እስሌማን ዓባይ የዓባይ ልጅ
…ሩሲያ ፖርት ሱዳን ላይ ከ25 ዓመታት በላይ የሚዘልቅ የባህር ኃይል የማቋቋም ስምምነት ከሱዳን ጋር ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን ..
በሱዳን ከሔሜቲ ፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ጋር ባደረጉት ውጊያ ካርቱምን የለቀቁትና ሀገራትን እየጎበኙ የሚገኙት የወታደራዊ ቡድኑ አመራር አብደልፋታህ አል ቡርሃን በአየርላንድ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ በሚገኘው ሻነን አይሮፕላን ጣቢያ ተገናኝተው የተናጋገሩት አይሮፕላኑ በነዳጅ ማደያው እየቀዳ ባለበት ቅፅበት ነው።
የሱዳን እና የዩክሬን መሪዎች ከኒውዮርኩ የተመድ 78ኛ ጉባኤ በኋላ በነበራቸው በረራ ወቅት ነው ተነጋገሩ የተባለው። የሻነን አየር ማረፊያ (ኤርፎርት ና ሲኦናይኔ) በአየርላንድ፣ ወደ አውሮፓ እና ከአውሮፓ ውጭ ለሚደረጉ የአትላንቲክ በረራዎች ታዋቂ የሆነ የአውሮፕላን ነዳጅ ማደያ ነው።
ዘለንስኪ በኤክስ(የቀድሞው ትዊተር) ገፁ አስተያየት ሲሰጥ ያልታቀደውን ስብሰባ በአይሮፕላን ማደያው ውስጥ ማድረጋቸውን ያረጋገጠ ሲሆን “ሱዳን ለዩክሬን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት የማያቋርጥ ድጋፍ ስላደረገችልኝ አመስጋኝ ነኝ” ሲል ተናግሯል። ዘሌንስኪ ስም ባይጠቅስም ከአል ቡርሃን ጋር በጸጥታ ችግሮችና በሩሲያ የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖችን እንቅስቃሴ በተመለከተ ተወያይተናል” ብሏል። በ78ኛው የቲድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንዲሳተፍ አል ቡርሃንን እንደጋበዘም ተናግሯል።
https://twitter.com/ZelenskyyUa/status/1705546855977787690?t=UxJhnaUjhOqmyS-Dg3mDjg&s=19
የሱዳን – ሩሲያ ግንኙነትበወርሃ ሚያዝያ 2022 እኤአ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ES-11/3፣ ሩሲያ ከዩክሬን የምታደርገውን ውጊያ ከማውገዝ ተቆጥበው ድምጽ ካልሰጡ 58 ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳን ነበረች። ከዚህ በኋላም ካርቱም ከሩሲያ ጋር ያላት ግንኙነት የጠበቀ ሆኖ የመቀጠሉ የሚነገር ሲሆን፤ በያዝነው አመት ወርሃ ሰኔ፣ የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ-መንበር ማሊክ አጋር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀዳሚ ፀሃፊ እና ከሌሎችም ባለስልጣናት ጋር በመሆን ሩሲያን ጎብኝተዋል። የአጋር ልዑካን ቡድን ከሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የሩሲያ ተወካይ ሚካሂል ቦግዳኖቭ ጋር የተወያየ ሲሆን ላቭሮቭ የሩስያ ፌደሬሽን ከሱዳን መንግስት እና ህዝብ ጋር ያላትን አጋርነት እንዲሁም ለሱዳን ህጋዊ ተቋማት ያላቸውን ድጋፍ መግለፃቸው ይታወሳል።
ሩሲያ ፖርት ሱዳን ላይ 25 ዓመታትና በላይ የሚዘልቅ የባህር ኃይል ለማቋቋም በ2020 እኤአ ሱዳን ጋር ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን፣ በዚህም ሩሲያ ቀይ ባህር ላይ የኒዩክለር ተሸካሚዎችን ጨምሮ 4 ያህል የባህር ሃይል መርከቦችን እንድታሰፍር ያስችላል።