Diplomacy ዲፕሎማሲ

የኬኒያ አበርክቶ በፀጥታው ምክር ቤት

By Esleman Abay

September 23, 2021

kenyataabiy ahmed and uhuru

ተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የሚሰራበትን አንድ ደምብ አለ። በአጀንዳነት በተያዘ ጉዳይ ዙሪያ የመንግስታቱ አቋም ከመገለፁ በፊት በጉዳዩ ረቂቅ ዙሪያ ተከታታይ ምክክሮች ይደረጉበታል። የጉዳዩ ረቂቅ በምክክሩ የሚቀርቡ ሃሳቦችን ጠብቆ ማስተካከያ እየተደረገበት ገቢ መሆኑን ይቀጥላል።

ገቢ የሆነው ረቂቅ (በጣት የሚቆጠሩ) ቀናትን ይጠብቃል። በነዚህ ቀናት ውስጥ ከአባል አገራቱ ሀሳብ ካልቀረበበት ይፀድቃል ወይም የፀጥታው ምክር ቤቱ የጋራ አቋም ይሆናል። ቀነ ገደቡ ከመድረሱ በፊት ከአባል አገራት አንዱ ጥያቄ ካቀረበ ደግሞ ዝምታው ተሰበረ ይባልና እንደገና ይመከርበታል። ተሻሽሎ እንዲቀርብም ይደረጋል።

ቱኒዚያ የግብፅን ጉዳይ ለማስፈፀም ለፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችው ፕሮፖዛልል እስከ ወርሃ መስከረም ድረስ አራት ጊዜ ነበር እንዲሻሻል የሆነው። በዚህ የጊዜ ቆይታ መካከል ነበር ይፋዊ ጉባዔ ተደርጎ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ስር እንዲደረግ የተወሰነው። ይሁን እንጂ በድርድሩ ቀጣይ ሂደት የፀጥታ ምክር ቤቱ እጁ እንዲገባ ሴረኛ ይዘቶች በፕሮፖዛሉ ተሰግስገውበት ነበር።

➪የመጀመሪያው ረቂቅ የሰኔ 15ቱን የአረብ ሊግ አቋም ተከትሎ ገቢ ከተደረገ በኋላ እስከ ሐምሌ 16 እኤአ ድረስ በዝምታ ነበር የቀጠለው።➪በ 16 ኬኒያ ዝምታውን ሰበረች➪2ው ረቂቅ ተሻሽሎ በሐምሌ 17 እኤአ ቀረበ➪በድጋሚ መስከረም 2 ላይ ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሻሎ እንዲቀርብ አሁንም ኬኒያ ዝምታውን ሰበረች➪ይህም መስከረም 7 ላይ ገቢ ከሆነ በኋላአራተኛውና የመጨረሻው ረቂቅ ገቢ የሆነው በመስከረም 13 ነበር

በቱኒዚያው ፕሮፖዛል 4 ማሻሻያ ጥያቄዎች መሰረትም ተከታዮቹ ይዘቶች እንዲወገዱ ሆነዋል፦➪ቀጣዩን የድርድር ውጤት በተመለከተ ዋና ጸሐፊው በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤቱ ሪፖርት እንዲያቀርብ የሚጠይቀው➪ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነት አስቀድማ እንድትፈርም ለማስገደድ የቀረበው፣➪ሶስቱ አገራት የሙሌቱ ወሩ ከመድረሱ በፊት ከአስገዳጅ ስምምነት እንዲደርሱ ራሱ ምክር ቤቱ በጠንካራ “ቋንቋ” የጠየቀበትና በዚህም እንደማትስማማ የሚታወቅ ሲሆን ተከትሎ ይመጣ የነበረው አቋም ያልተስማሙትን ሶስቱንም ሳይሆን ኢትዮጵያን ብቻ የሚበድል ነበር፤ እሱም ሙሌቱን መቃወም፤

በነዚህ ሂደቶች ውስጥ የኬኒያ ሚና ለራሷም ለአፍሪካም ሆነ ለኢትዮጵያ ጠቀሜታ ያለው ነበርበነዚህ ጊዜያት ውስጥ ከኬኒያ ጋር በሃይል በሌሎችም ዘርፎች ያደረግናቸው ስምምነቶች ወሳኞች ነበሩ። በኬኒያ በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሚናም ሊመሰገን የሚገባው ነው።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

GERD

eslemanabay Meles Alem

የዓባይልጅ

Ethiopia Citizen TV Kenya Love Matters Kenya Ethiopian Embassy Nairobi

AsantekenyaUmojaWaAfrika

afrikamoja

Asante #UhurusLegacy