የዓባይ ንጉሠ ነገሥቱ ፡ ጀማል በሺር – ኡሥታዝ

ብፃዊ ፀሐፍትና የፖለቲካ ተንታኞች ስለሱ ብዙ ተናግረዋል። ስለ ዓባይ በሚወያዩባቸው አጀንዳቸው መሀል “ኡስታዝ ጀማል” ሳይሉ አያልፉም።

ከኢትዮጵያውያን፣ ከአረቡ አለም ልሂቃን እና ከሌሎች ሃገራት ዜጎች ይበልጥ እንዲታወቅ ያደረገው በቀጥታ ስርጭት እየተዘጋጀ የሚቀርበው ‘የዓባይ ንጉሶች’ Kings of Abay የተሰኘው ቻናሉ ነው። በየቀኑ ከ5-8 ሰዓት የሚቆየው ‘የዓባይ ንጉሶች’ ፕሮግራሙ ይህ ፅሁፍ እስከተሰናዳበት ዕለት ድረስ ከ 18 ሚሊዮን ጊዜ በላይ የታየ ሲሆን፤ የዕይታው ሰዓታዊ መለኪያ ደግሞ 6 ሚሊዮን ሰዓታትን ሊደፍን ተጠግቷል። 758 የቀጥታ ስርጭት መሰናዶዎች የቀረቡበትና የሚገኙበትም ቻናል ነው። ከ15ሺ በላይ ቋሚ አባላትም አሉት፡፡ በየትኛውም መመዘኛ ቁጥር አንድ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሚዲያ መፍጠር ችሏ፤ ጀማል በሺር

Kings of Abbay ወይም የዓባይ ንጉሶች ዩቲዩብ ቻናል በየትኛም መስፈርት ወደር የሌለው ተፅዕኖ ፈጣሪ ነው። ቻናሉ የቀጥታ ስርጭት ነው። አሳታፊ መሆኑ ሌላው ጉልበቱ ነው። መረጃ ከማድረስ በተጨማሪ አስተያየቶችና ማጠናከሪያ መረጃዎች አዜጎች ከምሁራንና ከአንቂዎች በቀጥታ የሚስተናገዱበትም ነው። በእያንዳንዳንዱ የቀጥታ ስርጭቱ አነሰ ከተባለ አንድ ሺህ አራት መቶ የቀጥታ ታዳሚ አለው። ከአስራ አምስት ሺህ በላይ አባላቱ ጀማል የሚለውን ማድመጥ ብቻ ሳይሆን በመዋጮ እና በተለያዩ ተግባራዊ ግልግሎቶች ላይ የሚንቀሳቀሱት ናቸው።

ኡስታዝ ጀማል በዚህ ፕሮግራሙ ላይ ከዓባይ ወንዝ እና ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በተለይም በአማርኛና በአረብኛ ቋንቋዎች በርካታ መሰናዶዎችን ማቅረብ ችሏል፡፡በሚዲያ ቻናሉ አማካኝነት ያፈራቸውን ተከታዮችና ኢትዮጵያውያን የዓባይ ንጉስታት አባላትን በመያዝ በበድር እና በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበር በሲያትል እንዲሁም በዋሽንግተንDC ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሃብት የማሰባሰብ ስራ በመጀመር ከፍተኛ ገቢ ማሰባሰብ ችሏል፡፡

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥም በየዕለቱ በዩቲዩብ ሚዲያ ቻናሉ ቅስቀሳ በማድረግ በ 24 ሰዓት ውስጥ ከ 100 ሺ ዶላር በላይ በማሰባሰብ ትልቅ ተፅዕኖ ማድረግ የቻለ ነው። አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ዶላር በላይ ያደረሰውን መዋጮም በስኬት ገቢ አድርጓል። ከተባበርን ብዙ መስራት እንችላለን የሚለው የኡስታዝ ጀማል መርህ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን በማስተባባር ተጨማሪ ሚሊዮን ዶላሮችን ማሰባሰብ እንደሚችልና ለዚህም የዜጎች የአገር ፍቅር ዋነኛው አቅም ስለመሆኑ በልበ ሙሉነት ይገልፃል፡፡

በአረቡ ዓለም ከሙሐመድ አል አሩሲ፣ ያሲን አህመድ(ስዊድን)፣ ሙሳ ሸኮ፣ ሰብሪን ሸፋ ሙሐመድ(ፖላንድ)፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያ ሙስሊም የዓባይ ተሟጋቾች ጋር በመሆን የፈጠሩት ንቅናቄ ትልቅ ለውጥ ስለማምጣቱ ግብፃዊያኑ በተለያዬ አጋጣሚ የመሰከሩት እውነት ነው። አንድ ግብፃዊ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኢትዮጵያዊያን በግድቡ የዲጂታል ዘመቻ 80 በመቶውን የድል ውጤት ወስደውብናል ማለቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ሌላኛው ግብፃዊ ምሁር ደግሞ “የግብፅ ጠላቶች ኢትዮጵያዊ አፄዎች ይመስሉን ነበር፤ ነገር ግን ዋነኞቹ እነዚህ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ሆነው አገኘናቸው” ነበር ያለው። የዚህን ተፅዕኖ የአንበሳ ድርሻ የሚወስደው ደግሞ ኡስታዝ ጀማል ነው።

ኡስታዝ ጀማል በሰሳም ፋውንዴሽን እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰላምና ዕድገት ማዕከል ውስጥ በአመራርነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

በታላቁ የህዳሴ ግድብና በዓባይ ጉዳይ በዓረቡ ዓለም የኢትዮጵያ ዕውነት ይታወቅ ዘንድ ለረጂም ጊዜ እያከናወናቸው የቀጠሉት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አበርክቶው ከተለያዩ ባለድርሻዎች ድጋፍ እንዳይለየው የሚለው ሊሰመርበት ይገባል።

ሰላም ጤና ስኬት እና ረጂም እድሜ ለዓባይ ንጉሰ ነገስቱ ኡስታዝ ጀማል ይሁንልኝ።

እስሌማን ዓባይ፣ የዓባይ ልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories