ ወታደሮችም ይገኙበታል የሚሉ መረጃዎች ተሰምተዋል።

ሸለምጥማጧ በድንበር ግጭት ካርድ ትላንት በኦጋዴን ሞክራ ከቸፈባት፤ አሁንም በሱዳን በኩል ለመጫወት እየሰረሰረች ነው።

አንድነት ለኢትዮጵያችን ድል መሠረት ነውና የውስጥ ችግሮችን በተለይም ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎችን መንግስት በትኩረትና በአፋጣኝ አስወግዶ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ ትልቁ የቤት ስራው ይሁን !

   የዓባይ  ልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories