ፀረ- ጎልያዱ ዘመቻ በቪላዲሚር ቪላዲሚሮቪች ፑቲን


እስሌማን ዓባይ

የሩሲያ ዘመቻ በዩክሬይን ከተጀመረ ወዲህ አሜሪካ የ4 እና የ40 በድምሩ 44 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለዩክሬይን አቅርባለች። ይሁንና የዩክሬይን ምስራቃዊ ክፍል(ወደቦችን እጅግ ጠቃሚ የኢኮኖሚ ማእከላት) በሩሲያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከመዋል ሊተርፉላት አልቻሉም። ምእራባዊያን ይህን ርምጃ በዝምታ/በአማራጭ የለሽነት አልፈውታል።

ቻይና 4 ሀገር ሻጭ ባንዳዎች ላይ ርምጃ ወሰደች በሚለው እንጀምር። ቀጥለንም አንኳር አለማቀፍ ሁነቶችን እንቃኛለን። የመራረጥኳቸው ድርጊቶችና ሁነቶቹ የምእራባዊው ዘመነ-ጎልያድ ማብቃቱን ሲያስረግጡ በድል መነፅር ስናያቸው ደግሞ ዋጋቸው ከሞስኮ ባሻገርም ትርጉም ያላቸው ናቸው። ይህ ይመጣ ዘንድ በተለይም በሩሲያ የተከፈለ ዋጋ ቢኖርም በድል መነፅር ሲመዘን ግን ከሞስኮም ባሻገር ትልቅ አንድምታና ዋጋ ያለው ነው።
የፑቲኗ ሞስኮ ድል ተቀዳጀች ማለት ቻይናን ይዞ እስከ ህንድ ብሎም ለሰፊው እስያ የማሸነፍ ዱላ ቅብብሎሽ ስለመሆኑ በርካቶች ይስማሙበታል። በላቲን አሜሪካ በስፋት እንዲሁም በአውሮፓ በከፊል የዚሁ ድል አጋሮች መኖራቸው የሚታወቅ ነው። ለአፍሪካ በተለይም ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ደግሞ አንድምታው የተለየ ነው።(ከባንዳ በስተቀር)
ወደ ቻይናዊ ባንዳዎች ጉዳይ እንመለስ፤ ርምጃ የተወሰደባቸው አራት ቻይናዊያን የሀገሪቱ ወታደራዊ ጀነራሎች ነበሩ። ከሳምነት በፊት ግን አስገራሚው ክስተት ተፈፀመ። የቻይና መንግስት ከወታደራዊ አመራሮች ጋር ልዩ ስብሰባ ለማድረግ በሀገሪቱ የሚገኝ አንድ የባህር ዳርቻን መገናኛው እንዲሆን አዘዘ። እጅግ ጥብቅ ሚስጥር ነበር በተባለው የስብሰባ አጀንዳ ላይ የተደረጉ ንግግሮች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን በአለም ዙሪያ ያዳረሰው ልክ ስብሰባው ከማለቁ ከአፍታ ብቻ ቆይታ በኋላ ነበር። “በቅርቡ ታይዋን ወደ ነባር የቻይና አስተዳደር የምትቀላቀልበት ዘመቻ ይጀመራል።” በምስጢራዊው ስብሰባ ላይ ተቀድቶ ከወጣው ድምፅ መካከል ነበር….ይህ የሆነው ከጄኔራሎቹ መካከል በሆኑ ሰዎች መሆኑን ቤይጂንግ አላጣችውም። ከቀናት በኋላም አራቱን ጄኔራሎች በስቅላት መቅጣቷ ተሰማ። ዘገባውን ደግሞ በአሜሪካ የምትገኝ ትውልደ ቻይናዊ ጋዜጠኛ ናት ያስነበበችው።

ፕሬዝደንት ጆ. ባይደን የሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻ የአሜሪካን ኢኮኖሚ በከፍተኛ መጠን ስለመጉዳቱ እንዲሁም በአሜሪካዊያን ኪስ ላይ ከባድ ችግር መፍጠሩን አመኑ- በትላንትናው አለት የተሰማ ዘገባ ነው።
ኒውዮርክ ታይምስ ደግሞ የሩሲያ ኢኮኖሚ/ሩብል የምእራባዊያን ማእቀብ ሳይገድበው ማደጉን ቀጥሏል። የአሜሪካ ኢኮኖሚ በዚሁ ሳቢያ ጉዳት ገጥሞታል።” ሲል ነው በማስከተል ያስነበበው።
አሜሪካ በአለማቀፍ ሁኔታዎች ላይ ያላት የመወሰን አቅም ከዋሽንግተን እጅ መውጣቱን ፕሬዝደንት ባይደን ያመላከቱትም በያዝነው ሳምንት ከአንድ ቀን በፊት ነው። ባይደን ባደረጉት ንግግር “ሌሎች የአለማችን ብርቱ ሀገራት በአለማቀፍ ጉዳዮች ላይ እያሳረፉት የሚገኘው ጫና ዋሽንግተን ቀደም ባሉ ዘመናት የልቧ መሻት ሁሉ ተፈፃሚ የሚደረግበትን ዘመን ያለፈ ይሆን ዘንድ ግድ አድርጎታል።” የሚል ነው።
ባይደን የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ጋር የዲፕሎማሲ ንቃቃቱን ለመጠገን ባለፉት ሰባት አስርት አመታት በአሜሪካ ፖሊሲ ያልተለመደውን መለማመጥ ያሳዩትም ባለፉት ቀናት ሲሆን ባለፈው ሳምንት ወደ ሪያድ ሊያመሩ መሆናቸውን የገለፁት ባይደን ይኸው ጉዞ ስለመራዘሙ የተነገረውም በተከታይ ቀን ነበር-ምክንያቱን ማሳወቅ የፈለገ አካል ባይኖርም።
በትላንትናው አለት ደግሞ ከአልጋ ወራሽ ቢንሰልማን የመረረ እምቢተኝነት የገጠማለው ባይደን በአባትዬው በኩል ሪያድን ይጎበኙ ዘንድ እቅድ መያዛቸውን አሜሪካ የገለፀቸው የሰቀቀን ሀሴት የሞላባቸው ቃላትን በመጠቀም ጭምር ነው። በያዝነው ወር መጨረሻ የታቀደው የባይደን የሳኡዲ ጉዞ ገቢራዊ መሆን አለመሆኑን የሚያስተማምን አሁናዊ ተጨባጥ ባይኖርም የባይደን አስተደዳደር ግን ደስታውን መደበቅ አልተቻለውም። የአሜሪካ መንግስት ፅህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ የሳኡዲ መንግስትን በእጅጉ ያመሰገነ ሲሆን በተለይም “የንጉስ ሰልማን የበሰለ አመራር በአሜሪካ የሚደነቅ ነው።” የሚለው ሀረግ ተካቶበት ይገኛል።
ጆ. ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የሳኡዲ ንጉሳዊ አስተዳደርን አምርረው ሲያወግዙ ነው የሚታወቁት። ከሪያድ መሪዎች ጋር የመነጋገር ፍላጎታቸውም ሆነ የሰጧቸው ክብደት እጅጉን የወረደ ነበር። በተለይም የሳኡዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሙሀመድ ቢን ሠልማን ከአሜሪካ የገጠማቸውን ዲፕሎማሲያዊ መገለል ከሌሎች ቀውሶቻቸው ጋር ተደማምሮ ለወራት ከብዙሃን መገናኛዎች ጠፍተው ሲቆዩ ተስተውሏል። አንዳንዶችም “ድባቴ” ላይ ናቸው ሲሉ ሁኔታውን ይገልፁት ነበር። ያው “pariah” አድርገውት ነበር። ልክ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ላይም አድርገውት እምደነበረው። አብይን “from reformist to pariah” ነበር ያሉት። አሁን ላይ ለቢን ሰልማን እያሳዩት የሚገኘው ልምምጥ ደግሞ “from pariah to a worthy partner” ልንለው እንችላለን።
ዛሬ ከሰአት ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ለምእራባዊያን ስንዴ አልሸጥም ሲሉ ተደምጠዋል። ምእራባዊያን ቃል የገቡትን ዘመናዊ መሳሪያ ካላቀረቡልኝ ከዩክሬይን ወደብ የሚሄድላቸው ስንዴ አይኖርም።” ያሉት ዘለንስኪ አሁን ላይ ዩክሬይን የባህር በር የሌላት በሚባል ደረጃ ልትጠቀምበት የምትችለው ወደብ የላትም።

አሁን ከመሼ በወጡ ዘገባዎች ደግሞ  ባይደን የ1 ቢሊዮን ዶላር መሳሪያ ድጋፍ ለዩክሬይን እናቀርባለን ብለዋል። የሩሲያ ዘመቻ በዩክሬይን ከተጀመረ ወዲህ አሜሪካ የ4 እና የ40 በድምሩ 44 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለዩክሬይን አቅርባለች። ይሁንና የዩክሬይን ምስራቃዊ ክፍል(ወደቦችን እጅግ ጠቃሚ የኢኮኖሚ ማእከላት) በሩሲያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከመዋል ሊተርፉላት አልቻሉም። ምእራባዊያን ይህን ርምጃ በዝምታ/በአማራጭ የለሽነት አልፈውታል።

በሺዎች ማእቀብ የተጣለበት የራሺያ ኢኮኖሚ አንፃራዊ ጠቀሜታ እያገኘ ነው። ጦርነቱ ከሀጀመረ ወዲህ ብቻ ሩብል ከዶላር በተቃራኒው የ40 በመቶ እድገትን አስመዝግቧል። ጦርነቱ ያስከተለው የሃይል አቅርቦት ማነስና የዋጋ መናር በአውሮፓ ፋብሪካዎች እንዲዘጉ ምክንያት መሆን ጀምሯል። በተያያዘም “ጭራሮ ለቅማችሁ ቤታችሁን ማሞቅ ትችላላችሁ” የተባሉ አውሮፓዊያንም አሉ።

ቪላዲሚር ቪላዲሚሮቪች ፑቲን ምርጫ አልባውን ወታደራዊ ኦፕሬሽን በዩክሬይን ሲጀምሩ ምእራባዊያን ስለ ራሺያው ፕሬዝደንት ያልተጠቀሙት የፕሮፓጋንዳ አይነት የለም ማለት ይቻላል። እንደውዊው አዳዲስ የፕሮፓጋንዳ ፈጠራዎችንናን ሞክረዋል ለማለት ጭምር ያስደፍራል። ፑቲን የአይምሮ መቃወስ እንደገጠማቸው፣ የጦርነቱ ካልኩሌሽናቸው ፉርሽ ስለመሆኑ፤ የሩሲያ ኢኮኖሚ ሽባ ስለመሆኑ ፑቲን በህይወት እንደሌሉ(ስለመሞታቸው) ወዘተ ወዘተ …. በተጨባጭ የሆነው ግን ተቃራኒው ነው።
ይህን ተአትሎም ቻይና ለሩሲያ የምታሳየውን ድጋፍ ከሌላው ጊዜ በተለየ መግለፅ ጀምራለች። የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ፣ “በህንነትና ሉአላዊነት ጉዳዮች ቤይጂንግ ከሞስኮ ጋር ሁለገብ ትብብር ታደርጋለች።” የሚለው ላይ በተለየ ልናሰምርበት እንችላለን። ያው ነገረ ታይዋን የተሰኘ ሌላ አለማቀፍ ፖለቲካዊ/ወታደራዊ ትያትር በደቡብ ቻይና ቀጣና ተጠባቂ ነውና።

#የዓባይልጅ Esleman Abay

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories