የግብፅ ጦር በሱዳን ማሊያ

Alburhan and alsisi

Esleman Abay

የግብፅ እጅ በሱዳን ጦር ውስጥ በረጂሙ የገባው አል-በሽር ከወንበራቸው ከመነሳታቸው ጀምሮ ነበር።

የሱዳን ሽግግር ጦር ምክር ቤት መሪ አብዱል-ፈታህ አል-ቡርሃን ልክ የዛሬ አመት በተሾሙበት ማግስት የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ያደረጉት በካይሮ may 25 ነው። ክስተቱ ከቀደመው የሱዳን ዲፕሎማሲ የተለየ ነበር። በቀደሙ ጊዜያት አዲስ አበባ ለካርቱም ቀዳሚ ነበረች። በርግጥ የሱዳኑ ጠቅላይ ከኢትዮጵያና ከጠ.ሚ አቢይ ጋር የተወዳጀ አካሄድ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል። የአረብ ሊግ በግድቡ ድርድር ያወጣውን አድሏዊ መግለጫ በተቃወሙ ከቀናት በኋላም ነበር ከግድያ ሙከራ የተረፉበት ክስተት የተፈጠረው።

የሱዳን ጦር ግን በግብፅ እጅ እንደሚዘወር በርካታ ተንታኞች በተጨባጭ መረጃ ያስረደረሉ። የጦሩ መሪ አል-ቡርሃን አዲስ አበባን የጎበኙት ከአፍሪካ ማዶ ተሻግረው የግብፅ አጋር የሆነችውን የተባበሩት አረብ ኢምሬትን UAE, ደርሰው ከመጡ በኋላ ነበር። ከግብፅ ጋር በውስን አጀንዳዎችም ቢሆን ተፃራሪ የሆነችዋን ሳዑዲ አረቢያን የጎበኙት ደግሞ ከመካከለኛው ምስራቅ አልፈዋት መጡና ደቡብ-ሱዳንና ኢትዮጵያን ካደረሱ በኋላ ነበር።

ይህ የአል ቡርሃን አካሄድ የግብፅ፣ የሱዳን፣ የሳዑዲና የተ.አረብ ኢምሬት axis ውስጥ የተቀላቀለ ነው። የአል-በሽር አጋር ከነበሩት የቱርክና ኳታር axis በተፃራሪው መሆኑ ነው። ይህ የአል-ቡርሀን ጉብኝት ለሱዳን የነፃነትና ለውጥ ኃይሎች ጭምር ሰርፕራይዝ አይነት ያልተጠበቀ ክስተት እንደሆነባቸው ነበር የቡድኑ መሪ ባቢከር ፋይሠል በወቅቱ ለዓል-ሞኒተር የገለፁት። ከጉብኝታቸው መልስም የኳታሩን ተፅዕኖ ፈጣሪ ቴሌቪዥን የካርቱም ቢሮ እንዲዘጋ ያደረጉት፣ እኚሁ አል ቡርሀን። በነዚህና ሌሎች ማሳያዎችም ነው የአል-ቡርሃን ጉብኝት በአገሪቱ ቀጣይ አካሄድ ላይ ወሳኝ አንድምታ አለው የሚሉ ተንታኞች የተበራከቱት።

ሱዳንን ለመጠቀም ቀዳዳ ያልነበራት ግብፅ የዛሬ 2 ዓመት ከዛ በፊት የነበራት ዕድል ኤርትራን መጠቀም ነበር። በወቅቱ የሱዳን አማፂ ኃይሎችን እና በተባበሩት አረብ ኢምሬት የሚደገፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ሳዋ ማሰልጠኛ አስገብታ ስትዶልትና ስታሰለጥን ነበር። ይህን ተከትሎም የሱዳን ጦር አዛዥ ጄነራል ኢማድ አ-ዲን ሙስጠፋ አዳዊ ወደ አዲስ አበባ መጡ። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከነበራቸው ቆይታ በኋላም ከኤርትራ የሚዋሰን ድንበሯን ዘጋች። ከፍተኛ የጦር ሀይልም ወደ ኤርትራ ድምበር አስጠጋች። ብዙ ሳይቆይም ከኢትዮጵያና ሱዳን ወታደራዊ ጦር ተመስርቶ የሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበርንና ተያያዥ ችግሮችን በጥምረት እንዲጠብቁ ተደርጎ ነበር።

አሁን ላይ ግን በግብፅ የሚደገፉ የሱዳን ተቃዋሚ ሀይሎች የአል-ቡርሃን ጦር አካል ሆነዋል። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ትብብር መመለሷ ግብፅ ሽብርተኞችን እንደ ድሮው ኢሳያስ አያደራጅላቸውምና ሙሉ ለሙሉ ወደ ሱዳን ጦር ተጠቃለዋል። ከሰሞኑ የግድቡ ውሃ አሞላል ክልከላ ሴራዋን ትራምፕ የኮሮና ወረርሽኝ ዘመቻን ለመምራት ደክመው መገኘታቸው ማስታገሻ ሆኖልናል። ግድባችንን በራሳችን ዕቅድ መሙላት ልዕልናችን መሆኑን አስረግጠን ከገለፅን በኋላ የተ.መንግስታት ድርጅት፣ አውሮፓ ህብረት፣ የፀጥታው ምክር ቤት፣ እንዲሁም እንደ ጀርመን ያሉ አገራት አቋሟን ያጣጣሉባት ግብፅ ወደ ድርድሩ እንመለስ ስትል የመጨረሻ አማራጯን ልሞክር ብላለች። በሱዳን በየጊዜው በጦሩ ተፅዕኖ ስር አየዋሉ መሆናቸው የሚነገርላቸው የጠቅላይ ምኒስትር ሀምዶክ መንግስት የውሃ ሙሊት ዕቅዳችንን እንደማይቀበለው ይፋ ሲያደርግ ነገሮች ከቁጥጥራቸው ውጭ መሆናቸውን ያመላክታል። ተያይዞ የተባባሰው የኢቲዮ-ሱዳን የድንበር ላይ ግጭትም የሴራው አካል ነው። ከዚህ ቀደም ግጭቶች አልፎ አልፎ የነበሩ ቢሆኑም አገራቱ እንደ አገር ተወቃቅሰው አያውቁም። Sudan Tribune “የሱዳን ጦር በመሰል ችግሮች ዙሪያ የኢትዮጵያን መንግስት ተጠያቂ ሲያደርግ የመጀመሪያው ነው” ሲል ያተተውን የኛ መከላከያ ሀላፊዎች “ስለ ጉዳዩ መረጃ የለንም” ከሚለው መግለጫ ጋር ሲተያይ በርግጥም የሱዳን ጦር ባልጠበቅነው ሁኔታ (ነገር ግን ልንጠብቀው የሚገባን) በግብፅ ማሊያ እንድንጫወት እየቆሰቆሰን ነው።

ታዲያ፣ ይህን ጨዋታ ከጦር ይልቅ በዲፕሎማሲ ሜዳ ብናስተናግደው ግብፅን ብዙ ነጥብ አሳጥቶ አትራፊ ያደርገናል ባይ ነኝ።
ለተጨማሪ,👇
https://www.google.com/amp/s/www.al-monitor.com/pulse/en/originals/2019/06/egypt-sudan-military-council-protests-role.amp.html%3fskipWem=1
https://www.sudantribune.com/spip.php?article69393

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories