የአሜሪካ የልማት ባንክ በትግራይ ጦርነት ሰበብ ለነ ሳፋሪኮም ይሰጣል የተባለውን 500 ሚሊዮን ዶላር ማዘግየቱ የተነገረው ጥቅምት 18እኤአ ነው። የአሜሪካው የልማት ባንክ ዓለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ፈረንጆች አዲስ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ እጀምራለሁ ላለው በሳፋሪኮም የሚመራ ጥምረት ሊሰጥ የነበረውን 500 ሚሊዮን ዶላር ማዘግየቱ ከሳምንት በፊት ተነግሯል፡፡ባንኩ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተገናኘ ሁኔታዎችን በቅርበት እየመረመርኩ ነው ያለ ሲሆን፣ በዚህም የሚሰጠውን ገንዘብ አዘግይቻለሁ ነበር ያለው።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሌሎች የማዕቀብና የጫና ረቂቆችን በማውጣትና ፕሮፓጋንዳ በመንዛት እንደተጠመደ ይታወቃል።
የአውሮፓ ህብረት ግን የተለየ ጎዳና የያዘ ይመስላል፤ እንደስካሁን አካሄዶቹ ከሆነ። ህብረቱ የVodafone እና Safaricom ጥምረት በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፈቃድ ሰጥቶቷል። በመስከረም 8 2021 የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በገለልተኛ ኩባንያ የተለያዩ ጥናቶችን አስደርጎ ኩባንያዎቹ መቀጠል ይችላሉ ብሏል። ድጋፍም ያገኛል ነው ያለው።
ሌላው የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የውስጥ ቀውስ በተመለከተ ለማዕቀብ እንዲሰበሰብ አየርላንድ ብትጠይቅም ያለስምምነት ነበር የተበተነው። በመቀጠል የተለያዩ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ቀውሱን መፍታት እንደሚፈልጉ ከውጭ ጉዳይ ምኒስትር ጋር ምክክር ሲያደርጉ ተመልክተናል።ከዚህ ቀጥሎ በነበሩት ቀናት ደግሞ ከ59 በላይ የጀርመን ግዙፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በስፋት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ያለመ የምክክር መድረክ የተካሄደውም ባሳለፍነው ሳምንት በጥቅምት 19 ቀን 2014 ነው።የጀርመን አፍሪካ ቢዝነስ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ክላውዲያ ቮስ የጀርመን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በስፋት መዋለ ንዋያቸውን እንደሚያፈሱ እምነታቸው መሆኑን በመድረኩ ላይ ገልጸዋል።
አውሮፓ ህብረት የአሜሪካን አካሄድ እየተውት ይሆን!ህብረቱ የዋሽንግተንን አካሄድ ማማረር ከጀመረ ቆየት ብሏል። ጎልቶ መታየት የጀመረው በቻይና አሜሪካ ውዝግብ ወቅት ነው። በዚህም የአሜሪካን ራስ ወዳድ አካሄድ ሲያጣጥሉና ከቻይና ጋር ያላቸውን ትብብር በማሳደግ የበለጠ እንደሚጠቅማቸው አቋም እየያዘ ስለመሆኑ በስፋት ይነገራል።ምክንያቱን በንግድ ብቻ ብንመለከተው አውሮፓ ህብረት ከቻይናና አሜሪካ ያላቸው የንግድ ልውውጥ የአጠቃላዩን 39በመቶ ይሸፍናል። ቻይና ከህብረቱና ከአሜሪካ ያላት ልውውጥ ደግሞ የአጠቃላይ ንግዷን 30 በመቶ መሆንን የአሜሪካ ንግድ ልውውጥ ከቻይናና ከህብረቱ ጋር የአጠቃላዩን 35 በመቶ የሚበልጥ ነው። (Centre for European Reform; 21 Sept 2020)
ያለፈው ጥቅምት መጀመሪያ 2021 ላይ ካቶ ተቋም ባቀረበው ፅሁፍ የአውሮፓ መንግስታት በራሳቸው ቆመው እንዲሰሩና ተግዳሮቶቻቸውን ተጋፍጠው ችግሮቻቸውን ለመቅረፍ አሜሪካን መመልከት ማቆም አለባቸው ብሏል።
የአውሮፓ ኮሚሽኑ አባል ቲዬሪ ብሬተን በበኩላቸው “በአውሮፓ ህብረትና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የነበረው መተማመን እንደተሸረሸረ የሚያሳዩ ሁነቶች እየበረቱ ናቸው” ነበር ሲሉ ወቅሰዋል። “በአውሮፓ አገራት ዘንድ አንድ የተበላሸ ነገር ስለመኖሩ ስሜቶች እያደጉ ናቸው” ያሉት የኮሚሽኑ አባል “ምንም ጥርጥር የለውም መንስኤው የአሜሪካ በእብሪትና ንቀት የሚወሰዱ እርምጃዎች ናቸው። የሚገርመው 2ኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ከሰባ ስድስት ዓመታት ቢሞላውም አውሮፓ በአሜሪካ ላይ ጥገኛ መሆኗ አሳፋሪ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
የፋይናንሺያል ታይምስ ተንታኙ ፊሊፕ እስቴፋን አተያይ በፅሁፉ የተካተተ ሲሆን እሱም “የተለመደው የአሜሪካ አለመታመንና እምነት ማጉደል ለአጋሮች ምን ያህል ግድየለሽና ርህራሄ የለሽ መሆኗን በተደጋጋሚ ያረጋግጣል” ብሏል።“ዩናይትድ ስቴትስ ራስ ወዳድነትን ከማሳደድ ርቃ አታውቅም” ሲልም ህብረቱ አዲስ ስትራቴጂ መከተል እንዳለበት የሚሰነዘሩ ሐሳቦችን አጠናክሯል።
ታዲያ በተለያዩ አውዶች ከታየው አንድነትና ድል ጋር ተዳምሮ በዲፕሎማሲው ረገድም እንደ አውሮፓ ህብረት ያሉ አጋሮች ወደ ቀድሞ ትብብራቸው ይመለሱ ይሆን? አመላካቾች ቢኖሩም ተጨባጩ በቀጣይ ጊዜያት የሚገለጥ ሲሆን ይህንኑ ያገናዘብ አካሄድ መቀየስ ግን ለነገ የማይባል ስራ ነው።
ኢትዮጵያ ታሸንፋለችእስሌማን ዓባይ
ዋቢhttps://www.cato.org/commentary/europeans-whine-us-unreliable-time-them-take-over-responsibility-their-own-security