የዓለም አቀፍ ርዳታ ጥቋቁር ምዕራፎች

      የዓባይ፡ልጅ✍️እስሌማን፡ዓባይ

በካሪቢያን ኃይቅ የምትገኘው ደሴታዊት ሀገር ሐይቲ ከአስር አመት በፊት የደረሰባት ሱናሚ 200,000 ዜጎቿን ህይወት ተቀጠፈ። የአደጋው አሳዛኝ ፎቶዎች በመላው ዓለም ሲሰራጩ ለርዳታና ለመልሶ ግንባታ ተከታታይ የርዳታ ቃሎች ይደመጡ ቀጠለ። ዩናይትድ ስቴትስ ብቻ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ለመለገስ መወሰኗን አስታወቀች፣ ይሁን እንጂ የዚህ ገንዘብ ሽራፊ ብቻ ነበር ሄይቲ የደረሰችው።

የዳሰሳ ጥናት ውጤቶች እንደሳዩት በወቅቱ ሐይቲ የሚገኙ በጎ አድራጊዎች እጅ የገባው ገንዘብ ተከፈለ ከተባለው ርዳታ 0.9 በመቶው ብቻ ነበር።
የቀረው ገንዘብ የት ገባ?
ገንዘቡ ከዚያው ከዩናይትድ ስቴትስ እንዳልወጣና አብዛኛው መጠንም ወደ አሜሪካዊ የግል ኮርፖሬቶች አካውንት ውስጥ ሰርጎ ነበር የቀረው።
ታዲያ በስማቸው የተነገደባቸው የሐይቲ ዜጎች በአልሞት ባይ ተጋዳይ ኑሯቸውን ሲቀጥሉ፤ የሀገሪቱ 100,000 ዜጎች የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሆነው አሁንም በስደተኛ ካምፖች ውስጥ ተረስተው ነው የሚገኙት።
አብዛኛው ዕርዳታ ለታለመለት ሰዎች አይደርስም ሲባል መልካም የሚሰሩ ጥቂቶችንም ቢሆን ማስቀየም እንዳይሆን ፅሐፌን በመረጃ ላይ የተመሰረተ ማድረግ ግድ ይለኛል። የሆነ ሆኖ ግን አለም አቀፍ የኦዲት ውጤቶች ያስቀመጡት ከውጭ ዕርዳታ 1/5ው ገና ከጅምሩ ከለጋሽ ሀገራት ፈጽሞ እንደማይወጣ ነው። ይህኛው የርዳታ ማጨናበር በለጋሽ አካላት ባንክ ተቀምጦ ይቀራል፤ ወይም መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ይሰጣቸዋል ነገር ግን ለምስኪን ተረጂዎች አይደርስም።
በፈረንጆቹ 2011 ያደጉ አገሮች 100 ቢሊዮን ዶላር ለመለገስ ገንዘብ ሰብሰቡ፤ ለታዳጊው ዓለም የሚሰጥ የውጭ እርዳታ ነበር፤ መጠኑ እደግመዋለሁ 100 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ከዚህ ውስጥ 22 ቢሊዮን ዶላሩ ፍፁም ከሀገራቱ ሳይወጣ ነበር የቀረው።
በተመሳሳይ አመት ጣሊያን ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለዚሁ ርዳታ ሰብስባ ነበር። ይሁንና 300 ሚሊዮን ዶላሩ ብቻ ነበር አገሪቱን ለቆ የወጣው። ቀሪው ተላልፏል የተባለ የ 1.7 ቢሊዮን ርዳታ እዛው ጣልያን ነበር የቀረው።

አሁን አሁን እንደውም ይህ የርዳታ ማጨናበር ማሳፈሩ እየቀረ ይመስላል። ገመናበፈረንጅ 2019 ይፋ የፈተደረገ ሌላ ሪፖርት ነበር። በሪፖርቱ እንደተገለፀው 25 በመቶ የሚሆነው ዕርዳታ ከለጋሽ ሀገራት እንደማይወጣና የተቀረው 75በመቶውም ቢሆን ለርዳታ ተቀባዮቹ በቀጥታ እንደማይደርስ ነው የገለፀው።ርዳታው በበርካታ ኤጀንሲዎች ውስጥ ያልፋል። እያንዳንዱ ኤጀንሲ የየድርሻውን ይቆርጣል። ችግሩ ይባባስ ዘንድም በእያንዳንዱ ኤጀንሲና ኮርፖሬት የሚፈፀመው ተቆራጭ ላይ ግጉግፅነትና ተጠያቂነት አለመኖሩ ነው። ይህ ይመጣ ዘንድ ታዲያ አለም አቀፍ ዕርዳታ የአንድ ጊዜ ስሌት ውጤት አለመሆኑ ነው። በውስጡ የበርካታ ነገሮች ውስብስብና ስብስብ ውጤት ነው። ከፊሉ ጥሬ ገንዘብ ነው፣ ሌላው የምግብ አቅርቦት፣ ተቀረው ደሞ የዕዳ እፎይታ ይሆንና ​ሰዎች ጭምር ርዳታ ሁነው ይመጣሉ። ይህ ማለት የቴክኒክ ድጋፍ አማካሪዎችና ሠራተኞች ወጪ ይደረግ ዘንድ የተፃፈ በጀት ይከተላል ማለት ነው። ሰዎቹም ከርዳታ ለጋሾች የሚላኩ ነው የሚሆነው። በመሰል የርዳታ መጨናበር ማሳያ የሚሆነው የምስራቅ ኤሺያ ሀገር የሆነችው ቲሞር ናት።
ቲሞ ከነባር ግዛቷ ተገንጥላ ሀገር እንድትሆን ድጋፍ ተደረገና የዛሬ 20 አመት ገደማ በፈረንጅ 1999 ላይ ነፃነቷን አገኘች ተባለ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቲሞር ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ርዳታ ተቆርጦላታል። ከዚህ ውስጥ ታዲያ ሁለት ቢሊዮን ዶላሩ የዋለሁ ለተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ብቻ የዋለ ነበር። ሌላው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ በዕርዳታ ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ ወጪ አድርገውታል። ቀሪውስ? በዚህችው ሀገረ ቲሞር የ UN ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደሞዝ ከአካባቢው ነዋሪ በአስር እጥፍ ይበልጣል። ለምሳሌ፣ ከአውስትራሊያ ወደ ቲሞር የመጣ የታድ ሰራተኛ 200,000 ዶላር ይከፈለው ነበር፣ ይህ የሚሆነው ታዲያ 50% የሚሆነው ህዝቧ በቀን ከ 2 ዶላር በታች የሚያገኝበት በሆነችው ሀገር ላይ ነው።

“ጥርንፍ-ርዳታ” ወይም Tied-Aid ተብሎ ለሚጠራ ፅንሰ-ሀሳብ አዘጋጅተዋልና በዚህ ዘዲዴ የሚጨናበረው ርዳታ ደግሞ ተከታዩን ይመስላል። በዚህ ጥርንፍ-ርዳታ ዘዴ ብድሩ የሚተሳሰረው ከለጋሽ አገሮች የቢዝነስ ኩባንያዎች ጋር ነው። ለጋሿ አሜሪካ ከሆነች ብድሩ ከአሜሪካ ኩባንያዎች ጋር የተሳሰረ ጥርንፍ-ርዳታ ይሆናል ማለት ነው። እነዚህ ኩባንያዎችም ገንዘቡ እንዴት ወጪ እንደሚወጣ የሚወስኑት ይሆናሉ። እንደ ጥናታዊ ሪፖርቶች በ 2012 ከ 14% በላይ የሁለትዮሽ ዕርዳታ በዚሁ Tied-Aid ስር ማለፉ የታወቀ ሲሆን በ 2017 ከ 15% በላይ፣ በ 2018 ከ 19 በመቶ በላይ አድጓል።
ይህን የጥርንፍ-ርዳታ የሚከተሉ ሁሉም ርዳታ ሰጪ ጨገራት ናቸው ማለት ይቻላል። ዩናይትድ ስቴትስ በሰንጠረዡ አናት ላይ ትገኛለች። በ 2018 40% የሚሆነው ዕርዳታ ማለትም 11 ቢሊዮን ዶላር የተገመተ ነው አሜሪካ በ Tied-Aid ዘዴ ያስተላለፈችው። ጃፓን ከ 22% በላይ ይኸውም ከ 4.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጥርንፍ ርዳታ ዘዴ ትለግሳለች። ጀርመን 15% ርዳታዋን ወይም 3.1 ቢሊዮን እንዲሁም ደቡብ ኮሪያ ከ 48% በላይ ዕርዳታዋን በጥርንፍ Tied-Aid አስተሳስራ ልገሳ ትፈፅማለች።
እንግዲህ እነዚህ ሁሉ አገሮች ዕርዳታ ለመስጠት ቃል የሚገቡ ናቸው። ነገር ግን ርዳታውን ለተቀባይ አገሮች ከመስጠት ይልቅ፣ ለኩባንያዎቻቸው ያስተላልፋሉ። ምክንያቱም የእርዳታ ገንዘቡ በቀዳሚነት የራሳቸውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማስከበር ያለመ በመሆኑ ነው።

In fact, the department which was given the task, was itself found to be splurging aid money. The Department for International Development DFID, this was a British government agency for foreign aid. In 2012, an investigation revealed that this agency had spent €20M on five-star hotels, €6M on a university studying mental health, €3.9M on a think tank studying elections in Africa and €400,000 on furniture at its new branch in India.

ከአመታት በፊት የወጣ አንድ ሪፖርት እንዲህ ይል ነበር፡- “ብሪታንያ ለውጭ ርዳታ የምትመድበው በጀት ተቸገሩ ሰዎች ስም ኪሳቸውን ለሚሞሉ የድህነት ከበርቴዎችና የግል ዘርፍ ተዋንያን ነው ፈለፈለ።” ሲል ያትታል። – “Britain’s foreign aid budget had created a group of poverty barons, private players, who were filling their pockets in the name of helping disadvantaged people.”
በዚህ ሁነት ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠው የእንግሊዝ መንግስት ድርጅት ጭምር የዕርዳታ ገንዘብ ሲያጭበረብር ተገኝቷል። DFID, የእንግሊዝ መንግስታዊ ኤጄንሲ ሲሆን የውጭ ርዳታን እንዲያሳልጥ የተቋቋመ ነበር፤ ሙሉ መጠሪያው Department for International Development የሚሉት። ይህ የእንግሊዝ መንግስት የእርዳታ ኤጀንሲ በፈረንጅ 2012 በተደረገ ምርመራ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች €20 ሚሊዮን ዩሮ፣ የአይምሮ ጤናን ለሚከታተል አንድ ዩኒቨርሲቲ 6ሚሊየን ዩሮ፣ 3.9 ሚሊየን በአፍሪካ የሚደረጉ ምርጫዎችን ለሚያጠና መማክርት ወይም ThinkTank እና 400,000 ዩሮ ደግሞ በህንድ ለሚገኝ ቅርንጫፉ ፈርኒቸር ለማሟላት በሚል ወጪ ማድረጉ ነበር ይፋ የሆነው። ለልማት ዕርዳታስ ገንዘብ ሊተርፍ አልቻለም ነበር? ታዲያ ቀሪዋን ፍርፋሪ ብቻ ወደ አፍሪካ ሀገራት በሚል ተወሰደ ተብሏል።
አብላጫው የልማትም ሆነ የችግር ጊዜ ርዳታ የሚውለው ቢሮዎችን ለመገንባት፣ በሚገርም ሁኔታም ርዳታውን እንዴት መስጠት አለብን በማለት በሚደረጉ ጥናታዊ ስብሰባዎች ላይ ነው ፈሰስ የሚሆነው። ቀሪው በርዳታ ወይም በብድር ወደ ታዳጊ ሀገራት ይሄዳል። አንዳንድ ጊዜ ቃል የተገባው ርዳታ በዕዳ እፎይታ መልክ ይለወጣል፤ ይህ ሲሆን ደግሞ ገንዘቡ በተረጂ ሀገራት መሪዎች እጅ እንጂ በሕዝብ እጅ እንዲገባ የሚደረግ አይሆንም።
በፈረንጅ 2011 ኮንጎ የ 7.5 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ቃል ተገብቶላት ነበር። ይበልጥ በሚገርም እውነታ ወጪ ተደረገ ከተባለው ርዳታ የተገኘው 0 ብቻ ነበር። እንዴት እንዴት..? የተባለው እንዲህ ነበር። አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንዲሰጥ በሚል እስከዛውም የዕዳ-እፎይታ በሚለው መንገድ ተቀማጭ እንደሆነ ቀርቷል።
2015 በፈረንጆቹ ዘመን ደግሞ ወርልድ ቪዠን የተባለ አንድ የእርዳታ ድርጅት እንዲህ የሚል ማስታወቂያ አወጣ “የአሜሪካውን ትላቅ ስፖርታዊ መድረክ Super-Bowl ን ለመውደድ – መቶ ሺህ ምክንያቶች!” የሚል የተብለጨለጨ ማስታወቂያ..። የተገለፁት መቶ ሺህ ምክንያቶች ምን ነበሩ? ነገሩ በሱፐር ቦውል የተሸናፊው ቡድን 100,000 ቲሸርቶችን የሚመለከት ነው። እነዚህ ቲሸርቶች በመጀመሪያ የታቀደላቸው ቡድኑ ካሸነፈ እንዲከፋፈሉ ነበር፣ ነገር ግን ተሸነፈ፣ ስለዚህም ይህ ገዢ ያጣው የትልቅ ብራንድ ባለቤት ቲሸርት ምርት በወቅቱ የተራቡ ህፃናት ያሉባቸው ወደተባሉት ዛምቢያ፣ አርሜኒያ እና ኒካራጓ አንዲያመራ ተደረገ።
ወርልድ ቪዥን ይህን ያደረገው የተቸገሩ ህፃናትን ህይወት የሚቀይር ርዳታ በሚለው ነው ለገበያ አቅርቦ ሂሳቡን ያወራረደው። ህፃናቱ በርግጥም ችግርኞች በመሆናቸው ይህን ወርልድ ቪዥን ለአሜሪካዊያን ያሳተመውን የቲሸርት ብራንድ አይተው አያውቁም ነበር።
የእያንዳንዱ ቲሸርት ዋጋ 20 ዶላር ነበር። በአጠቃላይም 2 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ የወጣበት..።
2 ሚሊዮን ዶላር የወጣባቸው 100 ሺህ የሱፐር ቦውል ቲሸርቶች ለዛምቢያ ህፃናት ችግርን ባያባብስም ትርጉም የሌለው ብልጭልጭ ነበር።

ታዲያ እነዚህና እነዚህን መሰል ርዳታዎች አሁንም አሉ፤ የሚቀጥሉም ነው የሚመስለው። በሚናቸው ሲመዘኑ ቅኝ ግዛት ሆነው የሚዘልቁ አይነት ናቸው። ኢ-ርትአዊነትን ከመዋጋትና ድህነትን ከማስወገድ ይልቅ (በተለይም) ምዕራባውያኑ ንግዳቸውን ለማስፋፋትና ለትርፋማነታቸው አዋጪ ሆኖላቸዋል። ድሆችን ከመርዳት በላቀ ደረጃ በፖለቲካዊ አለማ እና በግልና የቡድን ጥቅም አቅጣጫዎች የሚመራ ነው።
ይህ በርዳታ የተሸፈነ ስውር ተግባር አሁን አሁን አሳፋሪነቱን ማጣት ጀምሯል። ለዚህም ነው የአሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባይደን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አንቶኒ ብሊንከን፣ የUSAID ዳይሬክተሯ ሳማንታ ፖወር በቅርብ ጊዜያት በግላጭ ተናግረውታል። “ዕርዳታን የሚጠቀሙበት ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ፖሊሲ መሣሪያነት- የአሜሪካን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማስጠበቂያ ዘዴ ፣ ለአሜሪካ አዳዲስ ገበያዎችን የማግኛ አስተማማኝ መንገድና ከዋሽንግተን ፍላጎት የሚስማሙ መንግስታትን ማንበሪያችን ነው።” በማለት በአንድ ቃል በይፋ ነው መግለጫ የሰጡበትና ደጋግመው ያረጋገጡት።

✍️በእስሌማን ዓባይ – #የዓባይልጅ

Ethiopia #HornOfAfrica #EU_Africa #USAfricaLeadersSummit22

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories