
ግብፅ ከአሜሪካ የሚኖራትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማሳደግ ሌሎችን ለመጫን የአገሪቱ ኢንተለጀንስ ተቋም የአመታት ስራ ሰርቷል። ከነዚህ ውስጥም ለታላላቅ የ PR ኩባንያዎችን በርካታ ወጪ መመደብ ዋነኛው ነው። ኩባንያዎቹም በሁሉም የሚዲያ አማራጮች ስለ ግብፅ አወንታዊ ሽፋን እንዲሰጣት አቅማቸውን ሁሉ ይጠቀማሉ። የ PR ስራ ሂደቶች በሆኑት RACE ማለትም (Research, Action, Communication, Evaluation) መሠረትም የመሪውን የምርጫ ድምፅ ከማብዛት የውጭ ርዳታን እስከማስጠበቅ እንዲሁም ተቀናቃኝ ፖለቲከኞችንና አገራትን በአሉታዊ ዘገባ እስከ ማጠልሸት ይሻገራል።
ለምሳሌም 2017 ላይ ግብፅ ዌበር ሻንዲዊክ የተባለውን አሜሪካዊ የ PR ኩባንያ የቀጠረች ሲሆን፣ በወር $ 100,000 ዶላርና ሌሎች ወጭዎች ትከፈለው ነበር ፡፡ ከዌበር ሻንዲዊክ ቅጥር በተጨማሪም የሎቢቢ ድርጅት የሆነውን Cassidy & Associates በወር 50,000 ዶላር እና ሌሎች ክፍያዎችን በማከል ቀጥረዋል።
ኩባንያው ድረ ገፅ ለግብፅ አዘጋጅቶ በጎ በጎውን ማስወራት ያዘ። አሉታውንም ለመጠጋገን ሞከረ። ለአብነትም የግብፅ መንግስት በሲቪል ማህበረሰቡ ዙሪያ በአሜሪካ ወቀሳ ለተፈጠረበት ጥቁር ጥላ ብርሀን ለመፈንጠቅ ሞክሯል ፡፡ የግብፅ አዲሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አዋጅ ልዩ መብትና ዋስትና ለመስጠቱ፣ አበረታች የለውጥ እርምጃዎችን እንደወሰደ፣ ለግሉ ዘርፍ ኩባንያዎችና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን ለማበረታታትም እስከ 10 ከመቶ የግብር ቅናሽ ስለማድረጉ ወዘተ ለ capitol hill ባለስልጣናት lobby አድርጓል።
በሌላ አውድ ደግሞ ሂውማን ራይትስ ዎች የአልሲሲ አዲስ ህግ “ታይቶ የማይታወቅቅ የጭካኔ ደረጃን የሚያመጣና የብዙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሥራ በሕገ-ወጥ መንገድ ገለልተኛ ያደርጋል፣ በዚህም እራሳቸውን ችለው እንዲሰሩ የማይቻችሉ ያደርጋቸዋል። ሰብዓዊ መብትንም ይጋፋል ወዘተ ሪፖርት ሲቀርብበት እየተከታተለ መልካሙን ሲዘግብለት የነበረው የ weber shandwik ተቀጣሪ ጋዜጠኞች ነበሩ።
…”Throughout the hearing, the only person who attempted to defend Egypt in any way was a silent Weber Shandwick employee at the back of the room who handed out glossy press packets praising ‘Egypt’s progress’.”…
በሌላ በኩል ተገዳዳሪዎችን በ Negative public relations በሌላ አጠራሩ dark public relations (DPR) በሚባለው ማጠልሸት ሌላው ዘመቻ ነው። ለምሳሌም ከ weber shandwik ጋር ሰባት ወራት ብቻ ሰርተው ኮንትራታቸውን ከሰረዙ በኋላ apco ከተባለው ሌላ የ pr ተቋም ጋር የሰሩትን እንመልከት። apco በአሜሪካ ቁጥር ሁለት ግዙፍ የ pr ተቋም ነው። የግብረ ሰዶም ተግባርንም ይደግፋል። ግብፅ ለ apco 120 ዶላር እና ተጨማሪ ክፍያን ለመፈፀም ተስማማች።
The Intercept እንደዘገበው APCO 12 አለማቀፍ ሰዎችን በአሜሪካ አውሮፓና እስራኤል አሰማርቶ ስራ ጀመረ። ኩባንያው ወዲያውኑ ነበር በዬ ወሩ 333 ሺህ ዶላር በየወሩ ከነጥቅማ ጥቅሙ እፈልጋለሁ ያለው። ኩባንያው ግድቡን አስመልክቶ ለግብፅ ካሰራላት ዘገባ ውስጥ የቅርቡን ብንመለከት በ foreign policy እና associated press የቀረበውን ሽፋን ማየት ይቻላል። ሁለቱ ሚዲያዎች የ apco አጋሮች ከሆኑት ውስጥ ናቸው። ጋዜጠኛ ኤሊያስ ለ associated press የገዱ አንዳርጋቸውን ጠንካራ ንግግሮች ያካተተ ቃለ መጠይቅ ለንባብ ካበቃው በኋላ ካይሮም ሁለት ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር በዚሁ የ AP ድረ ገፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ቃለ መጠይቅ ያቀረበችው። በዚህም ግብፅ ለአለማቀፍ ህግና ለድርድር ቀና እንደሆነች የሚያግባባ የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ተሞክሯል። የ foreign policy መፅሔትን አንድ ማሳያ ለመጥቀስም የግድቡን ሙሊት አስመልክቶ የቀረበው ፅሁፍ አብነት ይሆናል። በዚህም ፅሁፍ የትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ርዳታ የማቆም አቋም አንፀባርቋል የሚለው ዋናው ጭብጥ ነው። በድርድሩ ዝርዝር ድንጋጌዎች ላይም ኢትዮጵያዊ ተደራዳሪዎችን ለመጫን ያለመ ነው ሚመስለው።
ባጠቃላይም ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ dark public relation የሚባለውን ዘመቻ ለአመታት ስትጠቀም ቆይታለች። ከአለማቀፍ የ pr ተቋማት በተጨማሪ የራሷን ተቋማትም ለማጎልበት ሞክራለች። ከብዙዎቹ ውስጥም
Ketchum Raad Middle East, Media Republic, Editor እና MEAComS ይገኙበታል።
Ketchum Raad Middle East የተባለው ድርጅት በ 70 አገራት የሚሰራ ሲሆን ለግብፅም በካይሮና በ14 ከተሞችና በ 12 አገራት ቢሮ ያለው ነው። በ corporate communications፣ brand marketing እና crisis management በይፋ የተገለፁ ተግባራቱ ሲሆኑ የደህንነት ስራ ደግሞ በጥልቀት የሚሰራው ነው።
በአገራችን መሠል ተሞክሮ ያለው አየር መንገዳችን ነው። ከ 6 አመት በፊት emerald media group ን ለ UK እና Ireland ገበያው ቀጥሯል። አለማቀፍ ኩባንያ መሆኑ የ pr ፋይዳን እንዲገነዘብ ያደረገው አየር መንገዱ emerald media group ን ስለመረጠበት ምክንያት በ uk እና ireland ማናጀሩ በኩል ተከታዩን ነበር የገለፀው።
“Our increased capacity with state-of-the art equipment such as the Boeing 787 Dreamliner, and an award winning cabin product provides us with the perfect opportunity to bolster our PR efforts in the very important UK and Ireland market. We selected Emerald Media following a competitive pitch because of their strong media contacts, their experience and understanding of the aviation sector,” said Michael Yared, Country Manager, UK & Ireland.
ባለፈው 2019 ላይ ደግሞ የደቡብ አፍሪካውን Africa Communications Media Group ቀጥሯል። በደ.አፍሪካ የአየር መንገዱ ማናጀር Abel Alemu ተከታዩን ብለው ነበር።
“We are looking forward to working with Africa Communications Media Group on promoting the product and services of the airline to the wide client base and general public in south Africa. They approached the brief with a great deal of creativity and expertise which was paramount to us in finding the right agency to work with”.
በነዚህ ተግባራቱ አየር መንገዱ የሄደበትን ተሞክሮ ለግድባችንና ለቀጠናዊ ጂኦፖለቲክስ አልሰራንበትም። በነገራችን ላይ እኛ በርካታ እውነቶች ስላሉን የ pr ድርጅቶቹ የግብፅን ያህል ክፍያ አይጠይቁንም። ገንዘቡ በአገራችን እንደነ መብራት ሃይልና ንግድ ባንክ እንዲሁም ቴሌና ውሃና ፍሳሽ ለቴሌቪዥን የአየር ሰዓትና የራሳቸውን ቴሌቪዥን ለማቋቋም ከሚያደርጉት ፋይዳቢስ የገንዘብ ጨዋታ ባነሰ ወጪ ሊሰራ የሚችል ነው።
ከታሰበበት አሁንም አልረፈደም!