
ወደ አማርኛ የተመለሰውን ታነቡት ዘንድ ቀርቧል።
HR6600 ረቂቅ ህግ፥ ይፋዊ ያልሆነ ትርጉም – American Ethiopian Public Affairs Committee – AEPAC
“በኢትዮጵያ መረጋጋት፥ ሰላምና ዴሞክራሲን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶችን ለመደገፍ
HR6600 ረቂቅ ህግ
በመወሰኛና (Senate) የህዝብ ተወካዮች ም/ቤቶች (House of Representatives) በተካሔደው የአሜሪካ ም/ቤት እንዳፀደቀው፥
ክፍል 1፡ አጭር ርዕስ፥
ይህ ረቂቅ ህግ (ድንጋጌ) በኢትዮጵያ ሰላም፥ መረጋጋትና ዴሞክራሲንለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶችን መደገፍ
ክፍል 2፡ የፖሊሲ መግለጫ፥
1ኛ/ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያገኙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፥ በጦርነት ወቅትና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፥ የዘር ማጥፋት እና ሌሎች አረመናዊ (atrocities) ተግባሮችን ለማቆም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ፥
2ኛ/ በኢትዮጵያ መረጋጋት እንዲሰፍንና ግጭት እንዲቆም ሁሉንም የዲፕሎማሲያዊ ፥ ልማታዊና ህጋዊ መንገዶችን መጠቀም፥
3ኛ/ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያገኙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፥ በጦርነት ወቅት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን፥ የሰብዓዊ ወንጀል፥ የዘር ማጥፋትና ሌሎች በኢትዮጵያ የሚታዩ አረመንያዊ ተግባሮችን የፈጸሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ፥
4ኛ/ ሰላማዊ፥ ዴሞክራሲያዊና አንዲት ኢትዮጵያን (unified Ethiopia) ለማምጣት ሁሉ-አቀፍ ሀገራዊ ውይይትን መደገፍ፥
ክፍል 3፥ ዴሞክራሲን መረጋጋትንና የሰባአዊ መብትን ለመጠበቅና ለመርዳት የወጣ ስልት፥
a) አጠቃላይ (General)
የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት አስተዳዳሪ፥ ከገንዘብ ሚ/ር፥ እና ከሌሎች የፈዴራልና ሌሎች ወኪሎች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች እንዲቆሙ የሚደረገውን ጥረት ለመርዳት፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፥ የጦር ወንጀሎች፥ ሰብዓዊ ወንጀሎች፥ ዘር ማጥፋትና ሌሎች አረመናዊ ተግባሮች የፈፀሙ ተጠያቂ እንዲሆኑና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ፥ ሰብዓዊ መብቶችና እርቅ እንዲሰፍን ማድረግ ነው።
b) መሠረታዊ ጉዳዮች (Elements)
በንዑስ ክፍል የተጠቀሰውን ስልት ተግባራዊ ለማድረግ የሚከተሉትን ዕቅዶች ማካተት ያስፈልጋል፥
ከተባበሩት መንግሥታት፥ ከአፍሪካ ህብረት፥ ከአውሮፓ ህብረት፥ እና ከሌሎች ክልላዊ አካላት፥ ከሀገሮችና ከዓለም አቀፍ ወዳጆች ጋር በመሆን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ማራመድ
በኢትዮጵያ በሚካሄደው ጦርነትና በሌሎች ግጭቶች ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች፥ ስደተኞችን፥ የተጋለጡ ህብረተሰብ፥ በግል ከመኖሪያቸው በሃይል የተፈናቀሉ ሰዎችን መርዳትና፥ ስር የሰደደ (acute) የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ያልተስተጟጎለ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስ ማድረግ
በኢትዮጵያ የሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች እንዲቀጥሉ በማሰብና በግጭቱ ለሚገኙ ለየትኛውም ወገን ከውጭ የሚመጣ ቁሳዊ ዕርዳታን መለየትና እንዳይደርሳቸው ማድረግ (identify)
በኢትዮጵያ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ሰብዓዊ መብቶች፥ ሰብዓዊ ወንጀሎች፥ የዘር ማጥፋት፥ የጦር ወንጀሎችንና አሬመናዊ ተግባሮችን የፈፀሙ ተጠያቂ እንዲሆኑና ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲጠናከር ማገዝ
በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞችን፥ የአሜሪካ ዜጎች፥ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው (Legal permanent residents in Ethiopia)፥ እንዲሁም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ እነዚህን ሰዎች ከሃገር ለማስወጣት አማራጭ ጥብቅ ዕቅድ መኖሩን ማረጋገጥ
በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች እንዲራዘሙ በማሰብ ከአሜሪካ ውጭ የሚመነጭ የጥላቻ ንግግር፥ በኢትዮጵያ የተዛባ ወሬዎች ይዞታቸውና ውጤታቸው እንዲቀንስ ከማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር መታገል
በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ብጥብጥ (violence) ለማስቆምና ሰላምን ለመመስረት የሁሉንም ብሄረሰቦች (all ethnicities)፥ የሲቪል ማህበረሰብ (civil society) ሴቶችንና ወጣቶችንም ጨምሮ፥ የግጭት አፈታት፥ ሁሉ አቀፍ ውይይትና እርቀ ሰላም እንዲወርድና ፍሬያማ በሆነ መንገድ እንዲሳተፉ ማድረግ
በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች ሳቢያ የተጎዱ ሰዎችን በግጭት አፈታትና (psychosocial) በማህበራዊ ሰነ አዕምሮ (conflict resolution) ግንባታ መርዳት፥ ይህም የርስ በርስ ጦርነቱንና ሌሎች ግጭቶችን የሚያራምዱበትንም ትንተና ይጨምራል
በኢትዮጵያ በተካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ወቅት የወደሙትን የጤናና ሌሎች ከጤና ጋር የተገናኙ ተቓሞችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደአግባብነቱ (as appropriate) ማገዝ
በኢትዮጵያ የሚታየውን የርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶችን የሚያካሄዱትን አመራሮች ሂደት በመተንተን (development and analysis) ኢትዮጵያ የተወሰነ ዕርዳታ እንድታገኝ፥ ከዴሞክራሲና አስተዳደር ጋር የተዛመደ የኤኮኖሚ እድገት መለኪያዎችንና መመዘኛዎችን ማውጣት እና
በዘር፥ በሃይማኖት፥ በፖለቲካ ወይም በጂኦግራፊ ቁርኝት ( geographic affiliation) ወይም ከአሜሪካ ጋር ወይም በኢትዮጵያ በሚገኙ ተቛሞች ውስጥ ለአሜሪካ በሚሰሩ ላይ የሚደርሰውን ማስፈራራት ለማስቀረት (address)
(c) ሪፖርት፥
ይህ ድንጋጌ ስራ ላይ በዋለ 180 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ለምክር ቤቱ አግባብ ላለው ኮሚቴ በንዑስ ክፍል (a) በተጠቀሰው መሠረት ስልት (strategy) የያዙ መሆኑን የሚገልጽ ሪፖርት ያቀርባል
d) የተጠያቂነት ሂደትን የሚያሳይ ሪፖርት
ይህ ድንጋጌ ስራ ላይ በዋለ 180 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከዚያ በሗላ ለአምስት ዓመታት በየ 180 ቀኑ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በዓለም አቀፍ የታወቁ ሰብዓዊ መብቶች፥ በጥቅል የጣሱ የጦር ወንጀሎች፥ አረሜናዊ ተግባሮችን የፈፀሙ ግለሰቦችን ሁኔታ ሂደት ለም/ቤቱ አግባብ ላለው ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባል።
ክፍል 4 ፡ ሰለም፥ መረጋጋትና ተጠያቂነትን አስመልክቶ የሚወሰዱ የተግባር እርምጃዎች፥
የሁለትዮሽ ማዕቅቦች፥ (Bilateral Sanctions)
አጠቃላይ (in general)
ከላይ በምዕራፍ (paragraph2) የተጠቀሰውን ማዕቀብ፥ ፕሬዘዳንቱ በማናቸውም የውጭ ሀገር ሰው (foreign person) ላይ መጣል ይችላል።
(A) በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የርስ በርስ ጦርነት ወይም የሌላ ግጭት ተኩስ እንዲቆም፥ ጦርነት ወይም ሌላ ግጭቶችን ለማስቆም በድርድር የተደረሰበትን ስምምነት (negotiated settlement) ለማቅለል፥ ለማቃለል መሞከር ወይም ለማቃለል መፈለግ፥
(B) በኢትዮጵያ ያለውን የርስ በርስ ጦርነት ወይም ሌላ ግጭት እንዲስፋፋ ወይም እንዲቀጥል በተግባር ወይም በፖሊሲ ተባባሪ የሆነ ተጠያቂ ይሆናል።
(C) በኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ እውቅናን ያገኙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፥ የጦር ወንጀሎች፥ በሰብዓዊነት ላይና ወይም የዘር ማጥፋት ወይም ሌላ አረመናዊ ተግባር የፈጸመ፥
(D) በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ወይም ግጭት የተነሳ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የታቀደውን አቅርቦት እንዳይደርስ፥ እንቅፋት የሆነ፥ ያዘገየ፥ ወይም አቅጣጫ የቀየረ፥ ወይም ለማዘግየት፥ ለማደናቀፍ፥ ወይም አቅጣጫ ለማስቀየር የከጀለ፥
(E) በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካ ህብረት ሰብዓዊ ወይም በጎ አድራጊ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ጥቃት ያቀደ፥ የመራ ወይም የፈጸመ፥ እና
(F) __
(i) በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ወይም ግጭት ውስጥ አውቆ (knowingly engaged) የተሳተፈ ወይም በቁስ (materially) ዕርዳታ ያደረገ፥
(ii) በተባበሩት መንግሥታት ብሔራዊና ይፋዊ የጦር መሣሪያ (conventional arms) ምዝገባ ማዕቀፍ ውስጥ የተካተተ መሣሪያ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ወይም ግጭት ውስጥ ላሉ ለማናቸውም ወገን የሰጣ እንደሆነ፥ ወይም
(iii) በአንቀጽ አንድ በተጠቀሰው መሠረት በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ወይም ሌሎች ግጭቶች ለዘለቄታው እንዲቆይና እንዲራዘሙ ማናቸውም የቴክኒክ ሥልጠና፥ የገንዘብ ምንጭ፥ ወይም አገልግሎት፥ ምክር፥ሌላ አገልግሎት ውይም ለአቅርቦት የተዛመደ ዕርዳታ (assistance related to supply) ለሽያጭ፥ ለዝውውር፥ ለማምረት፥ እድሳት ወይም በጦር መሣሪያ ለመጠቀም፥ መለዋወጫ ዕቃ፥ ተጟዳኝ ቁስ (related material) የሰጠ እንደሆነ፥
የተገለጹ ማዕቀቦች (Sanctions Described)፥
በአንቀጽ አንድ መሠረት በውጭ ሀገር ሰው (foreign person) ላይ የሚጣሉት ማዕቀቦች የሚከተሉት ናቸው፥
ንብረትን ማገድ ( Blocking of Property)፥ በዓለም አቀፍ የአስቸዃይ የኤኮኖሚ ሥልጣን ህግ (50 U.S.C. 1701 et.Seq) መሠረት ፕሬዘዳንቱ በህጉ የተሰጠውን ሥልጣን በሙሉ በተግባር ለማዋል ሲያስፈልግ የውጭ ሀገር ሰው ሙሉ ንብረት ማናቸውንም ግብይት (all transactions) በሁሉም ንብረቶች ላይ ወለድ፥ ይህ ንብረትና ወለድ የሚገኘው አሜሪካ ውስጥ ከሆነ፥ ወደ አሜሪካ የገባ እንደሆነ ወይም በአሜሪካዊ ሰው ( United States Peroson) እጅ ወይም ቁጥጥር ስር የገባ እንደሆነ
የውጭ ዜጎች (Aliens) ለመግቢያ፥ ወይም የይቅርታ ቪዛ የሚከለከሉበት
(i) ቪዛ፥ ፈቃድና ይቅርታ፥
በአንቀጽ አንድ የተገለፀው የውጭ ዜጋ
(I) ወደ አሜሪካ የማይገባ፥
(II) ወደ አሜሪካ ለመግባት ቪዛም ሆነ ወይም ሌላ ሰነድ ለማግኘት ብቁ ያልሆነ፥
(III) በስደተኝነትና ዜግነት ህግ ( 8 U.S.C. 1101 et seq) መሠረት ወደ አሜሪካ ለመግባት ብቁ ያልሆነና ማናቸውንም ዓይነት ጥቅማ ጥቅም ማግኘት የማይችል
(ii) የተሰጠን ቪዛ መሰረዝ፥
አጠቃላይ
በአንቀጽ አንድ እንደተጠቀሰው ለውጭ ዜጋ የተሰጠ ቪዛ ወይም ሌላ የመግቢያ ሰነድ የተሰጠበት ቀን ግምት ውስጥ ሳይገባ ሊሰረዝ ይችላል
ወዲያውኑ ተፈጻሚነት (immediate effect)
በንዑስ አንቀጽ አንድ ስር የተጠቀሰው ሰነድ የመሰረዝ
(aa) ወድይያውኑ ስራ ላይ ይውላል
(bb) በውጭ ሀገር ዜጋ እጅ ውስጥ የሚገኘው ማናቸውም ዓይነት ያልተቃጠለ ቪዛ ወይም ሌላ የመግቢያ ሰነድ ወዲያውኑ ይሰርዛል
ልዩ ሁኔታዎች (Exceptions)፥
ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ዕቃዎች አስመልክቶ ያለው ልዩ ሁኔታ፥
አጠቃላይ
በዚህ ንዑስ ክፍል መሠረት ሥልጣን ወይም ዕቀባ ለመጣል ያለው መስፈርት ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ማዕቀብ ለመጣል የተሰጠን ሥልጣንን ወይም መስፈርትን አያካትትም
(ii) የዕቃ ትርጉም
በዚህ አንቀጽ መሰረት “ዕቃ” የሚለው ቃል ማናቸውም ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ሰራሽ ነገር፥ ቁስ፥ አቅርቦት ወይም በፋብሪካ የተመረተ የምርመራና የፍተሻ ዕቃዎችን Cምr፥ ነገር ግን የቴክኒክ መረጃዎችን (technical data) አይጨምርም፥
አንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፥ ሌሎች ዓላም አቀፍ ተቛሞችና (other international entities)፥ የህግ ማስከበር ዓላማዎችን ይፋዊ እንቅስቃሴ አስመልክቶ የወጣውን ስምምነት ስለመቀበል ያለ ልዩ ሁኔታ (exception)፥
ወደ አሜሪካ ለመግባት የተፈቀደለት የውጭ ሀገር ዜጋ በአንቀጽ (2) (B) የተጠቀሰው ዕቀባ ተፈጻሚ አይሆንበትም።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፥ በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌሎች አግባብ ባላቸው የፈደራሉ ክፍል መሪዎች ወይም ወኪሎች፥አሜሪካ ከተባበሩት መንግስታት ጋር፥ ከሌሎች ዓልም አቀፍ ድርጅቶች ወይም ተቕሞች (entities) ወይም አሜሪካ የገባችበት ሌሎች ዓለም አቀፍ ግዴታዎችን ማክበር አስፈላጊ ነው ወይም
ህግ የማስከበር ዓላማን ወደፊት ታራምዳለች
(4) ትግበራ ፥ ቅጣቶች፥
ትግበራ (implementation)፥
ይህን ንዑስ ክፍል በተግባር ለመተርጎም ፕሬዘዳንቱ በዓለም አቀፍ አስቸዃይ የኤኮኖሚ ሥልጣን ህግ (International Emergency Economic Power) (50 U.S.C 1702 እና 1704) በክፍል 203 እና 205 ስር የተሰጠውን ሥልጣን በሙሉ ተግባራዊ ያደርጋል
ንብረትን ከመገደብ ጋር የተያያዙ ቅጣቶች፥
ይህን ንዑስ ክፍል ወይም ማናቸውንም ህጎች፥ ፈቃድ (license) ወይም ድንጋጌ (order) የጣሰ፥ ለመጣስ የሞከረ፥ ለመጣስ አድማ ያካሄደ፥ ወይም ለጥሰቱ መንስኤ የፈጠረ፥ በዓለም አቀፍ አስቸዃይ የኤኮኖሚ ሥልጣን ህግ (International Emergency Economic Power Act) (50 U,S.C. 1705) በክፍል 206 በንዑስ ክፍል (6) እና (C) መሠረት የሚቀጣ ይሆናል፥ ይህም በዚያው ክፍል በንዑስ ክፍል (a) በተጠቀሰው ህግ ውስጥ ተግባር እንደፈጸመ ሰው እኩል የሚቀጣ ነው።
(C) የማብቂያ ጊዜ (Termination)፥
በአንቀጽ (2) ዕገዳ ተጥሎበት የነበረ ሰው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንቀጽ (1) በተጠቀሰው እንቅስቃሴ ውስጥ የማይሳተፍ መሆኑን የሚኒስቴሩ መ/ቤት ከወሰነና ለመሚለከታቸው ኮሚቴዎች ካሳወቀ ከሰላሳ ቀናት በሗላ ዕገዳው አይመለከተውም።
(D) የማዕቀቦች ዕገዳ (Suspension of Sanctions)።
(i) አጠቃላይ
በኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት ወይም ሌላ ግጭቶች ውስጥ ያሉ ወገኖች የተኩስ ማቆም ስምምነት ከደረሱና ሁላአቀፍ የፖለቲካ ውይይት ለማካሄድ መስማማታቸውን ፕሬዘዳንቱ በዚህ ንዑስ ክፍል መሠረት ከዘጠና ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ዕቀባውን በሙሉ ወይም በከፊል ማገድ ይችላል።
(ii) ማሳሰቢያ ይስፈልጋል (Notification Required)
በአንቀጽ (1) እንደተገለጸውና ፕሬዘዳንቱ የተጣለውን ዕቀባ ማገዱን ከወሰነ በሰላሳ ቀናት ውስጥ የሚመለከታቸው የምክር ቤቱ ኮሚቴዎች መወሰኑን የሚያሳይ ማስታወሻ ይልካል።
(iii) ማዕቀቦችን እንደገና ስለማጽናት
ፕሬዘዳንቱ መስፈርቶች አለመከበራቸውን እንዳወቀ፥ በዚያው አንቀጽ መሰረት ታግዶ የነበረው ዕቀባ እንደገና ስራ ለይ እንዲውል ሊያደርግ ይችላል።
(E) ማንሳት (Waiver)፥
ፕሬዘዳንቱ በአሜሪካ ጥቅም አዃያ ነው ብሎ ከወሰነና ይህንኑ ለሚመለከታቸው የም/ቤቱ ኮሚቴዎች ካሳወቀ በአንቀጽ (1) የተጠቀሰው ሰው በአንቀጽ (2) የተገለፀውን የማዕቀብ ማመልከቻ ሊያነሳው ይችላል።
(F) ብሔራዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ ልዩ ሁኔታ (Exemption to Comply with National Security)፥
የሚከተሉት እንቅስቃሴዎች በዚህ ንዑስ ክፍል መሠረት ማዕቀቡ አይመለከታቸውም።
(i) የ 1947 ዓም የብሔራዊ ደህንነት ድንጋጌ በ 5ኛው ርዕስ ስር እንቅስቃሴዎችን ሰለማሳወቅ ያሉ መስፈርቶች
(ii) ሥልጣን የተሰጠው ማናቸውም የአሜሪካ የደህንነት ወይም ህግ አስከባሪ እንቅስቃሴዎች
(5 ) ትርጟሜዎች፥
በዚህ ንዑስ ክፍል፥
(A) መቀበል፥ ተቀበለ፥ የውጭ ዜጋ ( Admission, Admistted, Alien)
“መቀበል”፥ “ተቀበለ” እና “የውጭ ዜጋ” የሚባሉ ትርጟሜያቸው በስደተኞችና ዜግነት ህግ (8 U.S.C. 1101) በንዑስ ክፍል 101 ውስጥ የተሰጠው ትርጙሜ አላቸው።
(B) የውጭ ሀገር ሰው (Foreign Person)፥ “የውጭ ሀገር ሰው የሚለው ትርጟሜ አሜሪካዊ ያልሆነ ማለት ነው።
(C) እያወቀ (Knowingly)፥ “እያወቀ” የሚለው ቃል ከባህሪይ (Conduct)፥ ከሁኔታ ወይም ከሚታየው ውጤት አዃያ ሲታይ ግለሰቡ ትክክለኛ ዕውቀት አለው ወይም ባህሪይ፥ የሁኔታው ወይም ውጤቱን ያውቃል ወይም ሊያውቅ ይገባል ማለት ነው።
(D ) አሜሪካዊ ሰው (United States Person)፥
አሜሪካዊ የሚለው ቃል ትርጙሜ፥
(i) በዜግነት አሜሪካዊ የሆነ፥ በህጋዊ መንገድ በአሜሪካ በቛሚነት እንዲኖር ፈቃድ የተሰጠው የውጭ ሀገር ሰው ወይም ሌላ ግለሰብ በአሜሪካ ሥልጣን ስር ያለ ወይም በአሜሪካ ህግ መሠረት የተቛቛመ ድርጅት ወይም
(ii) በአሜሪካ ህግ መሠረት የተቓቓመ ድርጅት ወይም በማናቸውም ሥልጣን የተቓቓመ የውጭ ሀገር ቅርንጫፉን ጭምር፥
(b) ዘርፈ ብዙ ማዕቀቦች ( Multilateral Sanctions)፥
የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከገንዘብ ሚ/ር እና ከንግድ ሚ/ር ጋር በመመካከር እንዲሁም ከተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ም/ቤት፥ ሌሎች አባል ሃገሮች፥ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት (NATO)፥ የአውሮፓ ህብረት፥ የአፍሪካ ህብረትና ሌሎች አግባብ ያላቸው አካሎች እንዲሳተፉ በማድረግ በንዑስ ክፍል (a) (1) መሠረት በተጠቀሰ ሰው ላይ የተቀነባበረ ዘርፈ ብዙ ማዕቀቦች ለመጣልና በውጭ ንግድ እንቅስቃሴን መቆጣጠር፥
(c) የመከላከያና ጥንድ ጠቀሜታ ያላቸው መሣሪያዎችን ወደ ውጭ የመላክ ውሱንነት ( Limitation of Export of Defense and Dual Use Items)፥
ድርብ ጠቀሜታ ያላቸው ዕቃዎች
በአንቀጽ (ii ) በተጠቀሰው መሠረት የንግድ ሚ/ር ከ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር በመተባበር በክፍል 1754 (C)(1)(A) ወደ ውጭ በሚላኩ ዕቃዎች ቁጥጥር ማማሻያ ደንብ 2018 ( 50 U.S.C.4813 (C)(1)(A) መሠረት ወደ ውጭ መላክ (Re-export) ፥ መልሶ መላክ ወይም በሀገር ውስጥ ዝውውር ተደርጎ ወደ ኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ ለማዛወር ፈቃድ ያስፈልግ ወይም አያስፈልግ እንደሆነ ይወስናል።
(2) የመከላከያ ዕቃዎች፥
በአሜሪካ የጦር መሣሪያ ወደ ውጭ የመላኪያ የቁጥጥር ደንብ (22 U.S.C. 2778 (a)(1) በአሜሪካ የጦር መሣሪያ ዝርዝር በክፍል 38 (a)(1) መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ ለመላክ ምንም ዓይነት ፈቃድ ላይሰጥ ይችላል (No license may be issued)
ክፍል 5 : በደህንነት ዕርዳታ ላይ ያለ ውሱንነት (Limitation on Security Assistance)፥
(a) አጠቃላይ፥
ይህ ድንጋጌ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በውጭ ዕርዳታ የ1961 ዓም ደንብ (22 U.S.C. 2151 et.seq) ወይም በአሜሪካ ህግ በርዕስ 10 በምዕራፍ 16 የተጠቀሰው ለኢትዮጵያ የደህንነት ኋይሎች በዕርዳታ ለመስጠት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በንዑስ ክፍል (b) የተጠቀሱት ሁኔታዎች መሟላታቸውን አረጋግጦ ለሚመለከታቸው የምክር ቤቱ ኮሚቴዎች ካሳወቀ እስከ ሰላሳ ቀን ድረስ ለመስጠት የገተባው ቃል የሚታገድ ይሆናል።
(b) ግልጽ የሆኑ ሁኔታዎች (Conditions Described)፥
በዚህ ንዑስ ክፍል የተጠቀሱት ግልጽ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፥
(1) የኢትዮጵያ መንግሥት ከእርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች ጋር ግንኙት ያላቸውን ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ማቆሙ፥
(2) የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትክክለኛው ሁሉ አቀፍ ሀገራዊ ውይይት ለማካሄድ የሚያስችል እርምጃ መውሰዱ፥
(3) የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብትን በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ህግን ስለማክበርሩ የወሰዳቸው እርምጃዎች፥
(4) የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስ ባልተገደበ መንገድ በቀጣይነት ክፍት ማድረጉ፥
(5) የኢትዮጵያ መንግሥት የርስ በርስ ጦርነቱና በሌሎች ግጭቶች ወቅት ተአማኒነት ያላቸው የጦር ወንጀሎች፥ የሰብዓዊ ወንጀሎች እና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ክሶችን ገለልተኛ በሆነ አካል እንዲጣራ መንግሥት ተባብርዋል፥
(c) ልዩ ሁኔታዎች (Exceptions)፥
የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ዓላማን የሚደግፍ በንዑስ ክፍል (a) የተጠቀሰው የዕገዳ መጠን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር ህግ ለማስከበር የድንበር ጥበቃ ማለትም በየብስ፥ በባህር፥ በዓየር መግቢያ በሮች ወይም ለሌሎች እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ የተፈቀዱትን መሣሪያዎች አይመለከትም።
(d) ሪፖርት፥
ይህ ድንጋጌ ካለፈበት ቀን ጀምሮ በንዑስ ክፍል (a) የተወሰነ ዕርዳታ በሚለው መሠረት፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአስራምስት ቀናት ባልበልጠ ጊዜ የታገደውን ዕርዳታ ዝርዝር ለምክር ቤቱ ለሚመለከታቸው ኮሚቴዎች ሪፖርት ማቅረብ አለበት።
(e) ማንሳት / መሰረዝ (Waiver)
በንኡስ ክፍል (a) እና ሌሎች አግባብ ባላቸው ህጎች ዕገዳ የተጣለበትን ለማንሳት ፕሬዘዳንቱ ከምክር ቤቱ በሚያገኘው ማሳሰቢያ መሠረት
(1) የዕገዳው መነሳት ከአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አዃያ መሆኑን ያረጋግጣል
(2) የተነሳው ዕገዳ ከአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አዃያ መሆኑን ከበቂ ምክንያት ጋር እገዳው በተነሳ አስራ አምስት ቀኖች ባልበለጠ ጊዜ ለምክር ቤቱ ለሚመለከታቸው ኮሚቴዎች ማስታወሻ የቀርባል።
ክፍል 6 : በዓልም አቀፍ የገንዘብ ተቛሞች በኩል የሚደረግ የዕርዳታ ውሱኑነት፥
(a) ገደብ (Restrictions)፥
የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ለበእያንዳንዱ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቛም ለሚገኙ የአሜርካ ዋና ዳይሬክተሮች መመሪያ ይሰጣል
ለኢትዮጵያም ሆነ ለኤርትራ መንግሥታት የሚሰጥ ምንም ዓይነት ብድር ወይም የገንዘብም ሆነ የቴክኒክ ዕርዳታ እንዳይራዘም የሚመለከታቸው ድርጅቶች የአሜሪካንን ድምጥ በመጠቀም ሊቃወሙ ይችላሉ
በኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላምና ሰብዓዊ መብት ለማካሄድና ሰላም ለማስፈን ከሌሎች ቁልፍ ከሆኑ ለጋሽ ሀገሮች ጋር በመሆን የተቀነባበረ ፖሊሲ ያወጣል….
ለሰብዓዊነት ሲባል ልዩ ሁኔታ (Exception for Humanitarian Purposes)፥
ለሰብዓዊ ዕርዳታ ተብሎ የ ኮቪድ 19 (Covid-19) ወረርሽኝን ለማስወገድ፥ ክትትል ለማድረግ እና ለመቓቓም ወይም ሌላ በዓለም የጤና ድርጅት አማካኝነት ዓለም አቀፍ የህዝብ የጤና አስቸኻይ ችግር ተብሎ ለተመዘገበ ሌላ ተላላፊ በሽታ፥ የበሽታ ስጋት (disease threat) የሚውል ማናቸውም ብድር ወይም የገንዘብ ወይም የቴክኒካል ዕርዳታን አይመለከትም።
(c) የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎትን በቀጥታ የሚመለከት ፕሮጀክትን ስለማንሳት (waiver for projects that directly support human needs)፥
የገንዘብ ሚኒስቴር በንዑስ ክፍል (a) (1) የተጠቀሰው ማመልከቻ ሊነሳ ይችላል ብሎ ለምክር ቤቱ ለሚመለከታቸው ኮሚቴዎች በጽሑፍ ውሳኔውን ካሳወቀና ይህም የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የዕቀባው መነሳት የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቱን በቀጥታ የሚመለከት ፕሮጀክት ነው ብሎ እኩል ያሳወቀ እንደሆነ የገንዘብ ሚኒስቴር በንዑስ ክፍል (a) (1) የተጠቀሰውን ማመልከቻ ሊያነሳው ይችላል።
(d) መቛረጥ (Termination)፥
የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ለምክር ቤቱ ለሚመለከታቸው ኮሚቴዎች በንዑስ ክፍል (a) (1) የተጠቀሰው የኢትዮጵያ መንግሥትና የኤርትራ መንግሥት አይመለከታቸውም ብሎ ካሳወቀ ከሰላሳ ቀናት በሗላ፥
በኢትዮጵያ ከእርስ በርስ ጦርነትና ከሌሎች ግጭቶች ጋር የተገናኙ ሌሎች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ቆመዋል
እውነተኛ በስምምነት ሁሉ_- አቀፍ ወደ ሆነ ብሔራዊ ውይይት የሚወስድ እርምጃ ወስዿል
ለሰብዓዊ ዕርዳታ መተላለፍ ያልተጛጎለ ማለፊያ ፈቃድ ስጥትዋል እንዲሁም
በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች በተደረጉበት ወቅት ተአማኒነት ያላቸው የጦር ወንጀሎች፥ በሰብዓዊነት ላይ የተከሰቱ ወንጀሎች፥ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች የሚባሉ ገለልተኛ በሆነ አካል እንድጣራ ከተባበረ፥
(e) ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቛሞች ትርጛዋሜ (Definition of International Financial Institutions)
በዚህ ክፍል ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቓሞች ማለት የሚከተሉትን ያካትታል፥ the International Monetary Fund, International Bank for Reconstruction and Development, European Bank for Reconstruction and Development, International Development Association, International Finance Corporation, Multilateral Investment Guarantee Agency, African Development Bank, African Development Fund, Asian Development Bank, Inter-American Development Bank, Bank for Economic Cooperation and Development in the Middle East and North Africa, and Inter-American Investment Corporation.
ክፍል 7 ፥ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ገንዘብ ኮርፖሬሽን የሚሰጠው የዕርዳታ ውስንነት (LIMITATION ON SUPPORT PROVIDED BY UNITED STATES INTERNATIONAL DEVELOPMENT FINANCE CORPORATION)፥
አጠቃላይ፥
በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ፕሮጀክቶች የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ገንዘብ ኮርፖሬሽን (The United States International Development Finance Corporation) መዋዕለ ንዋይ ወደልማት ድንጋጌ በተሻለ ጥቅም (Better utilization of investment leading to development act) በሚል ርዕስ II ስር በ2018 (22 U.S.C. 962 et.sqa) መሠረት ዕርዳታ ላይሰጥ ይችላል።
(b) ማቓረጥ (Termination)፥
የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በንዑስ ክፍል ( ኣ) የተጠቀሰው እገዳ አይመለከተውም ብሎ ከወሰነ ለሚመለከታቸው የምክር ቤቱ ኮሚቴዎች ካሳወቀ ከ 30 ቀናት በሗላ፥
የኢትዮጵያ መንግሥት፥
ከርስበርሱ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች ገርና የተገናኙ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በሙል ካቆመ፥
ወደ ስምምነት የሚያመራ ትክክለኛና ሁሉ አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እርምጃ ከወሰደ፥
ለሰብዕዊ ዕርዳታ መተላለፊያ የሚሆን ያልተስተጛጎለ ፈቃድ የሰጠ እንደሆነ
በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነትና ሌሎች ግጭቶች ጊዜ በዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጣቸውና ተአማኒነት ያላቸው የጦር ወንጀሎች፥ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፥ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ የተከሰቱ ወንጀሎችና የዘር ማጥፋት ክሶችን በገለልተኛ አካል እንዲመረመር የተባበረ እንደሆነ
(c) ማንሳት፥
በንዑስ ክፍል (a) የተጠቀሰውን ድንጋጌ ፕሬዘደንቱ ሊያነሳው የሚችለው፥
ከአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አዃያ ነው ብሎ ከወሰነና
ድንጋጌው የተነሳው ከአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አዃያ መሆኑን በመግለጽና ከተነሳ ከ 15 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለም/ቤቱ ለሚመለከታቸው ኮሚቴዎች ማሳወቅ አለበት።
ክፍል 8፥ ተጠያቂነትን ለማገዝ (Support for accountability)፥
አጠቃላይ ፥
በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርናትና ሌሎች ግጭቶች ወቅት የተፈጸሙ አረመኔያዊ ተግባሮችን በሚመለከት ማስረጃዎቹን ለመጠበቅ፥ ተጠያቂነትን ለመከታተል፥ በዓላም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ሰብዓዊ መብቶች፥ የጦር ወንጀሎች፥ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፥ እና የዘር ማጥፋት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ህግ (International humanitarian law) በኢትዮጵያ መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በገንዘብ፥ በቴክኒክ፥ እና በዲፕሎማሲ መንገድ እገዛ ለማድረግ ፕሬዘደንቱ ስልጣን ተሰጥቶታል።
(b) የኢንፎርሜሽን ድንጋጌ (Provision of information)፥
ዓላም አቀፋዊ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብዓዊ መብት ማለትም፥ የጦር ወንጀለኞት፥ ዘር ማጥፋት እና ሌሎች አረመናዊ ተገባሮች በዚህ ክፍል መሠረት የፈጸሙና ተአማኒነት ያለው የወንጀል ክስ የቀረበበት ማናቸውም ግለሰብ ክስ እንዲመስረትበት ፕሬዚደንቱ በመንግሥት እጅ ያለውን ኢንፎርሜሽን ለማጋራት ሥልጣን ተሰጥቶታል።
ክፍል 9 : ሪፖርት፥
አጠቃላይ፥
የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከገንዘብ ሚ/ር ጋር በመመካከር ይህ ደንብ ስራ ላይ በዋለ 180 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለምክር ቤቱ ለሚመለከታቸው ኮሚቴዎች
የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥት እና የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር፥ ሌሎች የታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖች ወይም ግንኙነት ያላቸው ከፍተኛ አመራር የሚሰጡ አካሎች
(A) በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኙ ሰብዓዊ መብቶች፥ የጦር ወንጀለኞች፥ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጽሙ ወንጀሎች፥ የዘር ማጥፋት እና ሌሎች አረመናዊ ተግባሮች በኢትዮጵያ እንዲካሄድ አመራር የሰጡ፥ የተሳተፉ፥ ወይም ሰብዓዊ መብት እንዲጣስ ያዘዙ፥
(B) በኢትዮጵያ ሰላማዊ ሰዎችን፥ የህዝብ መሠረተ ልማቶችን፥ የህክምና ተቛሞችን፥ ዕድሜአቸው ያልደረሱ ወጣቶችን በጦር ሃይል ወይም መሣሪያ ከያዘ ቡድን ጋር እንዲሰለፉ ያዘዘ፥ አመራር የሰጠ ወይም ኢላማ እንዲሆኑ ያደረገ፥
በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ወይም ለሌላ ግጭት ለየትኛውም ወገን የመሣሪያ ሽያጭ፥ በገንዘብ የሚረዳ ወይም ሁኔታዎችን የሚያመቻች፥ ቻይና፥ ኢራን፥ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ፥ ሩሲያ፥ ግብጽ፥ ሱዳንና፥ ቱርክ ወይም ሌላ የወጭ ሃይሎች ያላቸውን ተግባርና ተሳትፎ መግለጽ
በምዕራፍ (1) የተገለጹት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ወይም በምዕራፍ (2) የተጠቀሱት የውጭ ሃይሎች ያላቸው ከፍተኛ ንብረትን ግምታቸውና በየትኛው የውጭ የገንዘብ ተቓሞች ውስጥ እንዳሉ እንዲታወቁ ማድረግ
በኢትዮጵያ በሚካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ወይም ሌላ ግጭት ውስጥ ካሉት ለየትኛውም ወገን እያወቀ የመሣሪያ የጦር መሣሪያ ወይም የመግደል ሃይል (Nonlethal equipment) የሌለው መሣሪያ በሶስተኛ እጅ ያዘዋወረ ወይም ሁኔታዎችን ያመቻቹ የውጭ የገንዘብ ተቓሞች እንዲታወቁ
(b) ፎርም (Form)፥
በንዑስ ክፍል (a) የሚጠየቀው ሪፖርት በተከለከለ (Unclassified) ፎርም፥ ነገር ግን የተከለከሉ አባሪ በሚይዝ ፎርም ሊቀርብ ይችላል።
ክፍል 10፡ የሰብዓዊነት፥ የጦር ወንጀልና በዘር ማጥፋት ወንጀሎችን የሚመለከት ውሳኔ
አጠቃላይ:
ይህ ድንጋጌ ስራ ላይ በዋለ ዘጠና ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከሌሎች የፌዴራል ክፍል ሃላፊዎችና ቅድመ አረሜናዊ ተግባር ማስጠንቀቂያ ግብረ ሃይል (Atrocities early warning task force) ተጠሪዎችና እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተምዋጋቾች ድርጅቶች ጋር በመሆን በክፍል 1091 of title 18, U.S.C.) በተገለፀው መሠረት በኢትዮጵያ፥ በኤርትራና ትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (Tigrayan People’s Liberation Front) ወይም ተዛማች በሆኑ ሃይሎች ወይም በጦር ሃይሎች የዘር ማጥፋት፥ የጦር ወንጀሎችና የሰብዓዊ መብት ወንጀሎች መፈፀማቸውን ለምክር ቤቱ ለሚመለከታቸው ኮሚቴዎች በመወሰን ሪፖርት ያቀርባል።
ፎርም
በንዑስ ክፍል (a) እንዲቀርብ በሚጠይቀው ውሳኔ መሠረት ይፋ በሆነ ፎርምና (unclassified form) ህዝብ ሊያገኘው በሚችል፥ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ድረ ገጽ የሚወጣ ሆኖ ይፋ በሆነ አባሪ (unclassified index፥ ነገር ግን ይፋ የሆነ አባሪ (classified annex) በተለይ የቀረበ እንደሆነ ነው።
ክፍል 11፥ ትርጟሜዎች
በዚህ ድንጋጌ፥
የምክር ቤቱ መዳቢ ኮሚቴዎች (Appropriate Congressional Committees)፥
“የምክር ቤቱ መዳቢ ኮሚቴዎች” የሚለው ቃል፥
A) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መዳቢ ኮሚቴዎች (Committee on Appropriation) እና
B) የውጭ ግንኙነትና የመወሰኛው (Senate) ምደባ ኮሚቴዎች ማለት ነው።
በዓለም አቀፍ እውቅናን ያገኙ የሰብዓዊ መብት ጥቅል ጥሰቶች፥
በዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙ የሰብዓዊ መብት ጥቅል ጥሰቶች ማለት፥
የሰዎችን ደህንነት፥ የመኖር መብትና ነፃነት፥ በማሰቃየት፥ በጭካኔ፥ ኢሰብዓዊ ወይም አዋርዶ በመቅጣት፥ ክስ ሰይመሰረትና ፍርድ ቤት ሳይቀርብ በእስር ለብዙ ጊዜ በማቆየት፥ ሰዎች ተጠልፈው እንዲሰወሩ ማድረግ፥ በህቡዕ እስር ቤት ማቆየትና ሌላ ግልጽ በሆኑ ቅጣቶች መቅጣት ማለት ነው።
ክፍል 12፥ መብቂያ (Sunset)
ይህ ደንብና በዚህ ደንብ መሠረት የወጡት ማዕቀቦች በሙሉ ደንቡ ሥራ ላይ ከዋለ ከ 10 ዓመታት በሗላ ያበቃል።
(ትርጉም በአቶ መርድ በቀለ)