የዲጂታል 🇪🇹ዘመቻው በማንሰራራት ላይ

     የዓባይ፡ልጅ እስሌማን፡ዓባይ

ኢትዮጵያውያኑ ስለ ሀገራቸው ጉዳይ የሚያሰሙት ድምፅ አሁንም ቀጥሏል። በውጭ እና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ኤርትራዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጅ ዜጎች በተለይም ህወሃት ድጋሚ የከፈተውን ጦርነት በማውገዝ ረገድ ተሳትፏቸው በማደግ ላይ ይገኛል።

ትዊተር ላይ ከተሰራጩ መልእክቶች መካከል #TPLFisTheCause በሚለው ሀሽታግ ባለፉት ሰባት ቀናት ከ 312,000 በላይ መልእክቶችን አሰራጭተዋል። ይህ የዳታ አናሊቲክስ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ባሉት 24 ሰአታት ብቻ መቶ ሺህ ያህል(97 ሺህ) መልእክቶች በተጠቀሰው ሐሽታግ ሊሰራጭ ችሏል።

#TPLFisTheCause በሚለው ሀሽታግ በአለም አቀፍ ደረጃ የተሰራጩ የትዊተር መልእክቶች ሳምንታዊ አሀዝ


በመላው አለም በሁሉም አህጉራትና ሀገሮች መዳረስ የጀመረው ይህ የህወሃትን ጦርነት የሚያወግዘው ሐሽታግ በሰሜን አሜሪካ ካናዳ አውሮፓ እስያ አውስትራሊያ ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም አፍሪካ ሀገራት በሚኖሩ ዜጎች ያስተላለፉት መሆኑን የአናሊቲክስ ውጤቶቹ አመላክተዋል።

ከኢትዮጵያ የተሰራጩ መልእክቶች ብልጫ የወሰዱበት ከተጠቀሰው ሐሽታግ ጋር የተስተጋቡ ድምፆች ከኢትዮጵያ በመቀጠል በአሜሪካ፣ ኔዘርላንድ ህንድ ማሌዢያ ካናዳ ጣልያን እንግሊዝ ጀርመን የሚገኙ ትዊተር ተጠቃሚዎች የደረጃ ቅደም ተከተሉን ይዘው ይገኛል።

TPLFisTheCause በሚል ሀሽታግ ከፍተኛ መልእክት የተሰራጨባቸው ሀገራት

ህወሃት ድጋሚ ከከፈተው ጦርነት አስቀድሞ በህወሃት ደጋፊያን Tigray Under Attack በሚል ሐሽታግ የትዊተር ዘመቻዎች ሲደረጉ ይገኛሉ።

ከቀናት በፊት የተሰራው አናሊቲክስ የታየው ውጤት የኢትዮጵያኑን ድምፅ በብዙ እጥፍ መብለጡን ነበር። ህወሃትን የሚያወግዘው ሀሽታግ ስርጭትም በቀን ከአስር ሺህ ያልበለጠ ነበር።

አሁን ላይ ማንሰራራት ያሳየው የኢትዮጵያዊያን የትዊተር ዘመቻ የተመዘገበው ከ300 ሺህ በላይ ሳምንታዊ እና መቶ ሺህ የደረሰው ዕለታዊ ውጤት እየሞቀና እያደገ እንደሚቀጥል የሚጠበቅ ነው።

✍️ Esleman Abay

#የዓባይልጅ #eslemanabay

DisarmTPLF #TPLFisTheCause #childsoldiers #tplfbelligerencemustbecondemned #ENDF #EthiopiaPrevails

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories