Western

እንግሊዝ በኢትዮጵያ ግድብ መገንባት ያቀደችበት ታሪክ

By Esleman Abay

September 27, 2021

The Nile

ግብፅ ውስጥ ለሚገኘው አስዋን ግድብ ውሀ የሚያቀርብ ሌላ ግድብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሰራ ታቅዶ ነበር

በአሜሪካን ሀገር መኖርያቸውን ያደረጉት የምህንድስና ባለሙያው እና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጥናቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ የሚታወቁት አቶ ሲሳይ አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው መረጃውን የተናገሩት።

እንግሊዝ ግብፅ ውስጥ በስፋት ጥጥ ታመርት ነበር፤ ያ ጥጥ ወደ እንግሊዝ ሄዶ የሱፍ ጨርቅ ይመረትበት ስለነበር፤ የአባይ ውሀ ፍሰት እንዳይቀንስ ትሰጋ ነበር፡፡ በግብጽ እና በሱዳን ለከፈቷቸው ኢንዱሰትሪዎች ቋሚ የጥጥ አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግም ቋሚ የውሀ አቅርቦት ያስፈልግ ነበር፡፡ አስዋን ግድብ እንደተገነባ፤ እድሜው እንዲረዝምና በቋሚነት ውሀ እንዲያቀርብ እንግሊዞች ኢትዮጵያ ውስጥ ግድብ እንዲገነባ አቋም ይዘው ነበር፡፡ አንደኛ እንደ ድርቅ ያለ የችግር ጊዜ ሲመጣ መጠባበቂያ ግድብ ውሀ እንዲለቅ ነበር የታሰበው፡፡ሀይለኛ ጎርፍ ቢመጣም፣ እየበረደ ሱዳንን አልፎ ወደ ግብፅ ይደርሳል ተብሎ ታስቦ እንደነበር ነግረውናል፡፡ሌላው እንግሊዞች በወቅቱ አስበውት የነበረው፤ በትነት ውሀ እንዳያጡ ይሰጉ ስለነበር፤ ከጣና ሀይቅ በመጥለፍ በቱቦ አድርጎ ውሀውን መውሰድ ነበር፡፡

ታዲያ የህዳሴ ግድቡ ለግብፅ ያለውን ጠቀሜታ እንግሊዝም ቀድማ ያስገነዘበቻት ሀቅ ሆኖ እያለ ቅዠትን መንገዷ አድርጋለች።