የጣናን ችግር በኢትዮጵያ አቅም ብቻ መፍታት ይቻላልን?

Pan-African Global Concern – Nile Basin

ጣናን ለመታደግ የአገር ውስጥ አቅም ብቻውን በቂ አይሆንም። የናይል ተፋሰስ፣ የአፍሪካ ህብረትና አለማቀፍ ድርጅቶች ድርሻ ካልታከለበት ዘላቂ አስቸጋሪ ይሆናል። መሠል ተሞክሮዎችም ይህንኑ ያሳያሉ። ለማሳያም የቻድ ሀይቅን ለመታደግ የሀይቁ ተፋሰስ አገራት እንዴት አለምን እንዳሳተፉበት እቃኛለሁ።

የቻድ ሐይቅን ለመታደግ “ፓን-አፍሪካ ፕሮጀክት” ነው የተቀረፀለት።

በቻድ ሀይቅ ላይ የተደቀነው አደጋ

ቻድ ሐይቅ በአንድ ወቅት በትልቀቱ የዓለማችን ስድስተኛው የነበረ ቢሆንም ከ 1960ዎቹ ወዲህ ግን 90 በመቶ በላይ የውሃ ይዞታው ወደ የብስነት ተለውጧል። ከ 36 ሺ ስኩዌር ኪ.ሜትር ወደ 5 ሺ ተወሰነ። በ 5 አፍሪካዊ አገራት ውስጥ የ 40 ሚሊዮን ዜጎች በሰብል እርሻና እንስሳት እርባታ፣ በአሳ ማጥመድና በንግድ ተግባራት በመሠማራት ኑሯቸው በቻድ ሐይቅ ላይ የተመሠረተ ነበር ፡፡ ተፋሰሱ የአፍሪካን ስፋት ስምንት በመቶ የቆዳ ስፋት የሸፈነ ነበር። በአልጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቻድ፣ ሊቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ኒጀርና ሱዳን ይዋሰናል።

ቻድንየመታደግየተፋሰሱአገራትያከናወኑትየተቀናጀአለማቀፍ_ዘመቻ

ከባድ አደጋ የተደቀነበትን ቻድ ሐይቅ ለመታደግ የሀይቁ ተፋሰስ አገራት በሰፊው ነበር መንቀሳቀስ የጀመሩት። ከሁለት አስርት አመታት የዘለቀ ነበር ጥረቱ። በጦርነትና አለመረጋጋት እንዲሁም የፖለቲካ ሽኩቻና የመሪዎች መለዋወጥ በቀጠናው በስፋት የተስተዋለ ቢሆንም ሀይቁን ለማዳን ግን በርካታ አገራት ነበሩ ተቀናጅተው ሲንቀሳቀሱ የሚገኙት። ከአምስት በላይ ታላላቅ የምክክር ስብሰባዎችንም አካሂደዋል፡፡ 2018 ላይ ታዲያ ግዙፍ የሆነ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በናይጄሪያ አዘጋጅተው ነበር፡፡ ከ 1600 በላይ ተሳታፊዎች ከአለም ዙሪያ ታድመውበታል።

በርካታ የሀገር መሪዎችን ባሳተፈው ኮንፈረንስ ላይ የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሀመዱ ቡሐሪ የቻድ ሐይቅን የማዳን አጣዳፊነትን ሲያስረዱ “እርምጃ የምንወስድበትና ሰብአዊነታችንን የምናሳይበት ጊዜ አሁን ነው” ብለዋል።

UNESCO, WORLD BANK, AFRICAN DEVELOPMENT BANK እና ሌሎች በርካታ አህጉራዊና አለማቀፍ የልማትና ትብብር ተቋማት መሪዎች የመፍትሄው አካል ለመሆን ተሳታፊ ተደርገዋል።

የፕሮጄክት ዕቅድም ቀርቦ ነበር። ፕሮጀክቱን ሊፈትኑ በሚችሉ ውስብስብ አካባቢያዊና የምህንድስና ተግዳሮችን መቋቋም የሚያስችል አቅም ማጎልበትና መገንባት በሚቻልበት ነጥብ ላይም ከመግባባት ላይ ተደርሷል። ከነዚህ ውስጥም:-
1, በቻድ ሐይቅ ተፋሰስ ስላሉት የጄኔቲክ ሀብቶችና የብዝሃ-ህይወት ዳታ ፕላትፎርም መመስረት

2, የቻድ ሐይቅን መልሶ እንዲያገግም የሚያስችሉ ሳይንሳዊና ቴክኒካዊ ፈጠራዎችን ማቀናጀት

3, በሐይቁ ተፋሰስ ዙሪያ የነበረውን ሰላም ለመመለስና ክልላዊ ትብብርን ለመፍጠር ጠቃሚ የሆኑ መሠረተ ልማቶችና ፕሮጀክቶች የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ መተግበር፤ ወዘተ ከመግባባት የተደረሰባቸው ሲሆን የፀደቁ የመፍትሄ አማራጮችን በገንዘብ መደገፍ ደግሞ ቁልፍ የሆነው ርምጃ ነበር።

በዚህም የቻድ ሀይቅ ተፋሰስ ኮሚሽን LCBC የገንዘብ ድጋፍ አድርጎ ከአፍሪካ መንግስታትና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ADB በኩልም የተቀናጀ ፈንድ እንዲቀርብ ተስማምተዋል። መጠኑም 50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው። ከምንም በላይም ከ 20,000 square km በላይ ውሃ ከኮንጎ ወንዝ በሚገነባ በሺህ ኪ.ሜትር የሚረዝም ማስተላለፊያ ውሃ ወደ ቻድ ሀይቅ እንዲገባ በማድረግ ላይ ተስማምተዋል። ሀይቁን የማዳን ተግባሩም “Saving lake Chad, a Pan-African Initiative” በሚል ተግባብተውበታል።

ጣናን_ለመታደግ

በጣና ሀይቅ ዕውነታዎች እነሸጀምር። ሀይቁ 3672 .ኪ.ሜ ስኩዌር ስፋት ነበረው። አሁን ወደ 3000 ወርዷል። ማለትም የሐዋሳና የዘዋይ ሐይቆች ተደምረው የሚያክል የሃይቁ ክፍል ወደ የብስነት ተቀይሯል። የአማራ ቴሌቪዥን ከወራት በፊት እንደዘገበውም የሀይቁ 24 ሺ ሄክታር የውሀ ክፍል በእምቦጭ አረም ተወሯል፡፡

የተደረጉ_ጥረቶች

ይህ አደጋ የበርካታ ዜጎች ስጋት ሆኖ ቢቆይም የተቀናጀ የሚባል ርምጃ አልተወሰደም። ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ከወር በፊት እንዳሉት “ጣናን መታደግ ካልቻልን ሌሎች እቅዶቻችን ሁሉ አደጋ ውስጥ ይገባሉ ፤ ምክንያቱም ጣና ሀይቅ የህዳሴው ግድብ ዋና ምንጭ ስለሆነ መጠበቅ አለበት !” ማለታቸው ይታወሳል።

በትላንትናው ዕለትም ምክ.ጠ. ምኒስትር ደመቀ መኮንን የእምቦጭ አረምን በዘላቂነት መከላከልና መቆጣጠር ያስችላል ተብሎ በተዘጋጀ ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በምክክሩም..
“…ስትራቴጂክ ዕቅዱ አረሙን ማስወገድ፣ በዘላቂነት የውኃና አካባቢ ጥበቃ መሥራትና ነፃ የሀይቅ ዳርቻ መሥራት እንዲሁም በሀይቁ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ ነው…። …የተለያዩ አገሮችን ተሞክሮች በማየት እምቦጭ አረምን ለኃይል አማራጭነት መጠቀም እንችላለን” መባሉን አብራርተዋል።

ይህ ወሳኝ ጅማሮ ነው። ነገር ግን የተጠቀሱ ተግባራት ሌሎች ባለድርሻ አፍሪካዊና አለማቀፍ አካላትን ካላካተተ የአቅም ውስንነት ይገጥመናል ባይ ነኝ። ጣናን መታደግ ከኢትዮጵያም በላይ አገራትና አለማቀፍ ተቋማትን የሚመለከት ነው።

የጣና ሐይቅ 15 ወሰን ተሸጋሪ አካባቢዎችን በማካተት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመሬት ከባቢ ጥብቅ አካባቢዎች ጥምረት “World Network of Biosphere reserves” በሚል ከአለም አገራት ከመረጣቸው 651 ብርቅና ድንቅ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ በተ.መ.ድ የትምህርት የባህልና ትምህርት ድርጅት UNESCO አራተኛው የተፈጥሮ አካባቢ ነው፡፡ የUNESCO መረጃ ቋት፡- “ጣና የብዝሃ-ህይወት መናኸሪያ፤ የአዕዋፋት መገኛ፤ የናይል ዋነኛ የውሀ ምንጭ፤ የእርሻ መሰረትና የዘረመል መገኛ” ሲል ይገልፀዋል፡፡ ከ50% በላይ የኢትዮዽያ ገጸ-ምድር ውሃ መገኛ ነው። ከ 67 በላይ የአሳ ዝርያዎች (ከግማሽ በመቶ በላይ በሀገር ውስጥ ብቻ የሚገኙ)፡፡ ከ 217 በላይ የአእዋፍ ዝርያ በሀይቁ ዙሪያ ይገኛሉ፡፡ በዩኔስኮ “የትምህርት ከተማ” ተብላ የተመረጠችው የባህርዳር ከተማም ቁልፍ አቅሟ ጣና ነው።
በያዛቸው 37 ደሴቶች ውስጥ ከ 15 ሺ በላይ ሰዎች ይኖራሉ። ከ 2.5 ሚሊዮን በላይ ኢትዮዽያውያን ኑሮ በሀይቁ የመሠረተ ነው።

በመሆኑም የጣና ጥቅምም ሆነ ችግር የኢትዮጵያዊ ብቻ አይደለም። አፍሪካን፣ ዩኔስኮን፣ አለም ባንክን፣ የናይል ተፋሰስ አገራትና መላውን አለምን የሚመለከት ነው። የአየር ንብረት ለውጥ የአለም ስጋት በመሆኑም ጣናንና አካባቢውን የመጠበቁን ተግባር የአለም የቤት ስራ ይሆን ዘንድ ፕላትፎርም መዘርጋት አለብን።

Saving Lake Tana, a Pan-African and Nile Basin Initiative” የሚል ፕሮጀክት ተቀርፆ አለማቀፍ ተቋማትንም እንዲያሳትፍ ቢደረግ።

ከቻድሀይቅተሞክሮ እንቅሰም

በተለይም አንድ ኢትዮጵያዊ ጉምቱ ባለስልጣን ቻድን ለመታደግ በተዘረጋው ፕሮጀክት ላይ ተባባሪ በሆነው UNESCO ውስጥ በምክትል ዳይሬክተር ደረጃ ሆነው በአለማቀፉ የአቡጃ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ነበር። አቶ Getachew Engida በዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጓደኛየ ናቸው። አቶ ጌታቸው ተሞክሮዎችን ለአገራቸው ለማጋራትና ድጋፉ የሚገኝበትን መላ በማመላከቱ ረገድ ብሔራዊ ሚናቸው ታሪካዊ እንደሆነ ከአክብሮት ጋር ነው የምጠቅሳቸው።

በመጨረሻም እኔ እንደ ጋዜጠኛ ለጣና ይበጃል ብዬ ከማካፍለው መረጃ በተጨማሪ እምቦጭን ለማስወገድ ወደ ባህርዳር ተጓዝኩ….። የምችለውን ያህል አረም ነቀልኩ። ሌሎችን ለማነሳሳትም ፎቶውን በሶሻል ሚዲያ ለጠፍኩ። የባህርዳር ባለ ሆቴሎችነፃ አልጋና ምግብ አቀረቡልን። የኢትዮጵያ አየር መንገድም በነፃ ትኬት ወደ ሸገር መለሰን። …… ለማለት ያሰብኩት፣ መሠል ሙከራዎች ሸጋ ቢሆኑም የጣናው አደጋ በእንዲህ አይቀረፍም። አስቡት! እኛ ከሰራነው የወጣብን ወጪ ይበልጣል። ጣናን ለመታደግ የምትወጣ እያንዳንዷ ብር ለአረምና ተፋሰስ ለተዘረጋ ፕሮጀክት መዋልና የተዘጋጀው ፈንድም በሀይቁ ዙሪያ ህይወታቸውን ለመሠረቱ እንዲሁም ስራ ለሆኑ ዜጎች የስራና የገቢ ምንጭ ሆነ መቀናጀት አለበት።

Saving_Lake_Tana

Pan_African_Nile_Basin_Global_Concern

Pm_Abiy_Ahmed

ministry_of_water_electric_irrigation

vice_pm_demeke_mekkonen

Ref.
https://www.pambazuka.org/human-security/saving-lake-chad-pan-african-project
_

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) – GeraGetachew Befekadu Abay Teshager Tassew Aklilu Habtewold Alazar Terefe Mersha Henok Fekadu Eden Liul Hussen Kedir Anteneh Degefe Tesfaye Hailemariam Tesfaye Getnet Tes Hira Bereket Alebachew Teumelisan Solomon Solomon Nigus Henok Seyoum Habtamu Kassie Taye Bogale Arega Muktarovich Ousmanova Selam Mulugeta ዋልተንጉስ ዘሸገር Raju Mohammed Teddy Kassa Belay Bekele Weya Bisrat Aklilu Bisrat Mengistu Dereje Gizaw Dereje Belayneh Halleluya Halleta Chalta Tibebu Belete Nigus Wodajnew Mamuye Natnael Mekonnen Brook Abegaz

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories