ዓባይ ከግብፅ ተርፎ የውጭ ኢንቨስተሮችም በቀላሉ እንዲሸምቱት እየተደረገ ይገኛል። ለአብነትም ሁለት የባህረ-ሰላጤው አገራት ብቻ ከቶሽካ ፕሮጀክት ግማሹን ማለትም 29 ሺህ ፌዳን ገዝተዋል። ውሃ ያንሰኛል የምትለው ካይሮ ችግሯ ውሃ አለመሆኑን ዓባይን በርካሽ ወደ ውጭ አሳልፋ ከምትነግድበት አሳዛኝ ዋጋ ብቻ መታዘብ ይቻላል።
ፕሮፌሰር ገማል ሰያም፣ በካይሮ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኢኮኖሚ ፕሮፌሰር ናቸው። በ 2014 የግብፅ ማዕከላዊ ኦዲተር ያወጣውን መረጃ መሰረት አድርገው 210 ሚ. ኪዮቢክ የናይል ውሃ ለሁለቱ አገሮች ለተሸጠው 29 ሺህ ፌዳን መሬት ማልሚያ ይውላል። በወቅቱ በነበረው የ 1 ሜትሪክ ኩብ ዋጋ (0.12 ሣ.) ዶላር፣ ተሰልቶ 24.3 ሚሊዮን ዶላር የሚያስከፍል ነው (ምንም እንኳን አል-ሲሲ የዓባይ ውሃን የህይወት መሰረት ሳይሆን እንደ ርካሽ ሸቀጥ እንደጠላት ገንዘብ በመቁጠር አሊያም ስትራቴጂክ አጋር ለማፍራት ከወቅቱ የውሃ አለማቀፍ አማካይ ከ20 እጥፍ ባነሰ ዋጋ በ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ብቻ በሆነ ገንዘብ ነው ያድፋፋችው)። እንደ መረጃም፡
▪️የግብፅ overall GDP ባለፈው አመት 1.38 ትሪሊዮን ዶላር ነው።
▪️በተመሳሳይ አመት ግብፅ የነበራት Nominal GDP 409 ቢሊዮን ዶላር ነው።
ምንጭ፡- World Bank Report, 2021
▪️በግብፅ ከተፈጠሩ የስራ እድሎች 25 በመቶው በእርሻው ዘርፍ ላይ የተገኘ ነው። ▪️የግብፅ ኢኮኖሚ 12 በመቶው የግብርናው ድርሻ ነው።
▪️ለግብፅ ግብርና ጥቅም ላይ ከሚውለው ውሃ 98 በመቶ ውሃ ከዓባይ የሚገኘው ነው። ▪️ግብፅ ከምታገኘው የናይል ውሃ መጠን 88 በመቶው ከኢትዮጵያ የሚሄድላት መሆኑ ይታወቃል።
ይህም ማለት ከኢትዮጵያ የሚሄድላት የዓባይ ከግብፅ(የ 2021) overall GDP 350 ቢሊዮን ዶላሩ፤ እንዲሁም ከግብፅ Nominal GDP 102 ቢሊዮን ዶላሩ በዓባይ ውሃ ላይ የተመሰረተ ሆኖ እናገኘዋለን።
በግብፃዊው ፕሮፌሰር ገማል ሰያም መረጃዎች መሰረት እንቀጥል። ግብፅ ከምታገኘው 55 ቢሊዮን ውሃ 88 በመቶው ከኢትዮጵያ ነው። ለቀቅ አድርገንላቸው 54 ቢሊዮን BCM በያመቱ ከኢትዮጵያ አገኙ እንበል። በካይሮው ፕሮፌሰር ስሌት መሰረት 1 ሜ/ኩ በ 0.12 ሳንቲም $ እናስላው። ይኸውም 7 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ነው። ይህ የምንዛሪ ግኝት መጠን ኢትዮጵያ በ 2017 ከወርቅ፣ ከቆዳ፣ የቅባት እህል ቡና ወዘተ በሙሉ ኤክስፖርት አድርገን ያገኘነውን ምንዛሪ ሁለት እጥፍ ያህል ነው።
ባሳለፍነው የበጀት አመት (2020/2021) ከወጭ ንግድ ኢትዮጵያ ማግኘት የቻለችው 3.6 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን በዘንድሮው የስምንት ወራት ከተገኘው 2.52 ቢሊዮን ዶላር ስሌት የአመቱ ግኝት 3.8 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ነው።
ዓባይን አሳልፋ የምትሰጠው ግብፅ የሽያጩ አለም አቀፍ ዋጋ ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ሀገራዊ የወጭ ንግድ ግኝት እጥፍ መሆኑ ነው። ይህ በናይል ከሚለማው ግብርናዋ የምታገኘውን ገንዘብ ሳይጨምር ነው። የተጠቀሰው የካይሮ ምንዛሪ ግኝት ለሁለት የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ብቻ በቅርብ አመታት ባደረገችው የእርሻ ኢንቨስትመንነት ስምምነት ወዲህ ብቻ የምትቃርመው ነው።
ግብፃዊ ልሂቃን ውለታን እና ባለውለታን መካድ ከፈርኦን የተጣባቸው ተውሳክ ነው መሰል ሸለምጥማጣዊ አካሄዳቸውን ላይቃና የዘመናት ማገዶ ፈጅቷል። ለበጎ ነው። ለዘመናት የተሰነዘረብንን ፈተና ተሞክሮ ከወሰድንበት መጪው ዘመን ለመጪው ትውልድ የተመቸ ይሆን ዘንድ መስፈንጠሪያም መደላድልም ይሆነናል።
ግን ግን፣ የግድባችንን ግንባታ ማለቅ በተስፋ ስንጠብቅ የኛው በኛው ፍቅር ቀድሞ እንዳያልቅ ሌላ የሀገራዊ መስተዋድድ ፕሮጀክት ሊያስፈልገን ይሆን?
Esleman Abay #የዓባይልጅ
read more research articles below
1 thought on “ግብፅ ለሌላ የምትሸጠው የኛ ዓባይ ሥንት ነው?”
እውነትም የአባይ ልጅ!!!
ጥረትህን በጣም ነው የማደንቀው።
መረጃዎችህ ከተጠቀመበት ለሀገራችን መንግስት ትልቅ ግብአት ነው።
በርታ!!!