የአለም አቀፍ NGO አዋጁን መከለስ የህልውና ጉዳይ! ለምን..?

የእነ ዶክተር እሌኒ ቡድን እንደ ማሳያ
-እስሌማን ዓባይ

Those Controlling the money, controls the Media, & controls the Mind as wel

ትህነግ በሌላ ማሊያ ወደ ስልጣን ትመለስላቸው ዘንድ ዶክተር እሌኒና ግብረ አበሮቿ በzoom ያደረጉት የክፋትና የክህደት ድርጊት ከባንዳ ሊጠበቅ የሚችል ነውና ብዙም አልደነቀኝም። ከዚህ ይልቅ ኢትዮጵያን ለነዚህ ባንዳዎች ለማስረከብ ማን ጨካኝ አሰባሰባቸው? የሚለው ነጥብ ላይ ፍተሻ ማድረግ ጠቃሚ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

የዶክተር እሌኒ ቡድን የተሰባሰበው Peace and Development Center በተባለ ተቋም ስር ነው። ተቋሙ በትህነግና ሸኔ ሰዎች እንደተመስረተም ተጠቅሷል። ወደ ተቋሙ ድረገፅ ስትገቡ አቋቁመውና በጀት እያቀረቡላቸው የሚገኙ ስፖንሰርና አጋሮቻቸውን ዝርዝር በኩራት ለጥፈዋቸው ይታያል። USAID, National Endowment for Democracy NED, አውሮፓ ህብረት፣ ጀርመን ኢምባሲ፣ ተመድ ዋናዋናዎቹ ናቸው። በዚህ ፅሁፍ NED እና USAID የተባሉ አጋሮቻቸውን በተመለከተ ዳሰሳ አደርግ ዘንድ ምክንያት የሆኑኝ በርካታ ነጥቦች ናቸው።
መልካም ንባብ

○USAID, CIA & NED
አሜሪካ፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የውጭ ፖሊሲዋን በቀጥታ ጣልቃ ገብነት ማራመድ እንደማያዋጣት በመገንዘቧ በመንግሥት በጀት የሚደገፉ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን አቋቁማ፣ በህዝብ ድምፅ የተሰጠን የሥልጣን ውክልና እስከመቀልበስ በዘለቀ የመንግሥት ለውጥ ሀገራትን በተፅእኖ ሥር የማድረግ ሥልትን መረጠች። ይህን ለማድረግም በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት የስትራቴጂክ አገልግሎት ቢሮዋን 1947 ባቋቋመችው ሲአይኤ እንዲተካ አደረገች።
እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ መገባደጃ ላይ ታዲያ የአሜሪካ NGOs ጣልቃ ለመግባት ከሲአይኤ የገንዘብ ድጋፍ እያገኙ እንደነበር ተጋለጠ።
ይኸውም በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መንግስታትን ከስልጣን ማውረድ፣ አመጽ መቀስቀስና ድንበር ተሻጋሪ ኩባንያዎችን በመደገፍ የተደረጉ ነበሩ።
ይህን ተከትሎም CIA የውጭ አጀንዳውን ማስቀጠል እንዲችል ማሻሻያ ማድረግ ነበረበት። በዚህም ከአሜሪካው አለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ USAID በሚበጀት ገንዘብ አንድ የመንግስት ለትርፍ ያልተቋቋመ ኮርፖሬሽን እንዲቋቋም ተወሰነ። እ.ኤ.አ. በ1983፣ አዲሱ ድርጅት ተፈጠረና ሲአይኤ ከአሜሪካ ፖሊሲ ጋር ላልተስማሙ ሀገራት አዲስ መንገድ ጀመረ። ስሙንም “ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ ሲሉ ጠሩት – National Endowment For Democracy NED.

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በነበሩት ሮናልድ ሬገን ዘመነ ሥልጣን የሶቭየትን ተፅዕኖ ለመቋቋም የተመሠረተው ይኸው National Endowment for Democracy NED ያሉት ይህ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በአሜሪካ መንግሥት በሚመደብ በጀት የሚንቀሳቀስ ነው። የዚህን ድርጅት አጀንዳ ወደተፈለጉ አገራት ለማስገባት በጀት ተመደቦላቸው አስፈፃሚ ከሆኑ ድርጅቶች ውስጥም Institute for International Affair – NDI አሜሪካ ከምትከተለው ዴሞክራሲን በማስፈን ሽፋን አንዱ ጣልቃ መግቢያ ተቋም ነው፡፡ በተመሳሳይ ረድፍም International Republican Institute IRR፣ ዓለም አቀፍ የምርጫ ሥርዓት ፋውንዴሽን International Foundation for Electoral System IFES፣ International Research and Exchange Board IREX፣ ፍሪደም ሐውስ Freedom House የተባሉት ተጠቃሽ ናቸው። የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ተቋም Institute for International Affair – NDI 97% በጀቱን በUSAID በኩል ከአሜሪካ መንግሥት ይቀርብለታል፡፡

○መግቢያዎቻቸው እና አሽከሮቻቸው
የመንግሥት ለውጥ እስከማድረግ የሚዘልቀውን ጣልቃ ገብነት በሥራ ላይ ለማዋል፣ አስፈፃሚዎቹ NGOs ወደ ታላሚ ሀገራት የሚሰርጉበት ሥልት ይመቻቻል። ቀዳሚዎቹ ደግሞ ሰብዓዊ መብትና ዴሞክራሲን ማስፈን የሚሊ ሰበቦች ናቸው።
በዚህ ጭንብል ተጀቡነውም ሀገር ውስጥ ካሉ የሥልጣን ጥም ካንገበገባቸው ቡድኖችና ግለሰቦች ጋር ጥምረት ይፈጥራሉ።
በመቀጠልም በሀገር ውስጥ ያሉ ቡድኖችን ፍላጎት በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተጋባት ማጉላት፤ በሀገር ውስጥ የተቃውሞ አጀንዳዎችን ፈጥረው መልሰው ማስተጋባት።
መንግሥታዊ ተቋማትና ሚዲያዎችን ተዓማኒነት ማሳጣት ዋነኛው አካሄዳቸው ነው። ፅንፈኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና በነፃ ፕሬስ ሽፋን የነሱን አመለካከት የሚያራምዱ መፅሄቶችና ጋዜጦች በተከታታይ እንደ ፍርድ ቤትና ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማትን ተዓማኒነት የማሳጣት ዘመቻ መገለጫቸው ነው፡፡
በመሠረተ ቢስ ጥላቻ የሚነዱ የተቃዋሚ ሚዲያዎችን፣ አክቲቪስትና ጋዜጠኞችን እንደ ነፃና ገለልተኛ፣ እንዲሁም እውነትን ዘጋቢ አስመስሎ መሳል፤ የመረጃ ምንጭ ማድረግ፤

አገራዊ አንድነት ላይ የሚሰሩ ሚዲያዎችን አንቂዎችንና ጋዜጠኞችን ማጣጣልና እድል መንፈግ ሌላኛው ነው። በተመሳሳይም የዲጂታል ኩባንያዎችን አሰራር በመጠምዘዝ ከነሱ በተፃራሪ የሚገኙ የዲጂታል ይዘቶችን ተደራሽነት መገደብ፤ መዝጋት፤ ማስጠንቀቂያ ማብዛት ተጠቃሽ ናቸው።
ማህበራትን ማደራጀት፤ ለማስፈፀሚያነት የሚያገለግሉ የጋዜጠኞች ማህበር እና መሰሎችን ማቋቋም እንዲሁ የነሱ ተግባራት ናቸው።

○ጫናው ያረፈባቸው አገራት
አሜሪካና አጋሮቿ “ሰብዓዊ መብት ማስከበርና ዴሞክራሲን ማስፋፋት” በሚል ሽፋን በተለይም በምሥራቅ አውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ አገራት ውስጥ ምርጫን በማስታከክ ህገ ወጥ የመንግሥት ለውጥ እንዲካሄድ ሞክረዋል፤ አድርገዋልም።
ከሀገራቱ መካከልም እ.ኤ.አ በ2004 በዩክሬን፣ በ2005 በኪርጊስታን፣ 2003 በጆርጂያ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በ2004 በዩክሬን የተካሄደው የመንግሥት ለውጥ አመፅ ውስጥ ብሄራዊ ኢንዶውመንት ለዴሞክራሲ National Endowment for Democracy NED እጅ እንዳለበት በማስረጃዎች ተረጋግጧል። በየዩክሬይኑ ብጥብጥም 65 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ ሰጥታለች።

በሃያሏ ሀገረ ቻይና ሳይቀር ለተገንጣይ ቡድኖች የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት በውስጥ ጉዳይዋ በተደጋጋሚ ጣልቃ ገብታለች። በዚህም በዢንጂያንግ፣ ቲቤት፣ ታይዋንና ሆንግ ኮንግ በ”ሰብአዊ መብት” ሰበብ ቻይና በሰብአዊ መብት ላይ ያከናወኗትን ስኬቶች ችላ በማለት፣ እነዚህ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቻይናን የሚያበላሹ ሪፖርቶችን ይፋ አድርገዋል።
አንዳንድ የግል የጥናት ተቋማት ይህን አሳፋሪ ድርጊት ማጋለጥ የቻሉበት አጋጣሚዎችም ነበሩ። በ2018 ጋዜጠኛ ማክስ በUSAID እና NED የሚደገፉ NGOs በሌሎች አገራት ምርጫዎች ላይ የሚያሴሩ “የጣልቃ ገብነት ማሽኖች” ሲል ነበር የሰየማቸው።
NED በ2018 “ምስራቅ ቱርኪስታን” ተብሎ ከሚጠራው ዚንጂያንግ ጋር ለተያያዙ ፕሮጀክቶች 670,000 ዶላር ሰጥቷል። ከገንዘቡ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወርልድ ኡዩጉር ኮንግረስ ለተባለው ግንባር ነው። NED በዚሁ አመት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሲል ለጠሯቸው ቡድኖች 4.75 ሚሊዮን ዶላር አቅርቧል። በተጨማሪም በስደት የሚገኙና የተገንጣይነት ዝንባሌ ያላቸውን የቻይና አካል ቲቤታዊ ኅትመቶችና የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ስፖንሰር አድርጓል፣ ይህም የሰብአዊ መብት ረገጣ እያሉ እንዲመዘግቡና አዳዲስ የመገንጠል አራማጅ ግንባሮችን እንዲያበራክቱ ለማድረግ ሞክሯል። ለዚህ አላማም በ2018 ብቻ 630,000 ዶላር ሰጥቷል።
ወጣት ምሁራንን በማነሳሳት የመንግስት ገሰልበጣን ያበረታታሉ ሲል የጀርመን የዜና መጽሔት ዴር ስፒገል በሰኔ 2008 ባወጣው ዘገባ አስነብቧል።
የሆንግ ኮንግ የዜና ማሰራጫ wenweipo . com እንደዘገበው ደግሞ NED ከ2014 ወዲህ በሆንግ ኮንግ የሚረጨውን ገንዘብ ጨምሯል። ከ1990 እስከ 2018 ውስጥም 1.3 ሚሊዮን ዶላር አውጥቷል። NED ራሱ ባወጣው መረጃ መሠረት ደግሞ ከ2016-2018 ለሆንግኮንግ ንቅናቄዎች 1.16 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጓል።

○በኢትዮጵያ እግራቸውን የተከሉ ተቋማት
ከላይ የተዘረዘሩት በአገራችን እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ናቸው። እነሱም እነ USAID, International Republican Institute IRR, Institute for International Affair – NDI,
National Endowment for Democracy NED, Foundation for Electoral System IFES, International Research and Exchange Board IREX, ፍሪደም ሐውስ Freedom House

○መጠቅለያ
“ዛሬ እየሰራን ያለነው አብዛኛው ሥራ ከ25 ዓመታት በፊት የአሜሪካ የስለላ ድርጅት CIA ሲሰራ የነበረውን ነው” ሲሉ ከ2 አመት በፊት የተናገሩት ሚስተር አለን ዌይንስቴይን የተባሉ ሰው ናቸው። ይህ ሰው የሌላ ድርጅት ሀላፊ ሳይሆኑ የNational Democratic Institute for International Affair NDI ያልኳችሁ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ NGO ዳይሬክተር ናቸው።

የNED ድርጅትን ጨምሮ የዳሰስኳቸው ደም መጣጭ NGOs በኩል በቀረበላቸው ርዝራዥ የታወሩ ባንዳዎች አገራችን በአሸባሪ እንድትመራ ጉዳይ ሲያስፈፅሙ ተጋልጠዋል። ከነዚህ የሰይጣን ጭፍሮች ውስጥ ታዲያ የዶክተር እሌኒ ሰይጣናዊ አባልነት ይበልጥ አሳዝኖኛል።

ይህ የክፋት በር የተከፈተው ለአለማቀፍ NGOs የተፈቀደውን ህጋዊ ቀዳዳ በመጠቀም ነው። ከላይ የተጠቀሱትን የስለላ ዶላሮችና ተንኮሎች የሚያስገቡ ተቋማት የልማት ርዳታንም በማቅረብ ስም በር የተከፈተላቸው ናቸው።

በመሆኑም በውጭ አገራት/ተቋማት በጀት የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ሚዲያም ሆነ ጋዜጠኛ ለአገራዊ ጥቅም ይተጋል ማለት ዘበት ነው።
🔹አገር በቀል የሆነ public private ፈንድ የሚያገኙበት፣
🔹 ሚዲያው የውጭ ፈንድ የሚከለክል ህግ ያስፈልጋል።

ጉዳዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም በተመሳሳይ ይመለከታል

አዋጁ የሚከለስበት ጊዜ አሁን ነው።


Esleman የዓባይ፡ልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories