አዲስ ዘመን
- ኢትዮጵያ ውስጥ በሃይማኖትም ይሁን በብሔር ጉዳይ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ የሚለው እስሌማን የውጭ ኃይሎች በተለይም ግብፅች በውይይትና በንግግር ይፈታሉ እያልን በይደር ያቆየናቸውን ጉዳዮች ወደ ግጭት እንዲያመሩ በማድረግ የኢትዮጵያን ሰላም ለማወክ እየተጠቀሙበት መሆኑን ይናገራል።”
- “Egyptian Center for Strategic Study የሚባለው የግብፅ የጥናት ተቋም ከወር በፊት በኢትዮጵያ ጉዳይ ያወጣውን ጥናት ይፋ ማድረጉን እስሌማን ይናገራል። በዚህ ተቋም የሚደረጉ የጥናት ውጤቶች ለግብፅ የደህንነት መሥሪያ ቤት እንዲሁም ለግብፅ ውጭ ጉመስሪያ ቤት ይቀርባሉ። የጥናቶች መነሻ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ መልስ የሚሹ ጥያቄዎች ናቸው። መሰል ጥናቶች በግብፅ መደርደሪያ ላይ የሚቀመጡ ሳይሆኑ ወደ ተግባር የሚለወጡ ናቸው።
- “ወጣቱ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በሀገር ውስጥ አካሄዶች እንጂ የውጭ ኃይሎች በቀየሱለት ሊሆን እንደማይገባ፤ መንግሥትም ለጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ መስጠትና አስቀድሞም ችግሮችን መፍታት እንዳለበት ይጠቁሟል።”
- ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች የሚያስከትሏቸውን ስውር የጣልቃ ገብነት አጀንዳዎች ለመመከት የሚያግዝ የህግ አግባብ መንግስት ቢቀርፅ ችግሮቹን ማቃለል ይቻላል ብሏል።
አዲስ ዘመን: በዛሬው የወጣቶች አምድ ዝግጅታችን ወጣቶች መልኩን በየጊዜው እየቀያየረ ስለሚገኘውና አሁንም ሃይማኖታዊ መልክ ይዞ በተከሰቱ ሁነቶች ጀርባ የውጭ ጠላት ደባ ማስተዋል እንደሚሻ ምን ያህል ግንዛቤ አላቸው?ወጣት እስሌማን አባይ /የአባይ ልጅ/ አገራዊናወቅታዊ ጉዳዮችን እየተከታተለ ጠቃሚሀሳቦችን በማህበራዊ ሚዲያዎች በማጋራት ይታወቃል።በተለይም በህዳሴው ጉዳይ ዙሪያ የግብጾችን ሴራ እናየምዕራባዊያንን ጫና አስመልክቶ በርካታ ቁም ነገሮችንአስነብቦናል። በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ኢትዮጵያውስጥ ከሚፈጠረው ትርምስ ጀርባ የውጭ ኃይሎችእንደሚገኙበት እምነቱ ነው። በተለይም ግብፅ ከታላቁህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ በየጊዜው በጥናት የተደገፉሴራዎችን እየፈበረከች በጥቅም ለገዛቻቸው አካላትማስታጠቋ የአደባባይ ምስጢር እንደሆነ ይናገራል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በሃይማኖትም ይሁን በብሔር ጉዳይ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ የሚለው እስሌማንየውጭ ኃይሎች በተለይም ግብፅች በውይይትና በንግግርይፈታሉ እያልን በይደር ያቆየናቸውን ጉዳዮች ወደ ግጭትእንዲያመሩ በማድረግ የኢትዮጵያን ሰላም ለማወክእየተጠቀሙበት መሆኑን ይናገራል።ሕወሓት ከስልጣን መልቀቁን ተከትሎ በመንግሥትእና በቡድኑ መካከል የተፈጠረውን ጦርነት የውጭኃይሎች እንደጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ሕወሓትንበፕሮፓጋንዳ፣ በፋይናንስ እርዳታ እና በመሳሰሉትበመደገፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሳካት የሚፈልጉትን ጥቅምለማስከበር ሲጥሩ እንደነበር እስሌማን ያስታውሳል።በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮምዕራባዊያን፣ ግብፅና ሱዳን ሲፈጽሙ የነበረው ሴራየሚታወስ ነው። ሕወሓት በጦርነት በትረ ስልጣኑንመልሶ እንዲቆጣጠርና ጥቅማቸውን እንዲያስከብርላቸውየነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ ስለነበር በኢትዮጵያ መንግሥትላይ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችንየማሳደርና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን እየተጠቀሙ ሥምየማጠልሸቱን ሥራ ሲሠሩ ነበር። ሕወሓትአሸንፎ ስልጣን እንደማይዝ ሲያረጋግጡ ደግሞ ሌሎችአገር ያፈርሳሉ ብለው ያመኑባቸውን አጀንዳዎች እየቀረጹበተላላኪዎቻቸው በኩል ለማስፈጸም እየሞከሩ ናቸውይላል። ከነዚህም አንዱ ሰሞኑን ያየነው የሃይማኖትግጭት ነው።ጋዜጠኛ እስሌማን እንደሚናገረው፤ በግብጽ አገርየትኛውም ፕሬዚዳንት መጥቶ ቢሄድ ኢትዮጵያ ከአባይወንዝ ጋር በተያያዘ የግብፅ የምንግዜም ተቀናቃኝ ተደርጋመታየቷ አይቀርም። ማንም ይምጣ ማንም ይሂድግብፅ በአባይ ላይ ያላት ጥቅም አይቀየርም። ስለዚህጥቅማቸውን ለማስከበር የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።ፕሬዚዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ ከአመት በፊትየኢትዮጵያ መንግሥት ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ጦርነትውስጥ ሲገባ ቀጣናው ወደ ትርምስ ይቀየራል እያሉሲያስጠነቅቁ እንደነበር የሚታወስ ነው ይላል። የጦርነቱሁኔታ ብዙም እንደማያስኬዳቸው ሲረዱ ደግሞ የእርስበእርስ ግጭት የሚቀሰቀስባቸውን ስስ ብልቶች እያጠኑተግባራዊ ለማድረግ ይሞክራሉ።Egyptian Center for Strategic Study የሚባልአንድ የግብፅ የጥናት ተቋም ከወር በፊት በኢትዮጵያጉዳይ ያወጣውን ጥናት ይፋ ማድረጉን እስሌማንይናገራል። ተቋሙ በግብፅ መንግሥት ፈንድ የሚደረግነው። በዚህ ተቋም የሚደረጉ የጥናት ውጤቶች ለግብፅየደህንነት መሥሪያ ቤት እንዲሁም ለግብፅ ውጭ ጉመስሪያ ቤት ይቀርባሉ። ለሕዝብ መገለጽ ያለባቸውምበተለያየ መንገድ እንዲደርሱ ይደረጋል።ጥናቱ እንደ ሌሎች ጥናቶች መደርደሪያ ላይየሚቀመጥ ሳይሆን ወደ ተግባር የሚለወጥ ነው። በዚሁመሰረት ይህ ተቋም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የተለያዩጥናቶችን አድርጓል። ከነዚህ ውስጥ የሶስቱን ጥናቶችይዘት እንዲህ ያስረዳል። ለምሳሌ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥየኦሮሞ ሕዝብ የፖለቲካ ውክልና እና የዲሞክራሲጥያቄዎች፣ ለዘመናት ያልተሰማው ጩኸት›› በሚልአንድ ጥናት አውጥተዋል፤ ሌላው ጥናታቸው ደግሞ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደውን ግጭት ሙስሊሞችእንዴት ይመለከቱታል›› የሚል ሲሆን፤ ሶስተኛው‹‹እስልምናንና ክርስትናን በመጠቀም በናይል ዲፕሎማሲላይ ጫና ለማሳደር ትልቁ የኃይል አማራጫችን ይሆናል››የሚል ነው።ለነዚህ ጥናቶች መደረግ መነሻቸው አገር ውስጥያሉት መልስ የሚሹ ጥያቄዎች ናቸው። ጥናቶቹበሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ የሚችሉትን የሃይማትና የብሔርጥያቄዎችን ቤንዚል ጠብ እያደረጉበት የእርስ በእርስቀውስ ውስጥ እንድንገባ የሚያደርጉ ናቸው።“ጥያቄ አለኝ” የሚለው አካል ደግሞ አንዳንዱበማወቅ፤ አንዳንዱም ባለማወቅ በሰላማዊ ውይይትየሚፈቱ ጉዳዮችን የግጭት መንስኤ እያደረገ አጀንዳቸውንያስፈጽምላቸዋል።ግብፅ በአባይ ወንዝ ጉዳይ ከየትኛውም የተፋሰሱአባል አገራት ግንባር ቀደም ተሰሚነት እንደነበራትናፈላጭ ቆራጭ እንደነበረች፣ ከደርግ መንግሥት መምጣትበፊት ኢትዮጵያ የግብፅ ተባባሪ እንደነበረች፤ በተለይምበአጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የራሷን ጳጳስ ከመሾሟበፊት ጳጳሳት በግብፅ ይሾሙላት እንደነበር በጥናቱተጠቅሷል። ያ ዘመን ግብፅን ተጽዕኖ ፈጣሪ እንድትሆንአስችሏታል ይላል። በኢህአዴግ ዘመነ መንግሥትምኢትዮጵያና ግብፅ እንደቀድሞው ባይሆንም ሰላማዊየትብብር መንፈስ እንዳላቸው ይገልጻል። አሁንምሃይማኖታዊ ቅርርቦችን በማጠናከር ለናይል ድርድርመጠቀም በሚያስችል ወሳኝ ሰዓት ላይ እንዳሉ ጥናቱያመላክታል።እስሌማን እንደሚለው በትግራይና በኢትዮጵያየተለያዩ ክፍሎች ሁሉ ከዚህ በፊት ትምህርት ቤቶችንናየጤና ተቋማትን እያሠሩ እንደነበር በመጥቀስ አሁንምይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል አንዱ አማራጭ እንደሆነጥናቱ ይጠቅሳል።ጥናታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ለምሳሌ ኦሮሚያ ክልልከሰማኒያ በመቶ በላይ ሙስሊም ማህበረሰብ አለ ይላል።ቤኒሻንጉልን፣ አፋርን፣ ሶማሌንም እያነሳ ሙስሊሙማህበረሰብ አብላጫ አሃዝ እንዳለው ይጠቅሳል። ያምሆኖ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ፖለቲካዊ ተሳትፎው አናሳነው ይላል።ጽሑፉ አሁንም እንዲህ አይነት ጥያቄዎችንየሚያነሱ አካላት መኖራቸውን አትቶ የኢትዮጵያፖለቲካ ከለሩ እስላማዊ እስካልሆነ ድረስ የግብፅ ፍላጎትሊሳካ አይችልም ይላል። የተለያዩ ቅንጥብጣቢዎችንገጣጥመን ስንመለከት ግብፅ ሃይማኖትን መሰረት አድርጋኢትዮጵያን የማተራመስ እቅድ እንዳላት እንረዳለን። በጣም የተቀናጀና የተናበበ ነገር እንዳለም የሚያሳዩ ነገሮችአሉ።ሌላው የውጭ ተራድኦ ድርጅቶች ይዘው የሚመጡትተልዕኮ ነው። ከሌሎች አገራት ተሞክሮ ስናይ በእነዚህድርጅቶች የሚደረገው ድጋፍ ሰዎችን በተለይምወጣቶችን በገንዘብ እያማለሉ የራሳቸውን ፍላጎትለማሳካት ሲጠቀሙበት ነው። መንግሥት ይህን የሚገታየህግ አሠራር ቢኖረው ችግሩን ማቅለል ይቻላል ብሏል።ጋዜጠኛ እስሌማን ወጣቱ ምንም አይነት ጥያቄቢኖርበት መፍታት ያለበት በሀገር ውስጥ አካሄዶች እንጂ የውጭ ኃይሎች በቀየሱለት መንገድ ሊሆን እንደማይገባ ይገልጻል።መንግሥትም የውይይትና የምክክር መድረኮችን እያዘጋጀአስቀድሞ ችግሮችን መፍታት እንዳለበት ይጠቁሟል።
▪️”ወጣቱ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በሀገር ውስጥ አካሄዶች እንጂ የውጭ ኃይሎች በቀየሱለት ሊሆን እንደማይገባ፤ መንግሥትም ለጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ መስጠትና አስቀድሞም ችግሮችን መፍታት እንዳለበት ይጠቁሟል።”