Notice: Function _load_textdomain_just_in_time was called incorrectly. Translation loading for the matomo domain was triggered too early. This is usually an indicator for some code in the plugin or theme running too early. Translations should be loaded at the init action or later. Please see Debugging in WordPress for more information. (This message was added in version 6.7.0.) in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-includes/functions.php on line 6131

Deprecated: mb_convert_encoding(): Handling HTML entities via mbstring is deprecated; use htmlspecialchars, htmlentities, or mb_encode_numericentity/mb_decode_numericentity instead in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/fb-instant-articles/vendor/facebook/facebook-instant-articles-sdk-php/src/Facebook/InstantArticles/Transformer/Transformer.php on line 249

Deprecated: mb_convert_encoding(): Handling HTML entities via mbstring is deprecated; use htmlspecialchars, htmlentities, or mb_encode_numericentity/mb_decode_numericentity instead in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/fb-instant-articles/vendor/facebook/facebook-instant-articles-sdk-php/src/Facebook/InstantArticles/Transformer/Transformer.php on line 249

Deprecated: Creation of dynamic property Facebook\InstantArticles\AMP\AMPHeader::$headerBar is deprecated in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/fb-instant-articles/vendor/facebook/facebook-instant-articles-sdk-extensions-in-php/src/Facebook/InstantArticles/AMP/AMPHeader.php on line 51
ፕሬዝደንት ሙሴቪኒ የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ልጃቸውን የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አገዱ

Horn Affairs አፍሪካ ቀንድ

ፕሬዝደንት ሙሴቪኒ የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ልጃቸውን የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አገዱ

By Esleman Abay

July 03, 2022

…ወታደራዊ አዛዡ ሽብርተኝነትን እንደሚደግፍ በይፋዊ ትዊተር ገፁ በመለጠፍ የአሸባሪው ህወሃትን ጥፋት እደግፋለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው…

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቻቸው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ የእገዳ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተሰምቷል። በተለይም የደህንነት እና የውጭ ፖሊሲ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠቡ ያደረጉ ሲሆን ከድርጊቱ እንዲታቀቡ ከተደረጉ ባለስልጣናት መካከል የኡጋንዳ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ዊልሰን ምባዲ እና ልጃቸው የሆነው የኡጋንዳ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሙሁዚ ይገኙበታል።

ፕረዚደንት ሙሴቬኒ በሩዋንዳ ለኮመንዌልዝ የመሪዎች ስብሰባ በቾግም ሲደርሱ የጀግና አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ረቡዕ እለት የአደጋ ጊዜ የሬዲዮ ጥሪ መልእክት እንደተደረገላቸው የኡጋንዳ ወታደራዊ ባለስልጣናት ለዴይሊ ሞኒተር ተናግረዋል።የአደጋ ጊዜ የራድዮ ጥሪውን ተከትሎ ሙሴቪኒ ከቾግም ወደ ኪጋሊ የነበራቸውን የአይሮፕላን ጉዞ ሰርዘው በተሽከርካሪ እንዲያደርጉ ሆኗልም ያሉት ወታደራዊ ባለስልጣናት ስለ ክስተቱ ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል ተብሏል። በማግስቱ ምሽት 12 ሰአት ላይም ወታደራዊ አመራሮቹ  ለስብሰባ ተጠርተው እንደነበር ነው ዴይሊ ሞኒተር ያስነበበው።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በተመለከተ እንደገለፁት “ማህበራዊ ሚዲያ በራሱ መጥፎ አይደለም፣ ጉዳዩ እንዴት ነው መጠቀም ያለብን የሚለው ነው።” ማለታቸው የተዘገበ ሲሆን አዛዦቹ በሀገሪቱ የውጭ ፖሊሲ እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በማህበራዊ ሚዲያ አስተያየት ከመስጠት እንዲቆጠቡ በመከልከል ከዚህ ውጭ ግን መድረኩን ስለ ስፖርት፣ ስለ ወጣቶች ጉዳዮች፣ ስለ ፖለቲካዊ ርዕዮተ አለም እና ትምህርትን በመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ይጠቀሙ ዘንድ መናገራቸው ተዘግቧል። ሙሴቪኒ ችግሩን የፈጠሩት የትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያ አስተያየቶች እንደሆኑ ለይተው ባይጠቅሱም ትዊተር ላይ ከ 568,000 በላይ ተከታዮች ያሉት ልጃቸው ሌተና ጄኔራል ሙሆዚ በአወዛጋቢ ልጥፎቹ እንደሚታወቅ ዴይሊ ሞኒተር ጠቁሟል።

ከኢትዮጵያ ጉዳይ ጋር በተያያዘም የሙሴቪኒ ልጅ የሆነው ወታደራዊ አዛዥ ባለፉት ወራት ከለጠፋቸው አነጋጋሪ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች መካከል “ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር ውጊያ የገጠሙትን የትግራይ አማፂያን እደግፋለሁ” ሲል የገለፀበትን ዴይሊ ሞኒተር አስታውሷል። ከዚህ በተጨማሪም የካምፓላ እና የኪጋሊ ግንኙነትን በማጣጣል ራስን የሚያሞግስ መልእክቱ እንዲሁም  እና በወርሃ የካቲት ሩሲዬ በዩክሬን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ስታውጅ “አብዛኛው (ነጭ ያልሆኑ) ሰው ልጆች” ሩሲያን ይደግፋሉ” ሲል በትዊተር ገፁ ያሰፈረው ልጥፍ በዘገባው ተወስቷል