Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the matomo domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-includes/functions.php on line 6131

Deprecated: mb_convert_encoding(): Handling HTML entities via mbstring is deprecated; use htmlspecialchars, htmlentities, or mb_encode_numericentity/mb_decode_numericentity instead in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/fb-instant-articles/vendor/facebook/facebook-instant-articles-sdk-php/src/Facebook/InstantArticles/Transformer/Transformer.php on line 249

Deprecated: mb_convert_encoding(): Handling HTML entities via mbstring is deprecated; use htmlspecialchars, htmlentities, or mb_encode_numericentity/mb_decode_numericentity instead in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/fb-instant-articles/vendor/facebook/facebook-instant-articles-sdk-php/src/Facebook/InstantArticles/Transformer/Transformer.php on line 249

Deprecated: Creation of dynamic property Facebook\InstantArticles\AMP\AMPHeader::$headerBar is deprecated in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/fb-instant-articles/vendor/facebook/facebook-instant-articles-sdk-extensions-in-php/src/Facebook/InstantArticles/AMP/AMPHeader.php on line 51
ቻይና የናይል ጂኦ-ፖለቲካ ጨዋታ ለዋጭ

Diplomacy ዲፕሎማሲ

ቻይና የናይል ጂኦ-ፖለቲካ ጨዋታ ለዋጭ

By Esleman Abay

August 09, 2021

china changing nile geopolitics

Esleman Abay – የዓባይ ልጅ

ቻይና በናይል ተፋሰስ የምዕራባዊያንን ነባር ጫና በማምከን ሰፊ ተሳትፎ እያደረገች መሆኗ ይታወቃል። ለዘመናት በቅኝ ገዢ ተቋማት IMF እና WORLD BANK ይሁንታና ክልከላ ስር የነበረውን የውሃ ሃብትን የማልማትና ያለማልማት ታሪክ ቤይጂንግ በእጅጉ ለውጣዋለች።

ኡጋንዳ

የኡጋንዳ የሀገሪቱ ትልቁ የሃይድሮ-መሰረተ ልማት ፕሮጀክት ለሆነው የኩራማ ግድብ ከ IMF ብድር ተከልክላ ነበር። ያስከለከለችውም ግብፅ ናት። ነገር ግን ቻይና 1 ቢሊዮን ዶላር አበድራት ግንባታውን በቻይና ኩባንያዎች እንዲገነባ ሆኗል። ለተለያዩ የውሃ ሀይል ማመንጫ ግድቦችም ተጨማሪ 900 ሚሊዮን ዶላር አበድራታለች።

ሱዳን

ሱዳንም ለሜሮይ ግድብ ማስፋፊያ ከአውሮፓዊያንና ሌሎች ለጋሾች የጠየቀችው ብድር ውድቅ ነበር የሆነባት። እዚ ላይም ቻይና የ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ብድር አቀረበችላት። ለሌላ ግድብ ማሳደጊያም 396 ሚሊዮን ዶላር፣ ለ ጀበል ግድብ 705 ሚሊዮን ዶላር፣ 711 ሚሊዮን ለሻሸኪ ግድብ እንዲሁም 838 ሚሊዮን ዶላር ለላይኛው አትባራ ፕሮጀክት አቀረበችላት፡፡

ኢትዮጵያአገራችንን ብንመለከት እ.ኤ.አ. በሚያዚያ 2011 የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ “ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ከመገንባት ልታስቆመን አትችልም፡፡ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድቦች በመገንባት የራሳችንን ሃብት መጠቀም እንችላለንም እንፈልጋለንም” ሲሉ ይፋ አደረጉ…በመቀጠልም የተከዜ፣ ጊልገል ጊቤ 3 እና 4 ፣ ጣና-በለስ፣ ፊንጫ አመርቲ የውሃ ኃይልና የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

ለ IMF እና WORLD BANK ያቀረብነው የብድር ጥያቄ ውድቅ ተደረገ። እነሱ በከለከሉን ማግስት ግን ቻይና “..አታስቡ..” አለችን። የቻይና መንግሥትና የቻይና ዓለም አቀፍ የውሃ እና ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን China International Water and Electricity Corporation በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች መድበው የሃይል ማመንጫዎቹን ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀመሩ። ለተከዜ ፕሮጀክት 365 ሚሊዮን ዶላር፣ ለጊቤ ሦስት 500 ሚሊዮን ዶላር ከአሜሪካ ጠይቀን ብንከለከልም ቻይና ሙሉውን አቀረበች፡፡

የጣና-በለስ የውሃ ኃይል ማመንጫ ካስፈለገው 500 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 85 በመቶው በቻይና ብድር ተሸፈነች። ለህዳሴ ግድቡም በይፋ ያልተነገረ የ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር አሰንደሰጠች ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ላይ ተመልክቻለሁ፡፡ ይኸውም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መሠረተ ልማቶችን ለመዘርጋት በሚል የተሰጠ ነበር።

ይህ የቻይና Game Changer የተባለለት የ Soft Diplomacy አቋማ በለይም ከኢትዮጵያ ጋር ካላት strategic partnership አኳያ ከአሁናዊም ሆነ ለመፃኢ ጫናዎች ሚዛን ማስጠበቂያ ስለመሆኑ አያጠያይቅም።– Esleman Abay የዓባይ ልጅ