ፕሬዝደንት ሙሴቪኒ የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ልጃቸውን የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አገዱ

…ወታደራዊ አዛዡ ሽብርተኝነትን እንደሚደግፍ በይፋዊ ትዊተር ገፁ በመለጠፍ የአሸባሪው ህወሃትን ጥፋት እደግፋለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው…

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቻቸው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ የእገዳ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተሰምቷል። በተለይም የደህንነት እና የውጭ ፖሊሲ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠቡ ያደረጉ ሲሆን ከድርጊቱ እንዲታቀቡ ከተደረጉ ባለስልጣናት መካከል የኡጋንዳ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ዊልሰን ምባዲ እና ልጃቸው የሆነው የኡጋንዳ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሙሁዚ ይገኙበታል።

ፕረዚደንት ሙሴቬኒ በሩዋንዳ ለኮመንዌልዝ የመሪዎች ስብሰባ በቾግም ሲደርሱ የጀግና አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ረቡዕ እለት የአደጋ ጊዜ የሬዲዮ ጥሪ መልእክት እንደተደረገላቸው የኡጋንዳ ወታደራዊ ባለስልጣናት ለዴይሊ ሞኒተር ተናግረዋል።
የአደጋ ጊዜ የራድዮ ጥሪውን ተከትሎ ሙሴቪኒ ከቾግም ወደ ኪጋሊ የነበራቸውን የአይሮፕላን ጉዞ ሰርዘው በተሽከርካሪ እንዲያደርጉ ሆኗልም ያሉት ወታደራዊ ባለስልጣናት ስለ ክስተቱ ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል ተብሏል። በማግስቱ ምሽት 12 ሰአት ላይም ወታደራዊ አመራሮቹ  ለስብሰባ ተጠርተው እንደነበር ነው ዴይሊ ሞኒተር ያስነበበው።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በተመለከተ እንደገለፁት “ማህበራዊ ሚዲያ በራሱ መጥፎ አይደለም፣ ጉዳዩ እንዴት ነው መጠቀም ያለብን የሚለው ነው።” ማለታቸው የተዘገበ ሲሆን አዛዦቹ በሀገሪቱ የውጭ ፖሊሲ እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በማህበራዊ ሚዲያ አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠቡ በመከልከል ከዚህ ውጭ ግን መድረኩን ስለ ስፖርት፣ ስለ ወጣቶች ጉዳዮች፣ ስለ ፖለቲካዊ ርዕዮተ አለም እና ትምህርትን በመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ይጠቀሙ ዘንድ መናገራቸው ተዘግቧል። ሙሴቪኒ ችግሩን የፈጠሩት የትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያ አስተያየቶች እንደሆኑ ለይተው ባይጠቅሱም ትዊተር ላይ ከ 568,000 በላይ ተከታዮች ያሉት ልጃቸው ሌተና ጄኔራል ሙሆዚ በአወዛጋቢ ልጥፎቹ እንደሚታወቅ ዴይሊ ሞኒተር ጠቁሟል።

ከኢትዮጵያ ጉዳይ ጋር በተያያዘም የሙሴቪኒ ልጅ የሆነው ወታደራዊ አዛዥ ባለፉት ወራት ከለጠፋቸው አነጋጋሪ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች መካከል “ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር ውጊያ የገጠሙትን የትግራይ አማፂያን እደግፋለሁ” ሲል የገለፀበትን ዴይሊ ሞኒተር አስታውሷል። ከዚህ በተጨማሪም የካምፓላ እና የኪጋሊ ግንኙነትን በማጣጣል ራስን የሚያሞግስ መልእክቱ እንዲሁም  እና በወርሃ የካቲት ሩሲዬ በዩክሬን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ስታውጅ “አብዛኛው (ነጭ ያልሆኑ) ሰው ልጆች” ሩሲያን ይደግፋሉ” ሲል በትዊተር ገፁ ያሰፈረው ልጥፍ በዘገባው ተወስቷል

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories