የዓባይ፡ልጅ
▪️በሺዎች ለሚቆጠሩ ሶማሊያዊያን ወታደራዊ ስልጠና መስጠት መጀመሯ ማነጋገር ጀምሯል▪️ግብፅ በኢማራት ፈንድ በሚደረግ ፕሮጀክት ስር በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊያ ወታደሮችን እየመለመለች መሆኗ ተጋልጧል።የግብፅና የኢማራት ወታደራዊና የስለላ ባለስልጣናት በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊያ ምልምሎችን ለመመዝገብ በማቀድ ባለፉት ሳምንታት ወደ ሞቃዲሾ ሲጎርፉ እንደሚገኙም ነው ይፋ የሆነው። በዚህም የማሊያዊ ወታደሮች ወደ ግብፅ ተጉዘው ቀጣይ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ ነው ሀገራቱ የወሰኑት። በመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር 1,200 የሶማሊያ ወታደሮች ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ግብፅ መወሰዳቸውን የገለፁት የሶማሊያና አካባቢው ገለልተኛ የዜና ምንጮች ናቸው። በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥም 8,000 ሶማሊያዊ ወታደሮችን ወደ ግብፅ መውሰድ የሚያስችል የምልመላ መርሃግብር በግብፅና ኢምሬት ባለስልጣናት መታቀዱም ነው የተነገረው።
በፈረንጆቹ 2018 ሶማሊያ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሰለጠነውን ሰራዊት በመበተን ሞቃዲሾ የሚገኘው የኢማራት ወታደራዊ ጣቢያን እንዲዘጋ መወሰኗ የሚታወስ ሲሆን፤ የፋርማጆ መንግስት ያንን ርምጃ የወሰደው በባህረ ሰላጤው የአረብ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ከፍተኛ ፉክክር በሚፈጥረው ተፅዕኖ ሳቢያ ነው በማለት በርካታ ተንታኞች ሲገልፁ ነበር።የሶማሊያ መንግስት ወደ ግብፅ የሚመለመሉ ወታደሮቻቸውን ጉዳይ በሚስጥር የመያዝ አቋም ነበራቸው የተባለ ሲሆን። ወታደሮቹ ስልጠናውን ከጨረሱ በኋላ የሁለቱንም ሀገራት ጥቅም በአገር ውስጥ በማራመድ ለግብፅ እና ኢማራት ቀጣናዊ ፕሮክሲ-ጦርነት ሊያገለግሉ የታሰቡ ናቸው የሚለው የበርካቶች እምነት ሆኗል።
ኢትዮጵያ ሶማሊያን ጨምሮ ታሪካዊ አጋሮቿ የትብብር ስትራቴጂን ለማጠናከር አቅምና ፍላጎቱ እንዳላት የሚገልፁት ተንታኞቹ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ካይሮ በአፍሪካ ቀንድ ተፅዕኖ ይኖራት ዘንድ ቆርጣ ተነስታለች ይላሉ።ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ስር በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿ በሶማሊያ እንደሚገኙ የሚገልፁት መረጃዎቹ በጦርነት በምትታመሰው ሀገረ-ሶማሊያ ውስጥ ሁለት ባላንጣ ወታደሮች መኖራቸው በራሱ አስርት አመታትን ባስቆጠረው የሶማሊያ ግጭት ውስጥ የበለጠ ስጋት አይሆንም ወይ? ሲሉ የሚጠይቁት በርካቶች ናቸው።
ግብፅ ለረጅም ጊዜ በሶማሊያ መገኘት ስትፈልግ ቆይታለች። አሁን በሞቃዲሾ የሚገኙ ባለስልጣናት ግብፅ በሶማሊያ ምድር የመጀመሪያውን ወታደራዊ ካምፕ የምትገነባበት የባህር ዳር የቱርክ ጦር ሰፈር አቅራቢያ ለግብፃውያን መሬት ሰጥቷቸዋል።
ሐሰን ሼክ ሙሐሙድ ከሳቸው በፊት የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ፋርማጆ ተቀናቃኝ በነበሩበት ወቅት፣ በውጭ ሀገራት የሚሰለጥኑ ወታደሮችን በማውገዝ ጠንካራ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ይታወሳል። ሐሴን ሼክ ሙሀሙድ ከመመረጣቸው በፊት ከገቡት ቁልፍ የቅስቀሳ ተስፋዎች መካከል መንግስታቸው በውጭ ሀገራት የሚደረጉ ማናቸውንም ኮንትራቶች(ወታደራዊ ጨምሮ) ለህዝብ ግልፅነት ባለው መንገድ ይሆናል የሚለው አንዱ ነበር። አሁን ወደ ግብፅ ይልኳቸው የጀመሩ ወታደሮች ጉዳይ፤ ጦርነት ለአመታት ያመሰቃቀላት ሶማሊያን ለውክልና ጦርነትና፣ የማያባራ የጦርነት አውድማነት ይዳርጋታል የሚል ስጋትም ፈጥሯል።
ለአመታት የባህረ ሰላጤው አረብ ሀገራት ጂኦ-ፖለቲካዊ ፉክክር ሰለባ ሆና የቆየችው ሶማሊያ፤ ከአምስት አመታት ወዲህ የነበረውን ብቻ ብናወሳ ኳታር እና ኢማራት በሀገሪቱ ጉዳይ ለተፅዕኖ እያደረጉት የሚገኘው ፍልሚያ ተጠቃሽ ነው። በሶማሊያ ግዛት ውስጥ አንዱ ሌላውን ለመርታት ለሶማሊያ መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ እንዲሁም ባሩድ በመስጠት ይታወቃሉ።ኳታር ለምሳሌ የሶማሊያ ባለስልጣናት፣ በፈረንጆቹ 2018 የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በሞቃዲሾ አውሮፕላን ጣቢያ በቁጥጥር ስር እንድታውል፤ ሲቀጥልም የኢማራት የጦር ሰፈርን እንድትዘጋ ተፅዕኖ አድርጋለች።በቅርብ በተደረገው ምርጫ ፋርማጆ መሸነፉ ለኢሚሬትስ እፎይታ የፈጠረና በሶማሊያ ፖለቲካዊ መድረክ እንድትመለስም በር ከፍቶላታል። ኤማራት በሞቃዲሾ የሚገኘውን ጦር ሰፈር እንደገና ለመክፈት አቅዳለችም ነው የተባለው። ለዚህም ቀደም ሲል ባሰለጠነቻቸውና ያስታጠቀቻቸው ወታደሮች መካከል በደርዘን ለሚቆጠሩ የሶማሊያ ወታደሮች ጥሪ ማቅረቧ ነው የተሰማው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአሁኑ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ከፊል ራስ-ገዝ በሆነችው ፑንትላንድ እያሰለጠነችና እያስታጠቀች መሆኗ በስፋት የተዘገበ ጉዳይ ነው። አቡ-ዳቢ ለሶማሌላንድ ተገንጣይ ክልል ወታደራዊና የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋለች በማለት የሚገልፁትም በርካቶች ናቸው።ይሁንና በቅርቡ ይፋ የሆነው፣ የሶማሊያ ወጣቶችን ወደ ግብፅ የመመልመልና የማዘዋወሩ ጉዳይ ኢማራትን ላልጠበቀችው ተቃውሞ ሊዳርጋት ይችላልም እየተባለ ይገኛል። ይህም ሐሰን ሼክ ውሳኔያቸውን እንደገና እንዲፈትሹ ሊያደርግ ይችላል በማለት…።
በተያያዘ፣ ግብፅ ለወታደራዊ ካምፕ የሚሆን ቦታ ከፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ መውሰዷና ይኸውም የቱርክ ጦር ሰፈር ከሚገኝበት የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ስለመሆኑም መረጃዎች እየወጡ ይገኛል።
ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ በምርጫው ማሸነፋቸውን ተከትሎ በካይሮ ጉብኝታቸው በህዳሴ ግድቡ ጉዳይ ከአል-ሲሲ ጋር መምከራቸው የተዘገበ ሲሆን፤ ለሞቃዲሾ በብዙ መለኪያ የከበደ ሚዛን ካላት አዲስ አበባ በፊት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ባላንጣዋን ካይሮ፣ በጉብኝት ቀዳሚ ማድረጋቸው የወቅቱ አነጋጋሪ እንደነበር አይዘነጋም።
ካይሮ የሶማሊያ ወታደሮችን መመልመል መጀመሯ ከፍተኛ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ በሶማሊያ ጉዳይ፣ በቀጣናውም ሆነ በአጠቃላይ የውጭ ጉዳያቸው ከግብፅ የሚፃረር ፖሊሲ ያላቸው ሀገራት ጋር ምን የሚያስማማ ነገር ጉዳይ ተገኘ የሚለው አንዱ ነው። ለአብነትም ቱርክ በሶማሊያ ያላትን ተፅዕኖ ለመገዳደር ከሞቃዲሾ ጋር ትብብር እንደምትሻ የገለፀችው ከወራት በፊት ነው። ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጋር አለም አቀፍ ጫናዎችን ተቋቁሞ የቀጠለ ግንኙነት ያላት አቡ-ዳቢ ካይሮ በሶማሊያ እግሯን መትከሏ ሁለቱንም አጋሮቿን ስጋት ላይ የሚጥል እንደሆነ ግልፅ ነው።
#የዓባይልጅ#HornOfAfrica #Somalia #Egypt #Mogadishu
#የዓባይልጅ#HornOfAfrica #Somalia #Egypt #Mogadishu
https://www.busiweek.com/egypt-recruiting-somali-soldiers-amid-horn-power-struggle-with-ethiopia/https://www.google.com/amp/s/somaliguardian.com/news/somalia-news/egypt-recruiting-thousands-of-soldiers-in-somalia-amid-horn-power-struggle-with-ethiopia/amp/https://somalimirror.net/2022/10/18/egypt-recruiting-thousands-of-soldiers-in-somalia-amid-horn-power-struggle-with-ethiopia/https://somalilandstandard.com/egypt-commences-to-recruit-hundreds-of-somali-soldiers-amid-horn-power-struggle-with-ethiopia/https://www.al-monitor.com/originals/2022/01/egypt-supports-somalia-counter-turkish-influence