የውሃ ጥም ጂኦፖለቲካ | የሳዑዲ የማያዛልቅ ጎዳና

የዓባይ ፡ ልጅ ✍️ እስሌማን ዓባይ

በቀጣዮቹ ሃያ አመታት ውስጥ ለመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ መንስኤ የሚሆነው ጦርነት ወይም ሽብርተኝነት እንዳይመስላችሁ” ይላል Jon B. Alterman ከ 10 አመት በፊት ይፋ ያደረጉት ጥናታቸው። “Clear Gold” በሚል ርዕሳቸው የውሃን ቀጣይ ውድነት በሚጠቁም ጥናታቸው አልተርማን “የመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂያዊ ከባድ ካርድ በመሆን ለፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ ዋነኛ መነሾ የሚሆነው ውሃ እና የውሃ እጥረት ነው” ነበር ያሉት።

የሳዑዲ ውሃ ጥም
በአንድ ወቅት 500 ቢሊዮን ሜኪዩብ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችት የነበራት ሳዑዲ አረቢያ 98 በመቶ የውሃ አቅርቦቷን ከዚሁ የውሃ ሐብቷ ነበር የምታገኘው። የዜጎቿ ዕለታዊ የውሃ ፍጆታ ከአውሮፓ ስታንዳርድ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን፤ በዛ ላይ ደግሞ በ 1980ዎቹ ጀምሮ አገሪቱን የሩዝና የእርሻ ደሴት ለማድረግ የተጀመሩ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች የከርሰ ምድር ውሃዋን አሟጠጠውና ከባድ አደጋ ተደቀነባት።

ይህን ተከትሎም 2015 ላይ 80 በመቶው የሳዑዲ የከርሰ ምድር ውሃ ማለቁን ጥናቶች አረጋገጡ። ናሽናል ጂኦግራፊ ጭምር ይህንኑ ጥናታዊ ሪፖርት መዘገቡ ይታወሳል።
ይባስ ብሎም የሳዑዲው ኪንግ ፈይሰል ዩኒቨርሲቲ በ 2016 ያወጣው ሪፖርት የሳዑዲ የከርሰ ምድር ውሃ በ 13 አመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚያልቅ ደምድሟል። ይኸውም በ 2020ዎቹ መሆኑ ነው።

የገጠማትን የውሃ ቀውስ ለመቅረፍ በተለያዩ አገራት ከገዛችው ውሃ ገብ የእርሻ መሬት በተጨማሪ የባህር ውሃን ለማጣራትም ሰፊ ርብርብ ማድረግ ከጀመረች ሰነባብታለች። ጨዋማ የባህር ውሃን አጣርታ ለመጠቀምም በዬአመቱ 3 ቢሊዮን ዶላር እያወጣች ነው የምትገኘው። በአለማችን ከሚደረገው የባህር ውሃ የማጣራት ስራ ግማሹን መጠን የሚሸፍነው የሳዑዲ ዲሳሊኔሽን ነው።

ተከዜን በፖርት ሱዳን ወደ ሪያድ የማሻገር ህልም

የናይል ዋነኛ ገባሮች የሆነውን የተከዜ-አትባራ ወንዝ በመጥለፍ ወደ ሪያድ-ሳዑዲ አረቢያ በቀይ ባህር በኩል ለማሻገር አቅደው ነበር። ዕቅዱ የታሰበው በሳዑዲ ምኞትና በግብፅ ማን አለብኝነት ነበር። ጊዜው ደግሞ የ 1980ዎቹ መጨረሻ። ዳንኤል ክንዴ የተባሉ ምሁር በ 1999 እኤአ ባወጡት ፅሁፋቸውም እንደሚከተለው አስቀምጠውታል።

▮…በሰዓት 4.5 ሚሊዮን ሊትር የሚሆን ውሃ ከአትባራ (ተከዜ) በመጥለፍ ወደ ቀይ ባህሯ የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ከዚያም ወደ ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ በቀይ ባህር በኩል ለማሻገር በግብጽ ሙሉ ድጋፍ የ2 ቢሊዮን ዶላር ስራ በአርቃቂዎች ተጀምሮ ነበር፡፡ እንደ እቅዱ ከሆነ ሱዳን በሁለት መልኩ የምትጠቀም ሲሆን አንድም ከአትባራ (ተከዜ) በስተምስራቅ የሚገኘውን ጠፍ መሬት ለማልማት የሚያስችላት ሲሆን እንዲሁም በቀይ ባህር ዳርቻ ያሉ ፏፏቴዎችን በመጠቀም በሰዓት ከ7000 ኪሎዋት በላይ ኤሌክትሪክ ለማምረት ያስችላታል፡፡ ሳዑዲዎቹም ግብፅን እና ሱዳንን (በዚህ ፕሮጀክት ምክንያት) ለሚያጡት የመስኖ ውሃ በግብርና ካፒታል ኢንቨስትመንት እና በኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ያካክሱታል…▮

ይህ ህልም ታዲያ ኢትዮጵያ ተከዜ ወንዝ ላይ የገነባችው ግድብ ህልም ሆኗል። ደግመው እንሞክር ቢሉም ማብሪያ ማጥፊያው ከተከዜው ግድብ ነውና።

ታዲያ እነ ሳዑዲ ይህን ወይም ይህን መሰል ፕሮጀክት አሁንም አያስቡም አይባልም፡፡ ዕድል እየተጠባበቁ ቢሆን እኝጂ። ሳዑዲ ትልቁ ስጋቷ ውሃ ጥም ነው። ከነዳጅም ከወርቅም በላይ ውሃ ትሻለች።

በግዛቷ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በማሰቃየት የጀመረችው ሩጫም የውሃ ጥሟን ለማርካት መሆኑ በግልባጩም ቢሆን ሐቅ ነው። ሪያድ የጀመረችውን ሴራ ትታ ወደ ትብብር ብትመለስ ከኢትዮጵያ ጥቅሟን እንጀምታሳካ ማን በመከራት። ሳዑዲ የማታ ማታ ስትለማመጠን መገኘቷ ለማይቀረው ካሁኑ የብርሃኑን መንገድ ብትመርጥ ያዋጣታል።
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች


Esleman Abay የዓባይ ልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories