የዓባይ:ልጅ Esleman Abay
...ከዓባይ አመታዊ ፍሰት 20 ቢሊዮን ኪዩቢክ ድርሻ ለማግኘት ኢትዮጵያ ያቀረበችው ፕሮፖዛል በካይሮ ውድቅ ተደርጓል...
የህዳሴ ግድቡን ቴክኒካል ጉዳዮች በዝርዝር ጠንቅቀው የሚያውቁ የግብፅ የመስኖ ሚኒስቴር ምንጭ ነግረውኛል ያለው የሳዑዲ አረቢያው አል አራቢ አል-ጃዲድ “ከኢትዮጵያ በኩል የአቋም ድርቅናው እንደቀጠለ ነው፤ ለመስማማት ቅን ልቦናም አለመኖሩ ተስተውሏል።” ሲል አስነብቧል።
“በአስገዳጅ ስምምነት እንዲፈረም ካይሮ የፀና አቋሟ የሚቀጥል ነው” በማለት የግብፁ የመረጃ ምንጭ ነግሮኛል ያለው Al-Arabia ፣ ካይሮ ከድርድሩ የምትሻው አጀንዳ ”የህዳሴ ግድቡ ጉዳይ አይደለም፤ ምክንያቱም ህዳሴ ግድቡ በአንድ ወገን ተገንብቶ እየተጠናቀቀ Fait Accomplai’ ሆኗልና፤ ይሁንና በህግ ካልታሰረች ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌላ የግድብ ፕሮጀክት ይፋ ስታደርግ የግብፅ ዋነኛው ቀውስ አሀዱ ብሎ ይጀምራል።” ብለዋል።
“ግብፅ የኢትዮጵያን እቅድ አለመቀበሏን አሳውቃለች” ያለው የአል-አረቢ ዘገባ፣ “ከዓባይ/ናይል ወንዝ አመታዊ ፍሰት 20 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ድርሻ ለማግኘት ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ፕሮፖዛል ውድቅ አድርጋዋለች።” ሲሉ ነግረውኛል ብሏል።በዚህ ጉዳይ በቀደሙት የድርድር ዙሮች ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከኤምሬትስ የተሳተፉት ታዛቢዎች በተገኙበት ድርድር ላይ በይፋ የታዘቡት ነው።” በማለትም አልአረቢ ፅፏል።አልአረቢ አክሎ በዘገበው የካይሮው ሰው መረጃው “የናይል/ዓባይ ተፋሰስ 3.4 ትሪሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያለው ሲሆን ኢትዮጵያ የ 150 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ድርሻ ሲኖራት፣ ሱዳን 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር፣ ግብፅ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ድርሻ ነው ያላቸው።” ሲል አስነብቧል።
ይህ የሳዑዲ አረቢያ ሚዲያ (አልአረቢያ) ምን አይነት ጉድ ነው የሚያስደምጠን!?
የዓባይ ልጅ Esleman Abay