ጋዜጠኛውና የአስመራው መፈንቅለ-መንግስት

1981 ላይ ነው። በአስመራ መፈንቅለ መንግስት በተሞከረበት ወቅት። ጋዜጠኛ መስፍን ዘለቀ ስቱዲዮ ውስጥ ነው። ክላሽ የደቀነ ታጣቂ አፈሙዙን በጭንቅላቱ ላይ ደቅኖ ይህንን በል አለው፤ መስፍንም አለ።
“ሰው በላውና ጨካኙ የደርግ ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተደመሰሰ”
…መፈንቅለ መንግስቱ ከከቸፈ በኋላ…..

ወዲያውኑ የመንግስት(ደርግ) ወታደር በመስፍን ጭንቅላት ላይ ሌላ የክላሽ አፈሙስ አስደግፎ ደቅነው “የምልህን አስተላልፍ” አለው።

“ወንበዴውና ባንዳው በአስመራ ያደረገው መፈንቅለ-መንግስት በጀግናው ሰራዊት ከችፏል”
……. ………………..
መስፍን ዘለቀ የረጂም ዓመት ልምድ ያካበተ ጋዜጠኛ ነው። በአዲስ ዘመ፣ አማራ ሬዲዮና የኢትዮጵያ ራዲዮ ለረጂም አመታት አገልግሏል። ከተስፋየ ገብረአብና ሱሌማን ደደፎ ጋርም ባልደረባ የነበረባቸው አመታት ነበሩ። ከብርሃኑ ገብረማርያም፣ ዳሪዎስ ሞዲ፣ አለምነህ ዋሴ እና ሌሎች ጎምቱዎች ጋር ባልደረባና ወዳጅ ነው። አሁን በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (የቀድሞው አዲስ ቴቪ Addis TV ) እያገለገለ ይገኛል። አባቱ ኮሎኔል ናቸው፤ ኮሎኔል ዘለቀ። ልጅም የአባቱን ተክለ ቁመና ከሙያዊ ዲስፕሊኑ ጋር ወርሷል።

ለአማራ ራዲዮ ይሰራ በነበረበት ወቅት ይጠቀሙት የነበረው መቅረፀ-ድምፅ National የሚባለውን ግብዳ ቴፕ ነበር። ናሽናል ቴፑን በእጁ ይዞ የጋራ ቃለ መጠይቅ ሲቀርፅ የቢቢሲና ሌሎችም የአለማቀፍ ሚዲያ ዘጋቢዎች የነ መስፍንን መቅረጫ ቴፕ አብረው ያካትቱ ነበር” ሲል በመገረም ያወሳልናል።
በአስመራ የከቸፈውን መፈንቅለ መንግስት መግለጫ በማንበቡ ተይዞ ወደ ኮሎኔል መንግስቱ ቢሮ ተወስዶ ነበር። “ተረሸንኩኝ ብዬ ደምድሜ ነበር፤ በይቅርታ ሲያልፉኝ እውነት አልመሰለኝም ነበር” እያለ አጫውቶናል። መስፍን ዘለቀ ጨዋታና ወግ የማያልቅበት፤ ተግባቢ አዝናኝ ተወዳጅ ሰው ነው። በቀልዶቹ ብዙ ስቀናል፤ ተዝናንተናል። አልረሳውም።
ረጂም ዕድሜና ጤና ለመስፍኔ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories