የወዳጅ ሀገር የቀድሞ ሶቬት ፕሬዝደንት ሚካይል ጎርባቾቭ በ 91 አመታቸው አረፉ

▪️ጎርባቾቭን ስናስብ
ሚካሄል ጎርባቾቭ በ 1990 የሶቪዬት ህብረት መሪ ሆኑ፤ የሶቬት የመጨረሻ ፕሬዝደንትም እሳቸው ነበሩ። ጎርባቾቭ ወደ ስልጣን እንደያዙ በጀመሩት ሪፎርም በተለይም Glasnost እና perestroika የሚሉ ፖሊሲዎቻቸው ዝነኛ አድርጓቸዋል ይባላል፤ perestroika = reconstruction እና glasnost = openness)

ሶቭየት ህብረት ከአሜሪካ የነበራትን ግንኙነት የተሻለ ማድረግ ችለዋል ይባልላቸዋል። ጎርባቾቭ ከአሜሪካ አቻቸው ሮናልድ ሬገን ጋር የኒውክለር መሣሪያ የመቀነስ ስምምነት ማድረጋቸውም በሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ታሪክ ይታወሳል። በ 1979እኤአ ነበር ያለ ቅድመ ሁኔታ የኒዩክሌር ጦር መሣሪያ የሚከለክለውን ስምምነት ፈቅደው የተስማሙት። በዚህ የተደሰቱት ምዕራባዊያን አደነቋቸው፤ የኖቤል ሽልማታቸውንም በ1990 ለሳቸው አደረጉላቸው። እነ ታይም መፅሔት ደጋግመው ዘመሩላቸው። ይሁንና፦
የምእራባዊያኑ የገነገነ ሴረኝነት በጎርባቸው መልካም ዲፕሎማሲ ሊለዝብ አልቻለም ነበር። ኖቤሉን በተቀበሉ አመት ነበር ታላቋ ሶቪዬት መበታተን የጀመረችው።

▪️ጎርባቾቭ በፈረሰችዋ ሶቪየት ሕብረት (ከ1924-1985) ያለው የታሪክ ምእራፍ ዘመነ ስህተት ነበር ሲሉ በእድሜያቸው መጨረሻ አካባቢ ተናግረው ነበር። ጎርባቾቭ የባከኑ ያሏቸው 60 ዓመታት ታላቋ ሶቬት የመፍረሷ አሳዛኝ ዘመነ ቁልቁለት ሲሆን የብሔር እና የማንነት ፖለቲካ መጧጧፉ ከዋነኛ ሰበቦች ይጠቀሳል።
የብሔር ፖለቲካ ሲንሰራፋ ምእራባዊያን ይዘነጣጥሉህ ዘንድ መደላድል ተፈጠረ ማለት ነው..።
▪️ይህን ጠንቅቀው የተጓዙት ቪላዲሚር ቪላዲሚሮቪች ፑቲን ሀገራቸውን ወደ ከፍታ እየወሰዷት ይገኛል።

የዓባይልጅ ✍️ እስሌማን ዓባይ

?photo;
col. Mengistu Hailemariam with #Mikhail #Gorbachev 1988

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories