░የ░ካ░ይ░ሮ░ ░ሸ░ለ░ም░ጥ░ማ░ጦ░ች░ ░በ░ም░ስ░ራ░ቅ░ ░አ░ፍ░ሪ░ካ░

【 የግብፅ የስለላ መስሪያ-ቤት የምስራቅ-አፍሪካ
  ሰሞንኛ እንቅስቃሴና ኢትዮጵያ first published in july 2020 】

የግብፅ ደህንነት ሀላፊ አባስ ካመል ማክሰኞ ዕለት ካርቱም ነበሩ። ከሶስት ወር በፊት ደግሞ ጁባ ደቡብ ሱዳን ተገኝተው ነበር። ባለፈው ሳምንት ደግሞ የግብፅ ልዑክ ሶማሊላንድ ተጉዟል። የካይሮ ከወትሮው የተለየ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን መረጋገጥ ከህዳሴ ግድቡ ጋር የተያያዘ ውይይት እንደተደረገበት ተዘግቧል። ልብ በሉ! ይህን እያደረጉ ያሉት ፕሬዘደንት አል-ሲሲ ‘የህዳሴ ግድቡን ጉዳይ በትብብር እንጅ በሀይል አይደለም መፍትሄ የምናመጣው’ ባሉበት ሳምንት ነው።

የካይሮ የስለላ ተቋም በግድቡ ድርድር ላይ የሚያራምደው አጀንዳ የተንኮል ስለመሆኑ በርካቶችን ያስማማል። ስለ ካይሮ ስለላ ካነሳን አይቀር ከአምስት አመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዙ ግብፃዊ ሸለምጥማጦችን እናስታውስ።
ሜይ 5 ፣ 2014 ላይ ሶስት ግብፃዊ ሰላዮች በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሦስቱ ግብፃውያን በኢትዮጵያ የግድብ ስርዓት ላይ የደህንነት መረጃዎችን ለመሰብሰብ ሲንቀሳቀሱ አንዱ በአቦቦ ግድብ አቅራቢያ የተያዘ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ወደ ህዳሴ ግድቡ ለማምራት ሲሞክሩ ነበር፡፡

በተያያዘ መረጃ ደግሞ እንግሊዝ የግብፅ የስለላ ሰዎችን ስልጠና መስጠት መጀመሯ የተዘገበው ከወራት በፊት ነው። የአባይን ጉዳይ ከግብፅ ጋር አስተሳስራ ለጥቅሟ ለመማዋል የረጂም ዘመን ሴራ ያከናወነችው እንግሊዝ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከግብፅና ከተባበሩት አረብ ኢምሬት የተውጣጡ ሰላዮችን ነው ያሰለጠነችው። በ MI6 የተሠጠው ስልጠናው በብሪፎርድሻየር በሚገኘው የጦር ሰፈር ነው የተካሄደው። በከፍተኛ ሁኔታ የተመረጡ የስለላ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ስልጠናው በመገናኛ ብዙኃን ሚና፣ የደህንነት ፖሊሲና የስለላ መረጃ ልውውጥ ላይ ስለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ወዘተ… ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን የሸፈነ ነበር፡፡ በቅርቡ ማለትም በወርሀ ሰኔ ደግሞ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የፓርላማ አባል ሆነው ሲያገለግሉ 2002 ላይ ያስነበቡት አቋማቸው ይፋ ሆኖ ነበር። እሳቸው እንደፃፉትም “በአፍሪካ የሚከሰቱ ችግሮች የብሪታንያ ጥፋት አይደለም። ችግሩ እኛ ቅኝ ገዢ ከመሆናችን የመነጨ ሳይሆን፣ እንደውም እኛ ከቅኚ ገዢነት መራቃችን ነው ምክንያት ሊሆን የሚችለው” ብለዋል። ዛሬ እሳቸው መሪ መሆናቸው ታዲያ ነባሩ የቅኚ ገዢዎች ሴራ እንዲያንሰራራ ለማድረግ ምኞቱ የማይቀር መሆኑን ያስገነዝባል።

ሌላው ደግሞ የሱማሌላንዱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ቱርክ ለጉብኝት የመጓዛቸው መረጃ ነው። ምኒስትሩ ከቱርኩ አቻቸው ጋር በቅርቡ በጅቡቲ ስለተካሄደው የሱማሊላንድና ሶማሊያ ዕርቅ ላይ ይወያያሉ ሲል የዘገበው ሶማሊላንድ ስታንዳርድ ነው፡፡ የሚንስትሩ የቱርክ ጉዞ “ግብጽ በሱማሌላንድ ወታደራዊ ጦር ሠፈር ለማቋቋም ከቀናት በፊት በላከችው ልዑክ በኩል ጥያቄ ማቅረቧ በተሰማበት ሰሞን ነው።

በ 2019 ከወጣው ሪፖርት ደግሞ ግብፅ ዩጋንዳን ከደቡብ ሱዳን ጋር በማቀራረብ በህዳሴ ግድቡ ላይ እያሴረች ነው የሚለውን እናስታውስ። አገራቱ ቢያስተባብሉትም። በርግጥ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ በግልፅ ደግፈው ተናግረዋል። ሌላው ቀርቶ ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን የሀይል አማራጭ ጩኸት ተችተዋል።
“ማንም አፍሪካዊ አገር ግብፅን ለመጉዳት አይፈልግም… ሆኖም ግን ግብፅ ጥቁር አፍሪካዊ አገራትን መጉዳት የምትችልበት መንገድ መኖር የለበትም” ብለዋል።

ባጠቃላይም አል-ሲሲ ከሰሞኑ የተናገሩት የማዘናጋት የሚመስለው ‘ቅቤ’ ንግግራቸው የኢትዮጵያን ቀጠናዊ ምልከታ ችላ ማስባል የለበትም። እንደውም “ለምን?” እና “እንዴት!” የሚያስብል መሆን ያለበት ነው። ከዚህ ጋር በሚዛመድ ጉዳይ ላይ ግብፃዊው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና የ african studies ስፔሻሊስት ዶክተር Badr Hassan Shafei ከአመት በፊት ባስነበቡት “Egypt between Horn of Africa” በሚለው ፅሁፋቸውም ግብፅ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር በጥቅም በመተሳሰር የህዳሴ ግድቡ ድርድር ላይ ጫና ለማሳደር ወሳኝ ስትራቴጂዋ መሆኑን አልደበቁም። “Egypt’s role in the Horn of Africa” በሚለው ንዑስ የፅሁፋቸው ክፍልም ግብፅ የበፊቷ የሴራ አጋሯ የነበረችውን ኤርትራን በጠ.ምኒስትር አብይ መነጠቋን ይጠቅስና የሚቀራት አማራጭ በኢትዮጵያ ብሔር ግጭቶች ውስጥ እጇን መክተት ስለመሆኑም ጠቁሟል።
….”Egypt’s loss of one of the most important pressure cards on Ethiopia, i.e. Eritrea. (According to the Ethiopian narrative, Egypt used to provide support to the Oromo Front. …..Cairo practiced pressures on Addis Ababa in pressuring it to accept its demands regarding the GERD…”

የቀጠናው አገራትን መሳሪያ እንደምታደርግም ዶክተሩ ገልፀዋል።
“within the countries of the Horn of Africa” ​​or even the inter-developments, where Egypt has taken certain positions with respect to these developments in the light of its various strategic interests…..

ለነዚህ ተግዳሮቶች በምሁራን የተሰነዘሩ ምክረ-ሐሳቦችን ለመዳሰስ ያገላበጥኳቸው ድርሳናት የሚመክሩትም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ላይ ትብብርን በማምጣት አገራቱን አጋር ማድረግ እንዳለባት ነው። ፕሮፌሠር መስፍን “አደጋ ያንዣበበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና” በሚለው መፅሀፋቸው ላይም ስለዚህ ጉዳይ ያስቀመጡትም፣ ኢትዮጵያ ነባሩን ጣልቃ የመግባት ተግባር አቁማ በልማት መተሳሰርና ወዳጅ ማድረግ ነው የሚል ምክር ነው። በዚህ ረገድ ከ 2 አመታት ወዲህ ትልቅ ለውጥ መኖሩን በርካታ የ geostrategic ጥናቶች አስቀምጠውት ተመልክቻለሁ። ለአብነት ብንመለከትም ….”Abiy’s political skill and bravery has created an opportunity to set a new course for his country and the wider region. As a trusted ally of Ethiopia, the United States should use his visit to support peacebuilding in the Horn of Africa, strengthen its relationship with Addis Ababa, and reset relations with Eritrea.”
Richard Downie (በ Africa Program at the Center for Strategic and International Studies)

በታዩት ውጤቶችም ለምሳሌ ሶማሊላንድና ሶማሊያን ለማቀራረብ ተችሏል። በቱርክ የተደነቀው ይህ የአቢይ ማሸማገል እያደገ ነው። በቅርቡ ስጋት ደቅኖ የነበረውን የግብፅና ደ.ሱዳን ግንኙነት በተመለከተ በተደረጉ እንቅስቃሴዎችም ጁባ የኢትዮጵያ አጋር እንደሆነችና ከኢትዮጵያ የምታገኘው ጠቀሜታ ከፍተኛ እንደሆነ እንድትገልፅ ሆኗል–ከአነሰገትም ይሁን ከ አነሰጀት። ከቀናት በፊት ከግብፅ ልዑካን ጋር የጦር ሰፈር ስለማቋቋም መከሩ-አልመከሩመሰ ሲያወዛግቡ የነበሩት ሶማሊላንዶች ወደ ቱርክ ሲያቀኑ ምናልባትም የግብፅን ጥያቄ እንዴት እንደምታስተናግደው ልትጠይቅ ሊሆን ይችላል። ቱርክን ላለማስቀየም። ምክንያቱም የዳጎሰ ዶላር ለሀርጌሳ መቁረጥ የጀመረች ናትና። በርግጥ ኤርዶጋን በሜዲትራኒያን ለሚቀናቀናቸው የአል-ሲሲ መንግስት በባብ-ኤል-ማንዴብ ቀጠና ላይ ግብፅ ተፅዕኖ እንዲኖራት የሚደግፍ ይሁንታን ለሶማሊላንድ ትፈቅዳለች ብዬ አላምንም።

የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካዊ ጣጣ ፈንጣጣ እንዲህ በአጭር ተቃኝቶ በውስን ማሳያዎች የሚደመደም አይደለም። ዋናው ጉዳይ ግን ከደቡብ-ሱዳን፣ ሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ሶማሊላንድ፣ ወዘተ… የተጀመረው የትብብርና የጋራ ሠላም ርምጃዎች በተለየ ጥንቃቄ የሚታይበት ወቅት መሆኑ ነው።

ከኢጋድና ሌሎች ቀጠናዊ ድርጅት አባል አገራት ጋር የተጀመሩት አዳዲስ የትብብር መነቃቃቶች ሳዑዲ አረቢያንም መሳብ የቻለ ነበር። በተለይም ጠ.ሚ አቢይ ” a wide-ranging transformative economic and political reform in Ethiopia and እና “regional integration initiative in the Horn of Africa region” የሚሉት ፅሁፎቹ ከሳዑዲው ቢን ሠልማን ጋር በተገናኙበት ወቅት ያቀረቧቸው ናቸው። ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የቀጣናዊ ትስስር ፕሮፖዛል እንደሆነም አለማቀፍ ተንታኞችና ተቋማትም የገለፁት ነበር። መሰል ጅምሮች ወደ ተግባር ቢገቡ ምዕራባዊውን ሚዛን ለአገራችን እንዲያጋድል የበለጠ እድል የሚፈጥር ነው።
ሠላም!❤

https://www.thetrumpet.com/11744-egyptian-spies-captured-while-gathering-intelligence-on-ethiopian-dams
https://marsad-egypt.info/en/2020/07/27/britain-is-training-spies-from-saudi-arabia-egypt-and-the-uae/
https://www.middleeastobserver.org/2018/10/16/egypt-between-horn-of-africa-settlements-renaissance-dam-crisis/
https://www.timesofisrael.com/israeli-firm-traces-cyberattacks-on-egyptian-activists-to-cairo-government/

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories