የኬኒያ አበርክቶ በፀጥታው ምክር ቤት

kenyataabiy ahmed and uhuru

ተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የሚሰራበትን አንድ ደምብ አለ። በአጀንዳነት በተያዘ ጉዳይ ዙሪያ የመንግስታቱ አቋም ከመገለፁ በፊት በጉዳዩ ረቂቅ ዙሪያ ተከታታይ ምክክሮች ይደረጉበታል። የጉዳዩ ረቂቅ በምክክሩ የሚቀርቡ ሃሳቦችን ጠብቆ ማስተካከያ እየተደረገበት ገቢ መሆኑን ይቀጥላል።

ገቢ የሆነው ረቂቅ (በጣት የሚቆጠሩ) ቀናትን ይጠብቃል። በነዚህ ቀናት ውስጥ ከአባል አገራቱ ሀሳብ ካልቀረበበት ይፀድቃል ወይም የፀጥታው ምክር ቤቱ የጋራ አቋም ይሆናል። ቀነ ገደቡ ከመድረሱ በፊት ከአባል አገራት አንዱ ጥያቄ ካቀረበ ደግሞ ዝምታው ተሰበረ ይባልና እንደገና ይመከርበታል። ተሻሽሎ እንዲቀርብም ይደረጋል።

ቱኒዚያ የግብፅን ጉዳይ ለማስፈፀም ለፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችው ፕሮፖዛልል እስከ ወርሃ መስከረም ድረስ አራት ጊዜ ነበር እንዲሻሻል የሆነው። በዚህ የጊዜ ቆይታ መካከል ነበር ይፋዊ ጉባዔ ተደርጎ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ስር እንዲደረግ የተወሰነው። ይሁን እንጂ በድርድሩ ቀጣይ ሂደት የፀጥታ ምክር ቤቱ እጁ እንዲገባ ሴረኛ ይዘቶች በፕሮፖዛሉ ተሰግስገውበት ነበር።

➪የመጀመሪያው ረቂቅ የሰኔ 15ቱን የአረብ ሊግ አቋም ተከትሎ ገቢ ከተደረገ በኋላ እስከ ሐምሌ 16 እኤአ ድረስ በዝምታ ነበር የቀጠለው።
➪በ 16 ኬኒያ ዝምታውን ሰበረች
➪2ው ረቂቅ ተሻሽሎ በሐምሌ 17 እኤአ ቀረበ
➪በድጋሚ መስከረም 2 ላይ ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሻሎ እንዲቀርብ አሁንም ኬኒያ ዝምታውን ሰበረች
➪ይህም መስከረም 7 ላይ ገቢ ከሆነ በኋላ
አራተኛውና የመጨረሻው ረቂቅ ገቢ የሆነው በመስከረም 13 ነበር

በቱኒዚያው ፕሮፖዛል 4 ማሻሻያ ጥያቄዎች መሰረትም ተከታዮቹ ይዘቶች እንዲወገዱ ሆነዋል፦
➪ቀጣዩን የድርድር ውጤት በተመለከተ ዋና ጸሐፊው በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤቱ ሪፖርት እንዲያቀርብ የሚጠይቀው
➪ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነት አስቀድማ እንድትፈርም ለማስገደድ የቀረበው፣
➪ሶስቱ አገራት የሙሌቱ ወሩ ከመድረሱ በፊት ከአስገዳጅ ስምምነት እንዲደርሱ ራሱ ምክር ቤቱ በጠንካራ “ቋንቋ” የጠየቀበትና በዚህም እንደማትስማማ የሚታወቅ ሲሆን ተከትሎ ይመጣ የነበረው አቋም ያልተስማሙትን ሶስቱንም ሳይሆን ኢትዮጵያን ብቻ የሚበድል ነበር፤ እሱም ሙሌቱን መቃወም፤

በነዚህ ሂደቶች ውስጥ የኬኒያ ሚና ለራሷም ለአፍሪካም ሆነ ለኢትዮጵያ ጠቀሜታ ያለው ነበር
በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ከኬኒያ ጋር በሃይል በሌሎችም ዘርፎች ያደረግናቸው ስምምነቶች ወሳኞች ነበሩ። በኬኒያ በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሚናም ሊመሰገን የሚገባው ነው።

𝔸𝕤𝕒𝕟𝕥𝕖 𝕄𝕨𝕒𝕟𝕒 𝕨𝕒 𝕁𝕠𝕞𝕠 𝕂𝕖𝕟𝕪𝕒𝕥𝕥𝕒
 🅰🆂🅰🅽🆃🅴 🆄🅷🆄🆁🆄
      ᗩᔕᗩᑎTE ᑌᕼᑌᖇᑌ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

GERD

eslemanabay Meles Alem

የዓባይልጅ

Ethiopia Citizen TV Kenya Love Matters Kenya Ethiopian Embassy Nairobi

AsantekenyaUmojaWaAfrika

afrikamoja

Asante #UhurusLegacy

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories