የዋሽንግተን ካርታና የድራጎኑ አፃፋ በኢትዮጵያ

US China on Africa

by, Esleman Abay

ሜሪካ ለሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሲፈፀም የነበረው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲያሳስባት አላየንም። የአሜሪካ የውጭ አጀንዳ ላይ ዋናውን ዋና አድርጎ አልሰራም በሚባለው የትራምፕ ዘመነ ስልጣንም በአገራችን በነበረው የተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ጥይት ሲዘንብባቸው የዋሽንግተን ቃል የነበረው “ዜጎች ተቃውሟቸውን ይግለፁ፤ አትከልክሏቸው” ከማለት አልተሻገረችም። ጥይትን እንደ ርችት የቆጠረ ቸልታ…። በዘመነ ባይደን ግን አዲስ ተረክ ተጀምሯል። “የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ያሳስበኛል” የሚል። መግፍኤው ሰብዓዊ መብቱ ስላሳሰባቸው ቢሆን ኖሮ ርህራሄያቸውን በባረክንላቸው። ነገሩ ወዲህ ነው – የቻይና ትኩሳት።

Biden should moult its beak and claw of us foreign policy

ባይደን ወደ ስልጣን ሲመጡ የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ አቅጣጫ አስያዙ። አንደኛን አንደኛ አደረጉ። በዓለም በግዝፈቱ ሁለተኛ ኢኮኖሚ ባለቤቷ ቻይና ጉዳያችን ናት አሉ። ቻይና በዚህ አካሄዷ በ 2028 የዓለማችን ቁጥር አንድ ኢኮኖሚ ባለቤት ያደርጋታል ተብሎለታል። ይህ የቻይና መፈርጠም ለፕሬዝዳንት ባይደን ዋነኛው የውጭ ፖሊሲ ተተኳሪ ነው እንዲሉ የግድ ብሏቸዋል። የቻይና በመላው አፍሪካ የፋይናንስና ፖለቲካ ተፅእኖ በፍጥነት መስፋት፣ አፍሪካዊ አገራት ለቤጂንግ ወዳጅነት በራቸውን በሰፊው መክፈታቸው ባይደን ለቻይና መመከቻ ከመረጧቸው ቀጣናዎች ውስጥ አህጉራችን ትሆን ዘንድ መንስኤ ሆኗል።

Dragon eagle symbolism

ወደ አገራችን ስንመጣም ቻይና በ 2020 ከፍተኛውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ስለመያዟ ተ.መ.ድ በሪፖርቱ ገልጿል። ቤይጂንግ 2019 ላይ ካፀደቀቻቸው የውጭ ፕሮጀክቶች ውስጥ 60 በመቶው በኢትዮጵያ ስለመሆኑም አብሮ ተዘግቧል፡፡ ቻይና በአፍሪካ ያሳረፈችውን መዳፍ ለመፈልቀቅ አፍሪካ እንደ አህጉር ኢትዮጵያም እንደ አገር በአሜሪካ የፖሊሲ መነፅር ውስጥ ናቸው ማለት ነው። የሰሞኑ የትግራይ ጉዳይ ደግሞ እንደ ካርታ ስለመመዘዙ ማሳያዎች እየታዩ ናቸው። ለካርታው ምላሽ ለመስጠት የቤይጂንግን ፍጥነት ስናይ ደግሞ የጨዋታውን ተጨባጭነት ያስረግጥልናል።

eagke dragon

የትግራይን ጉዳይ አስታከው የአሜሪካው ብሌንከን “ወደ ትግራይ ያልተገደበ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲደርስ ለጠ.ሚ ዐብይ ነግሬያቸዋለሁ” የሚል ትዕዛዝ መሰል መግለጫ የሰጡት በየካቲት 2021 ነው።
የባይደን ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን በመቀሌ ዙሪያ በተደረገው ውጊያ ሊከሰቱ የሚችሉ የጦር ወንጀሎችን ጨምሮ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰው በተመለከተ መስጋታቸውን መግለፃቸውም ይታወሳል። አሜሪካ በትራምፕ ዘመን ለኢትዮጵያ እንዲዘገይ ያገደችው ገንዘብ ከግድቡ ጋር እንደማይያያዝና ይልቁንም ከሰብዓዊ አያያዝ ጋር ሊሆን ይችላል የሚል መግለጫ መስጠታቸው የምናስታውሰው ነው። ታዲያ የቻይና የመልስ መግለጫ ፈጣን የነበረ ሲሆን በቀጣዩ ቀን ቤጂንግ በትግራይ ጉዳይ አፃፋዊ ድምጿን አሰምታለች፤ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌቢን በመግለጫቸው “በክልሉ መረጋጋት እንዲመጣ እና ለሚያስፈልገው የሰብዓዊ ድጋፍ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ ማድረግ አለበት፡፡ ቻይናም የምግብ ግብዓቶችን በአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ መልክ ለኢትዮጵያ ታቀርባለች” ነበር ያሉት። ከዚህ የሰብአዊ ድጋፍ ባሻገርም ለየትኛውም የዋሽንግተን ካርታ ምላሽ ከመስጠት ወደ ኋላ የማትል መሆኗንም ጠቁማለች። የቃል አቀባዩ ዋንግ “የኢትዮጵያ መንግስት ችግር የገጠመውን የህብረተሰብ ክፍል ለማቋቋም የሚያደርገውን ጥረት ቻይና ሙሉ በሙሉ መደገፈቀን ትቀጥላለች” የምትለዋ ንግግር ለአሜሪካ ውስጠ ወይራ ቅኔ ናት።

በመቀጠልም በፀጥታው ምክር ቤት በግድቡ ጉዳይና በትግራይ ቀውስ ዙሪያ በተደረጉ ጉባዔዎች ለኢትዮጵያ ድጋፏን ገልፃለች። በትላንትናው ዕለትም የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛዎ ሊያን የባይደን አስተዳደር ስለ ኢትዮጵያ ያፀደቀውን የማዕቀብ ጉዞ አገራቸው እንደምትቃወም በትዊተር ገዳቸው ይፋ አድርገዋል።

Zhawo lijian spokesperson of mofa china

https://twitter.com/zlj517/status/1440681744651325442?s=19

አሜሪካ ከዚህ ቀደም የምትታወቅበት ትልቅ ዱላና ቲኒሽ ካሮት የያዘ የውጪ ፖሊሲዋ እንደወትሮ በቀላሉ የሚሰምርላት አይመስልም ነው እየተባለ የሚገኘው። በጉዳዩ ላይ የቻይና ፍላጎት አብሮ ሲገኝ መሆኑ ነው። በትግራይ ጉዳይ የተንፀባረቀውም ይኸው ይመስላል። አገራችን ከንስሩም ከድራጎኑም ጋር የተቀመረ አካሄድ መከተሏ ይበልጥ አዋጭ እንደሚያደርግ ይመከራል። የምስራቁ ድራጎን ንስሩን መፈናፈኛ ማሳጣት የሚችልበት እድል አለው መባሉ ዋሽንግተን በአገራችን ጉዳይ የሚኖራትን ግብታዊ ጣልቃ ገብነት ያለዝባል የሚለውን አሳቤ ይፈጥራል።

Dragon eagle

ንሥሩና ድራጎኑ በአፍሪካ ሳር ላይ ሲፋለሙ በአፍሪካ ሳር ውስጥ የተኛው ጥቁር አንበሳ ድል የሚጨብጥበት ዕድል መኖሩን ብዙዎች ይገልፃሉ። ይሁንና የውጪ ፖሊሲ ቀመራችን የላቀ እንቅስቃሴ የሚጠይቅበት ወቅት መሆኑን ታሳቢ ማድረግ ነው ቁልፍ ነጥባችን።

 ~ የዓባይ ልጅ Esleman Abay ~

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories