Horn Affairs አፍሪካ ቀንድ

አብደላ ሐምዶክ የመንግስታቱ ድርጅትን በመርሆ ጥሰት ድርጊቱ አወገዙ

By Esleman Abay

September 25, 2023

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

ከሱዳን ሕጋዊ የሲቪል መንግስት መሪነት በአል ቡርሐን መራሽ መፈንቅለ መንግስት የተወገዱት ሐምዶክ ተመድ የራሱን መርህ እና አቋም የጣሰበትን ርምጃ ለፅህፈት ቤቱ ባደረሱት ደብዳቤ ኮንነዋል

የቀድሞው ጠ/ሚ አብደላ ሐምዶክ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የላኩት ደብዳቤ፣ [እኛ] ከዚህ ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው በ2019 ሕገ መንግሥታዊ ሰነድ መሠረት የተቋቋመው የሱዳን መንግሥት አባላት ነን፣” ሲል የሚጠቅስ ሲሆን ድርጅቱ የፈፀመው ጥሰት ማብራሪያ የሚሻ መሆኑንም የሚጠይቅ ነው።

አብደላህ ሐምዶክ መቀመጫው በኒዮርክ የሆነው የተመድ ጽህፈት ቤትን ያመላከቱበት ደብዳቤ ከአንድ ቀን በፊት (በመስከረም 23፣ 2023 እኤአ) የላኩ ሲሆን፣ “በሱዳን የጥቅምት 25ቱ መፈንቅለ መንግስት መሪ በ78ኛው የመንግስታቱ ምክር ቤቱ ስብሰባ ስለመጋበዙ፤” የሚል አርእስት የተሰጠው ነው።

ሐምዶክ፣ በቀዳሚነት ባሰፈሩት የመልእክታቸው ምዕራፍ፣ “ጥቅምት 25፣ 2021 በሌተናል ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን የተመራው ወታደራዊ ክንፍ በሱዳን የሽግግር ሲቪል መንግስቱ ላይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመፈፀም በሀገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ስርአት እንዲገረሰስ አድርጓል።” “ነው ያሉት።  “የዚህ መፈንቅለ መንግስት ቀጥተኛ ጦስ ያጠላበት ኢ-ህገመንግስታዊ ራስ ገዝ አስተዳደር በሀገሪቱ ለማቋቋም ቢሞክሩም ስርአቱ ከመሰረቱ የተጣሰ በመሆኑ የሚያዝያ 15ቱን ጦርነት በማስከተል ይበለጥ የፈራረሰ መንግስታዊ ተጨባጭ ሊያነብር ችሏል።”

ለምዶክ በሁለተኛ ደረጃ ባሰፈሩት መልእክታቸው አል ቡርሃን የመራው መፈንቅለ መንግስት አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ሌሎችም አህጉራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ማውገዛቸውና እንደማይቀበሉት አቋማቸውን መግለፃቸውን አስታውሰዋል።

የአዉሮፓ ኅብረትም የሱዳን የሽግግር መንግሥትን አደናቅፎና ዲሞክራሲያዊ ለዉጡን ያስቆመውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት እንደማይቀበለው ገልጾ በማውገዝ ሥልጣኑን ለሲቪሎቹ እንዲመልስ መጠየቁንም ሐምዶክ አውስተዋል።

በሶስተኝነት በሰፈረው የሐምዶክ መልእክት፣ “የመፈንቅለ መንግስት “መሪ” አል ቡርሃን ሱዳንን እንደሚወክሉ ተቆጥረው በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸው ከላይ ከተገለጹት ነባር አቋሞች ጋር ይቃረናል።” ሲሉ ያወገዙ ሲሆን፣ መሰል ከህግ የሚጣረስ ተግባር በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት የማራዘም አሉታዊ አስተዋፅኦ የሚያበረክት፣ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስትን አይዞህ ብሎ የሚያበረታታ እጅግ አደገኛ ምልክት የሚሰጥ ነው።” ብለዋል።

በታህሳስ 2018 የተካሄደውን የሱዳን ሕዝባዊ አብዮት ተከትሎ የመንግስት ህጋዊነት ሙሉ ለሙሉ ህዝባዊ የመሆኑን ማረጋገጫ ከሰጠ በኋላ ይህንኑ አቋም የሚፃረር ድርጊት ፈፅሟል በማለት ተመድን የኮነኑት ሐምዶክ፣ የጥቅምት 25ቱን አል ቡርሃን – መራሽ መፈንቅለ መንግስትን ውድቅ አድርጎ የቡድኑን ፖለቲካዊ ሚና ሀገሪቱን ከውጭ አደጋ በመከላከል ላይ ገድቦት የነበረው የመንግስታቱ ድርጅት፣ ዛሬ በተቃራኒው፣ በሱዳን ለሚካሄደው ጦርነት መንስኤና ዋነኛ ተዋናይ ለሆነው የመፈንቅለ መንግስት መሪ በመንግስታቱ ጉባኤ ላይ እንዲሳተፍ ግብዣ ማደረጉ የሱዳን ህዝብ ለዲሞክራሲ፣ ለሰላም እና ለነጻነት ያለውን ጽኑ ፍላጎት ፈፅሞ የሚቃረን ነው።” ብለዋል።