የሩሲያ እና ቻይና ሌላ መሳሪያ – ማዳበሪያ


            የዓባይ፡ልጅ

ያራ ኢንተርናሽናል የሚሉት የመሬት ማዳበሪያ በማምረት የሚታወቅ ኩባንያ በ 60 የዓለም ሃገራት ይንቀሳቀሳል። ኩባንያው ከሩሲያ እጅግ ብዙ ጥሬ ዕቃ ይሸምታል። ወቅታዊው ጉዳይ ስለዚሁ ኩባንያ ትንሽ እንድናወሳ መነሻ ሊሆነን ይችላል። አንዱን ላስቀምጥ።

ያራ ኩባንያ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ግዢ ውስጥ ከሁለት ቢሊዬን ብር በላይ በያመቱ ሲጭበረበር የነበረው ዝርፊያ አካል እንደነበር በስፋት ሲዘገብ ነበር። ለማባደሪያ ግዢ በየዓመቱ ከሚመደበው በቢሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ ውስጥ ተለቅ ያለው ደርሻ ለሙስና ሲጋለጥ እንደነበር ከአራት አመት በፊት ይፋ የሆነ መረጃ ነበር። በወቅቱ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተባለ መንግስታዊ መስሪያ ቤት በወቅቱ እንዳለው ቀደም ባለው ጊዜ የማዳበሪያ ግዢ በግብርና ሚኒስቴር አማካይነት ይካሄድ ነበር፡፡ መስሪያ ቤቱ ከመንግስት ጋር ወዳጅነት ካላቸው ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር ይፈጽማቸው በነበረው ግዢዎች የተነሳ 2.6 ቢሊዬን ብር በየዓመቱ ሲመዘበር ቆይቷል፡፡ በተለይ ደግሞ ያራ የተባለው (መለስ ዜናዊን የሸለመው የኖርዌይ ማዳበሪያ አምራች ድርጅት) በማዳበሪያ ግዢ ውስጥ በሚፈጸመው ምዝበራ ትልቅ ሚና ነበረው፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተባለው መስሪያ ቤት ‹‹በማዳበሪያ ግዢ አሠራር ላይ ማስተካከያ በመደረጉ ዓለም አቀፍ የማዳበሪያ አምራቾች በቀጥታ በመሳተፋቸው ሁለት የንግድ ሰንሰለቶች ተሰብረዋል፡፡›› ሲል መናገሩ የሚታው ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም በወቅቱ ከመንግስት ጋር በመመሳጠር ሲመዘበር የነበረን 2.6 በሊዬን ብር ወይም 120 ሚሊዬን ዶላር ከምዝበራ መዳኑን ገልፆ ነበር።

በሰሞነኛው የዩክሬይን ቀውስ “ኪየቭ የሚገኘው የያራ ኢንተርናሽናል ቢሮ በሚሳዔል ተመቷል።” በማለት ቢቢሲ አውርቷል። ሀገረ ሩሲያም የማዳበሪያ ምርት እንዲቆም አዛለች። ቢቢሲ አማርኛ ስለዚህ ጉዳይ ሲዘግብ አለማቀፍ አንድምታውን ከማሳየት ይልቅ ያራ ወደተባለው ማዳበሪያ አምራች መወገኑን አንፀባርቋል። አውሮፓ ውስጥ ምግብ ለማምረት ጥቅም ላይ ከሚውሉ ግብዓቶች ከሩብ በላይ የሚመጣው ከሩሲያ ነው።” የሚለው ቢቢሲ የያራ ኢንተርናሽናል ሀላፊ ተናገሩት በማለትም “ዓለም በቀጣይ ከሩሲያ ጥገኝነት መላቀቅ አለባት።” ሲል ፅፏል። ሞስኮን ከአውሮፓ የመነጠል አጀንዳ አካል መሆኑ ነው።

ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ የግብርና ምርቶች አምራቾች ናት። ከግብርና ምርቶች ባለፈ ለማዳበሪያ እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን ፖታሽና ፎስፌት የተሰኙ ነጥረ ነገሮች በገፍ ታመርታለች።
“ከግማሽ በላይ የዓለም ሕዝብ ምግብ የሚያገኘው በማዳበሪያዎች ምክንያት ነው። ይህ ማዳበሪያ ከእርሻ ሥፍራ ከጠፋ ምርት 50 በመቶ ቀነሰ ማለት ነው” ይላሉ የያራ ኩባንያ ሀላፊ።
የማዳበሪያ ግብአት የሆነውን አሞኒያ ለማምረት በርካታ የተፈጥሮ ጋዝ የሚፈልግ ሲሆን፤ ያራ ኢንተርናሽናል አውሮፓ ውስጥ ይህንን ለማምረት በሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ ላይ ጥገኛ ነው።
ሀላፊው እንደገለፁት “በአንድ በኩል ለግብርና ምርት ስንል የማዳበሪያ ምርት እንሻለን። በሌላ በኩል ሩሲያ ዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ እናወግዛለን። ይህ እውነት ለመናገር ከሁለት አንድ እንደማጣት ነው።” ብለዋል።

ሩሲያ 20 በመቶውን የአለም ማዳበሪያ ትሸፍናለች። ቻይና ጉዳዩን እንደ ካርድ ትጠቀማለች እየተባለ ሲሆን፤ ቻይናና ሩሲያ በጥምረት አለምን 45 በመቶ ፎስፌት አቅራቢ ናቸው። ሰሞነኛው የሩሲያ የማዳበሪያ ሽያጭ አገዳ ከአውሮፓ እስከ ካናዳና አሜሪካ ሳይቀር አለምን እየተጫነ የሚገኝ ስጋት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ለማዳበሪያ ግዢ 27.2 ቢሊዬን ብር (ከ 660 ሚሊዮን $ በላይ) ያወጣችው ባለፈው አመት ነበር።
ኬኒያ በተመሳሳይ አመት ለማዳበሪያ ኬሚካልና ዘር ግዢ 65.7 ቢሊዮን የኬኒያ ሽልንግ (578 ሚሊዮን $) ወጪ አድርጋለች።

ስቶን ኤክስ የተባለው ኩባንያ ሀላፊ ስለጉዳዩ ተጠይቀው ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ሀላፊው ሊንቪል እንዳሉት፣ “አሁን ላይ ቻይና ማዳበሪያ ኤክስፖርት ማድረጓን እንዳታቆምብን ትልቅ ትኩረትም ሰጥተን እየሰራን ነው። ነገር ግን ቻይና የማዳበሪያ ኤክስፖርቱን አቁማ “ሩሲያ ላይ ያደረጋችሁት ሁሉ በኛ ላይ እንደተሰነዘረ ጥቃት ነው የምናየው ብትለንስ? ቤይጂንግ ወደ ታይዋንን ልገሰግስ ነው ብትለንስ? ከዚያም፣ ሩሲያ ላይ ያደረጋችሁትን ሁሉ በቻይና ላይም ልታደርጉት?” ብትለንስ? ያኔ ዛሬ ካለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ መኖሪያህ በየትኛውም የአለም ክፍል ቢሆን እጅግ ከባዱን አደጋ ታስተናግዳለህ።” ነው ያሉት።

Esleman Abay #የዓባይልጅ

[ለቀጣይ 25 ያህል ቀናት የምታገኙኝ ቴሌግራም ላይ ነው ⬇️

https://t.me/+UrMOjKqc3U42Wc7c

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories