የዓባይ:ልጅ ✍️ እስሌማን ዓባይ ➖ Twitter: Esleman abay Facebook: Esleman Abay
የትግራዋይ ኢትዮጵያዊ ጀግንነት ሚዛን፣ የአንድነታችን ማገር፤ ዘመኑን ሙሉ ለኢትዮጵያ ክብር ሲዋደቅ የኖረ፤ ዕንደ ዕንቁ የከበረ የኢትዮጵያ ልጅ፣ ባለውለታችን– “..ዶጋሊ ላይ ዶጋመድ አረጋቸው..” በሚል ገለፃ የታሪክ መምህራችን ጋሽ አዛዥ [ዳሞት ት/ቤት፣ ፍኖተ ሰላም] ያስተማሩን አይረሳኝም፤ ለጓደኞቼም አይረሴ ነው..።
በፈረንጆቹ 1887፣ በቶማስ ዲ. ክርስቶፎር የተመራውን የኢጣሊያን 500 እግረኛ ጦር ለመፋለም 7000 የኢትዮጵያ እግረኛ ጦርን እየመሩ ወደ ዶጋሊ አውደ ውጊያ ዘመቱ – ራስ አሉላ እንግዳ (አሉላ አባነጋ)— ድንበራችንን ጥሰው የገቡ የጣሊያን ወራሪዎችን #ዶጋሊላይዶግአመድአደረጋቸው ~ ጣሊያን ያዘመተቻቸው 500 ወታደሮችን ደመሰሱ ~ 420ዎቹ የጣሊያን ወታደሮች ሲገደሉ የቀሩት 80ዎቹ ቆስለው ተማረኩ።
ጣሊያን░ሰሐጢ░ላይ░እግሩን░ቢዘረጋ፣
አንገብግቦ░ቆላው░አሉላ░አባነጋ፡፡
ይህ ሽንፈት ከፍተኛ ሕዝባዊ ቁጣ የቀሰቀሰባት ጣልያን በውጊያው ለተገደሉት ወታደሮቿ ሮም በሚገኝ Piazza dei Cinquecento በተባለ አደባባይ የመታሰቢያ ሐውልት ለማቆም ተገዳለች፡፡
ኢጣሊያ ሮም ላይ ካቆመችው ሃውልት በተጨማሪ ዶጋሊ በተባለውና ዛሬ ኤርትራ ውስጥ በሚገኘው ስፍራ ላይም ለሞቱት ወታደሮቿ ሌላ ሃውልት ገንብታ ነበር፡፡
ያ’ሉላ░ፈረስ░የረገጣቸው፣ እስካሁን░ድረስ░አለ░ቁስላቸዉ።
የአሉላ░ፈረስ░ተስቦ░ወርዶ፣
ያንን░ነጭ░ገብስ░አረገዉ░ነዶ።
የዶጋሊ ድል የአሉላ አባ ነጋን ዝና ከጣሊያን ባሻገር መላው አውሮፓ በፍርሃት እንዲርድ ያደረገ ነበር። የኢትዮጲያን ስም በዓለም ዙሪያ በጀግንነት እንዲነሳ ያደረገ ሲሆን ለአድዋው ጦርነት መነሻም የመጀመሪያ ምዕራፍ መሆኑ ይገለፃል።
አሉላ░አባነጋ░ካስመራ░ቢነሳ፣ ቢቸግረው░ጣሊያን░አለ░ፎርሳ░ፎርሳ።
አፄ ዮሐንስ በውስጥ ፖለቲካዊ ስራ ላይ በነበሩበት ጊዜ ቱርኮች ምፅዋን መያዛቸውን ሰሙ፤ ለራስ አሉላም እንዲህ ሲሉ ላኩባቸው፤ “እኔ እስክመጣ ድረስ ተጨማሪ ቦታ እንዳይዙ ነቅታችሁ ተጠባበቁ” የሚል..፡፡
ዮሐንስ░መብቱን░ላሉላ░ቢሰጠው፣
እንደቀትር░እሳት░ቱርክን░ገላመጠው፣
ጣልያንም░ወደቀ░እያንቀጠቀጠው፣
አጭዶና░ከምሮ░እንደገብስ░አሰጣው፡፡
“..መጥቼ እስክንዋጋቸው ድረስ በንቃት ጠብቁ..” የሚለው የአፄ ዮሐንስ መመሪያ የደረሳቸው ራስ አሉላ “ለጌታ ድግስ እንጂ ጦር አያቆዩትም!” በማለት ራሳቸው የሚመሩትን ጦር መርተው ትልቅ ጦርነት አደረጉና ድል አደረጉ፡፡
አሉላ░አባነጋ░የደጋ░ላይ░ኮሶ፣ በጥላው░ያደክማል░እንኳንስ░ተቀምሶ፡፡
ጀግናው አሉላ ከወራሪ ጋር ያደረጓቸውን ስምንት አውደ ውጊያዎች በድል ደምድመዋል:
⏹|ዘመናቱ ፈረንጅኛ ናቸው⤵️
▪️ጉንደት – ግብፅ+ኦቶማን – 1875
▪️ጉራዕ – ኦቶማን+ግብፅ – 1876
▪️አይለት- 1887
▪️ሰሃጢ -1880
▪️ኩፊት – መሀዲስት/ሱዳን – 1885
▪️ጋላባት /መተማ – 1889
▪️ሰሀጢ – ጣሊያን – 1887
▪️ዶጋሊ – 1887
▪️ዐምባላጄ – 1889
▪️መቐለ እና ዓድዋ – 1896
ራስ አሉላ አባ ነጋ በአፄ ዮሐንስ ዘመን ሐማሴንንና አካባቢውን ለረጅም አመታት አስተዳድረዋል፡፡
የመሃንዲስቶችን፣ የግብፆችን፣ የጣሊያኖችና የኦቶማኖችን ተደጋጋሚ የወረራ ጦርነት ድል ያደረጉት ጀግናው ራስ አሉላ ከንጉሠ-ነገስቱና ከመላው ህዝብ ትልቅ ከበሬታና ተደናቂነትን ሲያስገኝላቸው፤ ሀገሩ ኢትዮጵያን ጀግንነትም በአለም ዙሪያ በተለይም በምድረ አውሮፓ እንዲታወቅ ያደረጉ ባለውለታችን ናቸው፡፡
ዶጋሊ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ ቦታ ሲሆን፤ የደርግ መንግስት #የዶጋሊድልበዓል ሕዝባዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር እና ዶጋሊ ላይ የመታሰቢያ ሀውልት እንዲቆም አድርጎም ነበር፡፡ ጣሊያኖችም በጦርነቱ ለተሰዉ ወታደሮቻቸው ሮም ላይ የመታሰቢያ ኀውልት አቁመውላቸዋል፡፡
⏹ እስሌማን ዓባይ #የዓባይልጅ
#Yes_We_Blacks_Can