የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት – 117ኛ ኮንግረስ፤ 2ኛ ምዕራፍ
S3199
(“ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እና ዲሞክራሲ ለማረጋገጥ እና ለሌሎችም አላማዎች”) በሚል ርዕስ ለኮሚቴው የተመራ እና ከቀረበ በኋላ ሕትመት እንዲደረግበት ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል።
በምትክነት የተደረገ ማሻሻያ በምክረ ሀሳብነት እንዲቀረብ
የሆነው በሚስተር ሜንዴዝ ነው፡፡
ክፍል 1፡- አጭር ርዕስ
ይህ ሕግ “የኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት ሕግ 2122” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ክፍል 2፡- ትርጓሜዎች
በዚህ ሕግ ውስጥ፡
(1) አግባብነት ያለው የኮንግረስ ኮሚቴ – “አግባብነት ያለው የኮንግረስ ከሚቴ” ማለት የሴኔቱ የውጭ ግንኙነቶች እና የተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ማለት ይሆናል፡፡
(2) የእርስ በእርስ ግጭት – “የእርስ በእርስ ግጭት” ማለት በኖቭ 2020 ኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ክልል የተጀመረው እና ከዚያ በኋላም ወደ ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የተዛመተው የእርስ በእርስ ግጭት ማለት ይሆናል፡፡
(3) በእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ወገኖች – “በእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ወገኖች” የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስትን፣ የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባርን (ትህንግ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመከላከያ ሃይል (ኢብመሃ)፣ የኢትዮጵያ ክልላዊ ሃይሎች፣ የትግራይ መከላከያ ሰራዊት ፣ የትግራይ መከላከያ ሰራዊት, ፣ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ፣ የክልል ኃይሎች ፣ ተደራጁ የብሄር ሚሊሻዎች እና ለዚህ ሕግ አላማ ሲባል ፕሬዝዳንት በግጭቱ ውስጥ አሉበት ብለው የወሰኗቸው
ሌሎች ተቋማትን ጨምሮ በቀጥታ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ተሳትፎ ያደረጉ።
(4) ሚኒስቴር/ሴክሬታሪ ኦፍ ስቴት – “ሚኒስቴር/ሴክሬታሪ ኦፍ ስቴት” ማለት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማለት
ይሆናል፡፡
(5) ከፍተኛ ባለስልጣን – “ከፍተኛ ባለስልጣን” ማለት፡
(ሀ) ርዕሰ ብሄር ወይም የፓርቲው ፕሬዝዳንት
(ለ) ርዕሰ መንግስት
(ሐ)የካቢኔው አባል ወይም በሚኒስትር ደረጃ ስልጣኑን የሚጠቀም የመንግስት ሃላፊ
(መ) ማንኛውም በመከላከያ፣ ደህንነት ወይም በመንግስት የውጭ ጉዳይ መዋቅሮች ውስጥ የሚገኝ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ባለስልጣን
(ሠ) ሌላ ማንኛውም ለዚህ ሕግ አላማ ሲባል ፕሬዝዳንቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ብለው የሚወስኑት ኦፊሰር
ክፍል 3፡ የኮንግረሱ አመለካከት በኮንግረሱ አመለካከት
(1) ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭት በቀጥታ የኢትዮጵያ አንድነት እና ዲሞክራሲ ስጋት የሚፈጥር ከመሆኑ በተጨማሪ የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ ስጋት ያስከትላል፡፡
(2) ሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል ለተራዘመ ጊዜ መተላለፊያው በመዘጋቱ ምክንያት በችግር ላይ የቆየ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ሰብዓዊ ድጋፎች፣ የሕክምና አቅርቦቶች እና ነዳጅ ለማለፍ እንዳይችሉ ያደረጋቸው በመሆኑ ይህ ነው የማይባል ሰብዓዊ ቀውስ
አስከትሏል፡፡
(3) ሁሉም በእርስ በእርስ ግጭቱ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ወገኖች በአፋጣኝ ጠላትነታቸውን አቁመው ሰብዓዊ እርዳታ ያለ ምንም እንቅፋት /ገደብ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ፣ ተኩስ አቁም ላይ ለመድረስ መደራደር እና ዘላቂነት ያለው የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ድርድር ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
(4) የኤርትራ መንግስትም በአፋጣኝ እና ሙሉ በሙሉ የጦር ሃይሉን ከኢትዮጵያ ማስወጣት አለበት፡፡
(5) የውጭ/የሃገር ውስጥ ያልሆኑ ሌሎች ተዋንያኖቸም ሁሉንም መሳሪያዎች እና ማቴሪያሎች በግጭቱ ላይ እየተሳተፉ ላሉ ወገኖች መሸጣቸውን እና ማቅረባቸውን ማቆም አለባቸው፡
(6) አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት እና አለምአቀፉ ማሕበረሰብ ለሁሉም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካባቢያዎች ሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብን በሚመለከት ቅድሚያ መስጠት ያለበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለረሃብ እና ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ማሕበረሰቦች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ማቅረብን አስቸኳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
(7) አሜሪካ እና መረጋጋትን በተመለከተ የሚደረጉ ድጋፍ፣ የስጋት ሁኔታን መቀነስ፣ እርቅ እና ዲሞክራሲን ማጠናከርን
ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት የእርስ በእርስ ግጭትን በተመለከተ ሰላማዊ በሆነ ድርድር በሚደረሱ መፍትሄ ድጋፍ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
(8) አሜሪካ እና በደህንነት እና ሌላ ተዛማጅ ድጋፎች ላይ ገደብ መጣል ይኖርበታል፡፡
(9) ሁሉም ተፈጸሙ የሚባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች
በገለልተኛ ወገን በጥልቅ መመርመር ያለባቸው ሲሆን ጥፋቱን የፈጸሙት ወገኖች ተጠያቂ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡(10) አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት እና አለምአቀፉ ማሕበረሰብ መንግስታትን፣ ድርጅቶችን እና ግለሰቦችን እንዲሁም የሚከተሉትን ተግባራት ሲፈጽም የቆየውን ዲያስፖራውን ጨምሮ ተጠያቂ ለማድረግ መስራት አለባቸው።
(ሀ)ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የእርስ በእርስ ግጭት እና ሌላ ተያያዥ ችግሮችን ያባባሰና
(ለ)እንደ የውጭ መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የብሄር ቡድን ወይም ድርጅት በመሆን የእርስ በእርስ ግጭቱን እንዲቀጥል ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ፀረ-አሜሪካ አመለካከት እንዲፈጠር ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት
ክፍል 4፡ የፖሊሲው መግለጫ
በሚከተሉት መንገዶች ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና አንድ የሆነች ኢትዮጵያን መደገፍ የዩናይትድ ስቴትስ ፖሊሲ ነው።
(1) ዘላቂነት ያለውን የሰላም ስምምነት ለመደገፍ ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ፣ የልማት እና ሕጋዊ መንገዶችን በመጠቀም
(2) በጋራ መተባበር እና የጋራ ስምምነት ላይ በሚደርሱ ወገኖች፣ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች አማካኝነት ሃገሪቷን አንድ ለማድረግ ተአማኒነት ያለው እና አካታች የፖለቲካ ሒደትን በመደገፍ
(ሀ) የግጭቱን ፖለቲካዊ ባህሪ በመገንዘብ/ ማወቅ
(ለ) ቅሬታዎችን መፍታትን ለመደገፍ ፖለቲካዊ መፍትሄዎች በማፈላለግ
(ሐ) ለሃገሪቱ ዲሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ የሆነ መንገድ መጥረግ
(3) ብሄር፣ ሃይማኖት፣ ፆታ ወይም የተገኙበት መልከአ ምድራዊ አካባቢ ከግምት ውስጥ ሳይገባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ፣ የሲቪል፣ የፖለቲካዊ መብቶችን የላቀ ደረጃ በማድረስ
(4) አስከፊው የውጭ ጣልቃ ገብነትን እና የእርስ በእርስ ግጭቱን እንዲሁም የውስጥ ነውጦችን የሚያባብስ ሀሰተኛ መረጃን በመከላከል
ክፍል 5፡ ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶች የሚደረግ ድጋፍ
(ሀ) የኮንግረሱ አመለካከት – በኮንግረሱ አመለካከት ዩናይትድ ስቴትስ የሚከተለውን ማድረግ ይኖርበታል፡
(1) በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ወይም አመለካከታቸው፣ በብሄራቸው ወይም በሪፖርት አቀራረባቸው ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ ደጋፊዎች፣ ጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች እንደሚፈቱ ለማረጋገጥ ማድረግ በምትችለው ሁሉ በሁሉም ደረጃ ላይ ያለ ዲፕሎማሲን መጠቀም
(2) በብሄር፣ በርዕዮተ አለም ወይም በፖለቲካዊ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ መድልዎ ሳይኖር የኢትዮጵያ መንግስት የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንደሚያከብር ማረጋገጥ
(3) ቅሬታን ለመፍታት የሚያስችል እና ለሃገሪቱ ዲሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ መንገድን የሚጠርግ እንዲሁም በፖለቲካዊ እስረኝነት በእስር ላይ የነበሩ ሰዎችን፣የሲቪል ማሕበራት ድርጅቶች እና የብሄር ማሕበረሰቦች ተወካዮችን ጨምሮ ሁሉንም
የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች የሚያካትት ተአማኒነት ያለው የአሰራር ሒደት/ሜካኒዝም መደገፍ
(ለ) ስትራቴጂ(1) በአጠቃላይ – ከዩናይትድ ስቴትስ ኤጀንሲ ፎር ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አስተዳዳሪ ጋር በመመካከር፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ/ሯ የሚከተሉትን መግለጫዎች እና አሳማኝ ምክንያቶች የሚያካትት ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲን እና የሕግ
የበላይነት እንደሚኖር፣ አለምአቀፍ ሰብዓዊ ሕግ እና አግባብነት ያላቸው የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች እንደሚከበሩ የሚያረጋግጥ ስትራቴጂ መንደፍ እና መተግበር ይኖርባቸዋል።
(ሀ) የዜጎች ተሳተፎን እና የፖለቲካ ምሕዳር ከማስፋት ጋር በተያያዘ የሚደረጉ የሲቪል ማሕበረሰብ ጥረቶችን
የመደገፍ እቅድ
(ለ) ሰፋ ባለ ሁኔታ የሲቪል ማሕበረሰብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የብሄር ማሕበረሰቦች እና የሃይማኖት ቡድኖች
ተወካዮችን የሚያካትት ተአማኒ እና ሁሉን አቀፍ የሆነ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ፖለቲካዊ ሒደት
የመደገፍ እቅድ
(ሐ) ፍትህን እና በእርስ በእርስ ግጭቱ ወቅት ለተፈጸሙ ጥፋቶች እና አስከፊ ድርጊቶች ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ
የአሰራር ሒደትን ጨምሮ የህግ የበላይነትን የመደገፍ እቅድ
(መ) ኢትዮጵያ ውስጥ የጥላቻ ንግግሮችን እና ሐሰተኛ መረጃዎችን የመዋጋት እቅድ
(ሠ) ወቅታዊ እና ለእቅድ የተያዘ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን (የኢብምቦ) የመሳሰሉ ገለልተኛ ተቋማትን
ጨምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ተቋማት የዲሞክራሲያዊ እና አመራር ድጋፍ
(ረ) በወቅታዊ እና በእቅድ የተያዙ የዲሞክራሲያዊ እና አመራር ድጋፍ እና አተገባበሮች ላይ የተገኙ ትምህርቶችን
የመገምገም እቅድ
(ሰ) ዲሞክራሲያዊ ሒደቱን የሚያደናቅፉ፣ ጅምላ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲፈጸም ያደረጉ ወይም በሕዝባዊ ሙስና ላይ እንደተሳተፉ በተረጋገጠባቸው ግለሰቦች ላይ ተጠያቂነት እንዲኖር የማድረግ የአሰራር ዘዴ
(2) ለኮንግረሱ ሪፖርት ማድረግ – ይህ ሕግ ከወጣ በኋላ ከ90 በማያንሱ ቀናት ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በአንቀጽ (1)
ላይ የተጠየቁትን ስትራቴጂዎች አግባብነት ላለው የኮንግረስ ኮሚቴ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
(ሐ) በየሩብ አመቱ የሚቀርቡ ሪፖርቶች
(1) በአጠቃላይ ይህ ሕግ ከፀደቀ በኋላ 30 በማይበልጡ ቀናት ውስጥ እና ከዚያ በኋላ ደግሞ በየ90 ቀናቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ/ሯ ከፌዴራል መምሪያ ሃላፊዎች እና የአትሮሲቲ ኧርሊ ዋርኒንግ ታስክ ፎርስ ተወካዮች ኤጀንሲዎች እንዲሁም ከሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ጋር በመመካከር ኢትዮጵያ ውስጥ በግጭቱ ላይ የተሳተፉ ወገኖች የሚከተሉትን መፈጸም አለመፈጸማቸውን ጨምሮ አግባብነት ያለው ሪፖርት ለኮንግረሱ ኮሚቴዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
(ሀ) የዘር ማጥፋት
(ለ) በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ወይም
(ሐ) የጦር ወንጀሎች
(2) ይዘት/ቅጽ – እያንዳንዱ በአንቀጹ የሚጠየቅ ሪፖርት
(1) የሚከተለውን ማሟላት አለበት(ሀ) በዚህ አንቀጽ ላይ የተገለጹትን ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በግልጽ ለይቶ መጥቀስ
(ለ) በተናጠል የሚቀርብ ምስጢራዊ እዝል/አባሪ ሊያካትት ቢችልም፤ ምስጢራዊ ባልሆነ መንገድ መቅረብ
አለበት፡፡
(3) ለህዝብ ተደራሽ መሆን – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ/ሯ በዚህ አንቀጽ የተጠቀሰው እያንዳንዱ ሪፖርት
(1) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ-ገጽ አማካኝነት በኢንተርኔት ለሕዝብ እንዲደርስ ማድረግ
ክፍል 6፡ የግጭት አፈታት፣ ቅነሳ እና ስራ አመራር እንዲሁም እርቅ የሚደረግ ድጋፍ
(ሀ) የግጭት አፈታት – ፕሬዝዳንቱ ለሚከተሉት የፋይናንስ፣ የቴክኒክ እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ
ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡
(1) ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭቱን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት በአፍሪካ ሕብረት ወይም በሌላ ተአማኒ ተቋማት ለሚደረግ ጥረት
(2) በሰላም ግንባታ፣ ግልግል/ማስታረቅ እና በማሕበረሰብ እርቅ ውስጥ ተሳትፎ ለማድረግ በሲቪል ማሕበረሰብ /በተለይም በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ የተገለሉ ማሕበረሰቦች/፣ ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ለሚያደርጓቸው ጥረቶች
(ለ) ግጭትን መቀነስ እና እርቅ
ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭቶችን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር፣ እርቅ ለማምጣት እና በግጭቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ከጉዳቱ እንዲያገግሙ ለመደገፍ ሲባል አግባብነት ካላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ቢሮዎች ጋር በመተባበር በዩናይትድ ስቴትስ
ኤጀንሲ ፎር ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አስተዳዳሪ የሚዘጋጀውን ስትራቴጂ እንደሚዘጋጅ እና እንደሚተገበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ/ሯ ማረጋገጥ የሚኖርበት/ባት ሲሆን፤ ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፡
(1) ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭቱን ስለሚመሩ ሁኔታዎች የሚኖር ትንታኔ
(2) ማሕበረሰብ መር እና ከታች ጀምሮ የሚኖር እርቅ ላይ አጽንኦት በመስጠት ግጭትን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ ሁሉን አቀፍ እቅድ
(3) ከታች ጀምሮ የሚኖር ሃገራዊ የግጭት አፈታት የአሰራር ሒደት/መካኒዝም እና በማሕበረሰብ ደረጃ ቅሬታን ለመፍታት የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የአሰራር ዘዴ/መካኒዝም የመደገፍ እቅድ
(4) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዩናይትድ ስቴትስ ኤጀንሲ ፎር ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት በባህላዊ መንገድ የተገለሉ ማሕበረሰቦች፣ የብሄር ቡድኖች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
(5) ሁሉም የኢትዮጵያን ሕዝብ መጥቀም ወይም የሲቪል ማሕበራት አቅምን መገንባት ላይ ያተኮሩ ድጋፎች በተቻለ መጠን በማሕበረሰብ ላይ የተመሰረተ ግጭት መቀነስ እና መቆጣጠር፣ ግጭትን መከላከል፣ የሰላም ግንባታ መፍትሄዎች፣ የእርቅ ተግባራት፣ ስነ-ልቦናዊ-ማሕበራዊ ድጋፍ እና ቁስል መፈወስን የማካተት እቅድ(6) ሁሉም የኢትዮጵያን ሕዝቦች ለመጥቀም ታልመው የሚሰሩ የድጋፍ መርሃ ግብሮች በፍላጎት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ
መተግበር ያለባቸው ሲሆን በብሄር፣ ክልል ወይም ፖለቲካዊ ተሳትፎ ምክንያት መድልዎ መኖር የለበትም፡፡
(7) ግልጽ መግለጫ፡-
(ሀ) የስትራቴጂው ግቦች እና የሚጠበቁ ውጤቶች
(ለ) መደበኛ ግምገማዎችን ጨምሮ የስትራቴጂው ግቦች እመርታ የሚለካበት መንገድ
(8) በዚህ ንዑስ ክፍል መሠረት አስፈላጊውን የስትራቴጂ ግብዓቶች ለማካተት ወቅታዊውን የሃገሪቱን የልማት ትብብር ስትራቴጂ ግብዓቶች ወቅታዊ የማድረግ እና የማሻሻል እቅድ
(ሐ) አቅርቦት፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ/ሯ ይህ ሕግ ከወጣ በኋላ ከ90 ባልበለጡ ቀናት በዚህ ንዑስ ክፍል (ለ) የተጠየቁትን ስትራቴጂዎች አግባብነት ላላቸው የኮንግረስ ኮሚቴዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ክፍል 7፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ እና መረጋጋትን የመደገፍ እርምጃዎች
(ሀ) ወደ ዲሞክራሲ የሚደረገውን ሽግግር የሚያደናቅፉ ድርጊቶች ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች
(1) በአጠቃላይ – ይህ ሕግ ከወጣ በኋላ ከ180 ቀናት ጀምሮ ፕሬዝዳንቱ የሚከተለውን ፈጽመዋል ብለው በሚያምኑባቸው በማንኛውም የውጭ ሃገር ዜጎች ላይ ፕሬዝዳንቱ በአንቀጽ (2) ላይ የተጠቀሱትን ማዕቀቦች ይጥላሉ፡
(ሀ) ሆን ብሎ በተጨባጭ ሁኔታ ዋጋ የማሳጣት ጉልህ ድርጊቶች ላይ የተሳተፈ ወይም የእርስ በእርስ ግጭቱን
ለመፍታት ይፋዊ እውቅና እና ስልጣን የተሰጠውን ጥረት ቦታን ወይም ዋጋ ለማሳጣት ብሎ በመፈለግ
ተሳትፎ ያደረገ
(ለ) የእርስ በእርስ ግጭቱ እንዲባባስ በቀጥታ እና በማቴሪያል ረገድ አስተዋጽኦ ያበረከተ
(ሐ) ሆን ብሎ በሃገሪቱ ውስጥ በሚገኙ በማንኛውም አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፎች እንዳይቀርቡ እንቅፋት የፈጠረ
(መ) ከኢትዮጵያ መንግስት ወይም ከትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ከፍተኛ አመራሮች ወይም ከሌላ ግጭቱ ውስጥ
ተሳታፊ ከሆኑ አካላት ጋር የስራ ወይም የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር እያወቀ ከግጭቱ ወይም የሚከተሉትን
ለማድረግ ምሪት በመስጠት ወይም ሆን ብሎ የመሳተፍ ድርጊቶችን ጨምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን
ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ለማደናቀፍ ከሚደረጉ ጥረቶች የፋይናንስ ወይም ፖለቲካዊ ጥቅም ያገኙ፡-
(I) የምርጫ ማጭበርበር
(II) ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች
(III) የመንግስታዊ ሙስና ድርጊቶች
(ሠ) ሆን ብሎ ለማንኛውም በግጭቱ ውስጥ ተሳትፎ ላላቸው ወገኖች አቅርቦት ማድረግ እና ይህ ድርጊት ለእርስ
በእርስ ግጭቱ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የሚያውቅ ወይም ማወቅ የነበረበት
(I) የመሳሪያ ሲስተሞች፣ ለምሳሌ፡ ጠመንጃ፣ ያለ ሰው የሚሰሩ የአየር ላይ መሳሪያዎች ድሮኖች
(አንማንድ ኤሪያል ሲስተም)፣ ኢሊኮፍተሮች፣ እነዚህ በአየር ላይ የሚሰሩ መሳሪያዎች
ወይም ኢሊኮፍተሮች፣ ተተኳሾች፣ የሚጠቀሟቸው ትጥቆች የውጊያ ታንኮች፣ ብረት ለበስየውጊያ ተሽከርካሪዎች፣ እነዚህ ታንኮች እና ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሟቸው ትጥቆች፣ ሚሳኤሎች ወይም የሚሳኤል ሲስተሞች ወይም የታጠቁ ተሽከርካሪዎች ወይም
(II) ለእነዚህ ሲስተሞች የሚደረግ ድጋፍ ለምሳሌ፡ ተተኳሾች፣ መለዋወጫ እቃዎች፣ ፓይለቶች
ወይም ሌላ ኦፕሬተሮች
(ረ) ለማንኛውም በግጭቱ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ለሚገኙ ወገኖች የመሳሪያ ሲስተሞችን ሽያጭ፣ ኦፕሬሽን ወይም
ዝውውር ወይም ለእነዚህ መሠል ሲስተሞች የሚደረግ ድጋፍን ሆን ብሎ ያሳለጠ ወይም የፋይናንስ ድጋፍ
ያደረገ እና ይህ ጉዳይ በእርስ በእርስ ግጭቱ ጥቅም ላይ እንደሚውል የሚያውቅ ወይም ማወቅ የነበረበት
(2) የተዘረዘሩ ማእቀቦች- አንድን የውጭ ሃገር ሰው በተመለከተ ፕሬዝዳንቱ በአንቀጽ(1) መሠረት የሚጥሏቸው ማዕቀቦች የሚከተሉት ናቸው።
(ሀ) ንብረት ማገድ – ይህን መሰል ንብረቶች ወይም ጥቅሞች በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ ወይም
በዩናይትድ ስቴትስ በኩል የሚመጡ ወይም በዩናይትድ ስቴትስ ሰው ይዞታ እና ቁጥጥር ስር የሚገኙ ከሆነ
ሁሉንም የውጭ ሃገርን ሰው ንብረት እና ጥቅሞች ረገድ የሚኖሩ ሁሉንም ግብይቶች እስከማገድ እና እስከ
መከልከል ድረስ በኢንተርናሽናል ኢመርጀንሲ ኢኮኖሚክ ፓወርስ አክት (50 ዩ.ኤስ.ሲ 1701ኢቲ ሲኩ.)
መሠረት ለፕሬዝዳንቱ የተሰጣቸውን ሁሉንም ስልጣኖች መጠቀም
(ለ) ቪዛ፣ መግቢያ ወይም የግዜያዊ ፈቃድ የማይፈቀድላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች
(I) ቪዛዎች፣ መግቢያ ወይም የግዜያዊ ፈቃድ
በአንቀጽ (1) ላይ የተጠቀሰ የውጭ ሃገር ዜጋ፡
(I) ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመግባት አይችልም
(II) ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመግባት ቪዛ ወይም ሌላ ሰነዶች ለማግኘት ሕጋዊነት የለውም
(III) ወይም ደግሞ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመግባት ወይም ፈቃድ ወይም በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ሕግ (8
ዩ.ኤስ.ሲ. 1101 ኢቲ ሲኩ) መሠረት ማንኛውንም አይነት ጥቅማጥቅም ለማግኘት ተገቢነት/ሕጋዊነት
የለውም
(II) የሚሰረዙ ወይም የሚሻሩ ወቅታዊ ቪዛዎች፡
(I) በአጠቃላይ፡- ቪዛው ወይም ሌላ የመግቢያ ሰነዶች የተሰጡበት ጊዜ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ዩናይትድ ስቴትስ
በአንቀጽ (1) ላይ የተጠቀሰውን የውጭ ሃገር ዜጋ ቪዛ እና ሌላ የመግቢያ ሰነዶች ሰርዛለች፡፡
(II) በአፋጣኝ የሚወሰድ እርምጃ በንዑስ አንቀጽ (I) የሚደረገው ስረዛ፡
(ሀሀ) በአፋጣኝ ተግባራዊ ይደረጋል
(ለለ) ይህ የውጭ ሃገር ሰው በይዞታ የያዛቸው ሌላ የሰነድ ቪዛ ወይም የመግቢያ ሰነድ በአፋጣኝ ይሰረዛል
(3) የተለዩ ሁኔታዎች(ሀ) የደህንነት ተግባራት የተለየ ሁኔታ፡- በዚህ ክፍል መሠረት የሚጣሉ ማዕቀቦች በ1974ቱ ብሄራዊ የፀጥታ
ሕግ ርዕስ V(50 ዩ.ኤስ.ሲ. 3091 ኢቲ ሲኩ) መሠረት ሪፖርት ለማድረግ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ወይም
የተፈቀዱ የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ተግባራት/እንቅስቃሴዎች ላይ ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፡፡
(ለ) አለምአቀፍ ግዴታዎችን ለመወጣት እና ለሕግ ማስከበር ተግባራት የሚኖር የተለየ ሁኔታ፡- የውጭ ሃገር
ዜጋውን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲገባ ወይም ፈቃድ እንዲያገኝ ማድረግ የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ካሉት
በአንቀጽ (2)(ለ) መሠረት የሚጣሉ ማዕቀቦች ተፈጻሚ አይደረጉም፡-
(I) በተባበሩት መንግስታት እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ሰኔ 19 ቀን 1939 ዓ.ም በሌክ ሰክሰስ
በተፈረመው እና በሕዳር 11 ቀን 1940 ዓ.ም ወደ ስራ በገባው የተባበሩት መንግስታት ዋና
መ/ቤት ስምምነት መሠረት ወይም በሌላ ተፈፃሚነት ያላቸው አለምአቀፋዊ ግዴታዎች መሠረት
ዩናይትድ ስቴትስ ስምምነቱን እንድታከብር የሚረዳት ሲሆን
(II) በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሕግ ማስከበር ስራዎችን ለማከናወን ወይም ለመደገፍ
(ሐ) እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ከማስገባት ጋር የተያያዘ የተለየ ሁኔታ
(i) በአጠቃላይ በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር የተካተቱ ስልጣኖች እና ማዕቀብ የመጣል መስፈርቶች ወደ
ሃገር ውስጥ የሚገቡ እቃዎች ላይ ማዕቀብ የመጣል ስልጣንን ወይም መስፈርትን አያካትትም፡፡
(ii) የእቃ ትርጓሜ፡- በዚህ አንቀጽ ውስጥ “እቃ” ማለት የመሳሪያ ፍተሻን እና ምርመራን ጨምሮ ነገር
ግን ቴክኒካዊ ዳታን ሳይጨምር ማንኛውም ቁስ፣ ተፈጥሮአዊ ወይም ሰው ሰራሽ እቃ፣ ማቴሪያል፣
አቅርቦት ወይም የተመረተ ምርት ማለት ይሆናል፡፡
(4) አተገባበር፣ መቀጫዎች፡-
(ሀ) አተገባበር፡- ይህንን ንዑስ ክፍል ተፈጻሚ ለማድረግ ፕሬዝዳንቱ በኢንተርናሽናል ኢመርጀንሲ ኢኮኖሚክ
ፓወርስ ሕግ ክፍል 203 እና 205 (50 ዩ.ኤስ.ሲ 1702 እና 1704) መሠረት የተሰጣቸውን ሁሉንም
ስልጣኖች ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
(ለ) ከንብረት ማገድ ጋር የተያያዙ መቀጫዎች፡- በንዑስ አንቀጽ(ሀ) አንቀጽ (2) ላይ ወይም በማንኛውም ንዑስ
አንቀጹን ተግባራዊ ለማድረግ የወጣ ደንብ፣ ፈቃድ ወይም ትዕዛዝ ላይ ጥሰት የፈጸመ፣ ጥሰት የመፈጸም
ሙከራ ያደረገ፣ ጥሰት ለመፈጸም ያሴረ ሰው በዚያ ክፍል በንዑስ ክፍል (ሀ) ላይ የተዘረዘሩትን ድርጊቶች
ከፈፀመ ሰው እኩል በኢንተርናሽናል ኢመርጀንሲ ኢኮኖሚክ ፓወር ሕግ (50 ዩ.ኤስ.ሲ 1705) መሠረት
መቀጫ ይጣልበታል፡፡
(5) ትርጓሜዎች፡- በዚህ ንዑስ ክፍል ውስጥ፡-
(ሀ) መግባት፣ እንዲገባ የተፈቀደለት፣የውጭ ዜጋ፡- “መግባት”፣ “እንዲገባ የተፈቀደለት” እና “የውጭ ሃገር ዜጋ”
የሚሉት ቃላት በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ህግ ክፍል 101(8 ዩ.ኤስ.ሲ.1101) ላይ ለእነዚህ ቃላት የተሰጠው
ትርጉም ይኖራቸዋል፡፡
(ለ) አግባብነት ያላቸው የኮንግረሱ ኮሚቴዎች፡ “አግባብነት ያላቸው የኮንግረሱ ኮሚቴዎች” ማለት የሴኔቱ
የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ፣ የሴኔቱ የባንኪንግ፣ የቤቶች እና ከተማ ጉዳዮች ኮሚቴ፣ የተወካዮች ምክር ቤት
የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ እና የተወካዮች ምክር ቤት የፋይናንስ አገልግሎቶች ኮሚቴ ማለት ይሆናሉ፡፡
(ሐ) የውጭ ሃገር ሰው፡ “የውጭ ሃገር ሰው” ማለት የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ያልሆነ ሰው ማለት ነው፡፡
(መ) አውቆ፡ ሁኔታን፣ ተግባርን፣ ውጤትን በተመለከተ ”አውቆ” የሚለው ቃል ትርጓሜ ሰውየው ተግባሩን፣
ሁኔታውን ወይም ውጤቱን ያውቃል ወይም ማወቅ ነበረበት ማለት ይሆናል፡፡
(ሠ) የዩናይትድ ስቴትስ ሰው፡ “የየዩናይትድ ስቴትስ ሰው” ማለት፡
(i) የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በቋሚነት ለመኖር በሕጋዊ መንገድ የገባ ወይም
የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ውስጥ በሕግ የተፈቀደለት ማንኛውም ግለሰብ ወይም
(ii) በውጭ ሃገር የሚገኝ የዚህን መሠል ተቋም ቅርንጫፉን ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ ሕጎች ወይም
በማንኛውም ሕጎች መሠረት የተቋቋመ ተቋም ማለት ይሆናል፡፡
(6) ፕሬዝዳንታዊ ስልጣንን ያለመጠቀም፡- ሒደት በሒደት ላይ በመመስረት እና ከ180 ለማይበልጡ ቀናት በዚህ ክፍል
መሠረት በሚደረግ ማራዘሚያ እና መስፈርት መሠረት ፕሬዝዳንቱ አግባብነት ላላቸው የኮንግረሱ ኮሚቴዎች ሲያቀርብ
ብቻ በሰውየው ላይ ማዕቀብ የመጣል ወይም የማስቀጠል ስልጣኑን ላይጠቀም ይችላል፡
(ሀ) ስልጣኑን ያለመጠቀም ወይም ስልጣኑን ያለመጠቀም የዩናይትድ ስቴትስን ብሄራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ
ስለመሆኑ የጽኁፍ ማረጋገጫ
(ለ) ማዕቀብ በሚያስከትሉ ተግባራት ላይ ተሰማርቶ የነበረው ሰው ይህንን ተግባር ማቆሙ እና ሰውየው ይህንን
መሠል ተግባር ላይ ለወደፊቱ ቢሳተፍ የስጋት ሁኔታ እንደማይኖር ማረጋገጫ ሲኖር
(ለ) ወደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚላኩ የመከላከያ እና ጣምራ ጠቀሜታ ያላቸው እቃዎች ገደብ
(1) ጣምራ ጠቀሜታ ያላቸው እቃዎች በዚያ ክፍል አንቀጽ (ii) ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ለመላክ፣ ድጋሚ ከሃገር
ለማስወጣት ወይም በሃገራቱ ውስጥ ለማስተላለፍ በወጪ እቃዎች ቁጥጥር ሪፎርም ሕግ 2018(50
ዩ.ኤስ.ሲ.4813(ሐ)(1)(ሀ)) ሕግ ክፍል 1754(ሐ) (1)(ሀ) መሠረት ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡
(2) የመከላከያ ዕቃዎች፡ በዩናይትድ ስቴትስ የመሳሪያዎች ዝርዝር የመሳሪያ ወደ ውጭ የመላክ ቁጥጥር ሕግ (22 ዩ.ኤስ.ሲ.
778(ሀ)(1))/ታህሳስ 22 ቀን 2008 ዓ.ም/ ላይ የሰፈሩ እቃዎችን ወደ ኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ ለመላክ ፈቃድ
ያስፈልጋል፡፡
(ሐ) በኢትዮጵያ የሚደረጉ በተለይ የሚጠቀሱ ድጋፎችን መከልከል እና ማገድ
(1) በዩናይትድ ስቴትስ ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የሚደረግ ድጋፍ፡-
በዩናይትድ ስቴትስ ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ፕሮጀክቶች በ2018ቱ ቤተር ዩቲላይዜሽን ኦፍ ኢንቨስትመንትስ ሊዲንግ ቱ ዴቨሎፕመንት ሕግ (22 ዩ.ኤስ.ሲ. 9621ኢቲ ሲኩ) ርዕስ II መሠረት የሚኖሩ
ድጋፎችን አያደርግም፡፡
(2) ማቋረጥ፡ በአንቀጽ (1) ላይ የሰፈረው ክልከላ በክፍል 13 ላይ የተዘረዘረው መስፈርት በሚሟላበት ጊዜ ወይም ከተሟላ በኋላ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡
(3) ፕሬዝዳንታዊ ስልጣንን ያለመጠቀም፡- ሒደት በሒደት ላይ በመመስረት ፕሬዝዳንቱ ስልጣኑን ያለመጠቀሙ
ለዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ጸጥታ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን የጽኁፍ ማረጋገጫ አግባብነት ላላቸው የኮንግረሱ
ኮሚቴዎች ሲያቀርቡ በአንቀጽ (1) ላይ የሰፈረው ክልከላን በተመለከተ ስልጣናቸውን ላይጠቀሙ ይችላሉ፡፡
(መ) የተለያዩ ማዕቀቦች፡ እንደ አግባብነቱ ከትሬዠሪ ሚኒስትር እና ከንግድ ሚኒስትር ጋር በመመካከር የውጭ
ጉዳይ ሚኒስትሩ/ሯ በንኡስ ክፍል (ሀ)(1) ላይ በተጠቀሱ ሰዎች ላይ የተለያዩ የተቀናጁ ማዕቀቦችን ለመጣል
እና የወጪ እቃዎች ቁጥጥር ለማድረግ ከተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት፣ ከኖርዝ
አትላንቲክ ትሪቲ ኦርጋናይዜሽን፣ ከአውሮፓ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ሕብረት እና ከሌላ አግባብነት ካላቸው
ተዋናዮች ጋር በመተባበር መስራት ይኖርባቸዋል፡፡
ክፍል 8፡ የጸጥታ ድጋፍ
(ሀ) ድጋፍን ማገድ፡- ዩናይትድ ስቴትስ ሁሉንም ለኢትዮጵያ መንግስት እየተደረጉ ያሉትን የፀጥታ ድጋፎችን
በአስቸኳይ ማገድ ይኖርባታል፡፡
(ለ) ፕሬዝዳንታዊ ስልጣንን ያለመጠቀም፡- የሚከተለውን በተመለከተ ፕሬዝዳንቱ አግባብነት ላላቸው
የኮንግረሱ ኮሚቴዎች የጽኁፍ ማረጋገጫ ሲያቀርቡ ፕሬዝዳንቱ በንዑስ ክፍል (ሀ) ላይ የተጠቀሰውን እገዳ
በተመለከተ ስልጣናቸውን ላይጠቀሙ ይችላሉ፡-
(1) ስልጣንን ያለመጠቀም ወይም ስልጣንን ያለመጠቀምን ማራዘም ለዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ጸጥታ
ጠቀሜታ ያለው ሲሆን እና
(2) የኢትዮጵያ መንግስት እና ወኪሎቹ በግጭቱ ውስጥ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ዋና ዋና ወገኖች ጋር
እውነተኛ የሆነ በድርድር የሚደረስ መፍትሄ ላይ ለመድረስ እርምጃዎችን ሲወስዱ
(ሐ) ማቋረጥ፡- በንዑስ ክፍሉ ላይ የተጠቀሰው እገዳ
(ሀ) በክፍል 13 ላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶች ሲሟሉ ወይም ከተሟሉ በኋላ ተፈፃሚ አይደረግም፡፡
(መ) ሪፖርት፡- ይህ ሕግ ከወጣ በኋላ ከ30 ቀናት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ/ሯ ሕጉ
ከወጣበት ቀን ጀምሮ በንዑስ ክፍል (ሀ) መሠረት እንዲቆሙ የተደረጉ ሁሉንም አካታች ዝርዝሮች አግባብነት
ላላቸው የኮንግረሱ ኮሚቴዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ክፍል 9፡ በአለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማት በኩል ለኢትዮጵያ መንግስት የሚደረግ ድጋፍ
(ሀ) እገዳ፡ የትሬዠሪ ሚኒስትሩ/ሯ የአለምአቀፍ ተቋማት የዩናይትድ ስቴትስ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች
የሚከተሉትን እንዲያከናውኑ መመሪያ መስጠት ይኖርባቸዋል፡
(1) ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ መንግስታት የሚደረጉ ማንኛውንም የብድር ወይም የፋይናንስ ወይም የቴክኒካዊ
ድጋፍ ማራዘሚያን ለመቃወም በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ ያላትን ድምጽ እና ተሰሚነት
እንዲጠቀሙ
(2) ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት የሚሰጡ ብድሮች ሰላምን ለማስፋፋት እና አለምአቀፍ ሰብዓዊ ሕጎች
እና አግባብነት ያላቸው አለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶች እንደሚከበሩ በማረጋገጥ ላይ ያለሙ
እንዲሆኑ ለማስቻል ከሌላ ቁልፍ ለጋሽ ሃገራት ጋር የተቀናጀ ፖሊሲ ለመቅረጽ በጋራ መስራት
(ለ) ለሰብዓዊ አላማ የሚኖር የተለየ ሁኔታ፡ በአንቀጽ (1) እና (2) ንዑስ አንቀጽ (ሀ) ላይ የተጠቀሱት ገደቦች
ለሰብዓዊ አላማ የሚደረጉ ብድሮች ወይም የፋይናንስ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ ላይ ተፈጻሚነት
አይኖርቸውም፡፡
(ሐ) በቀጥታ መሰረታዊ ፍላጎቶችን የሚደግፉ ፕሮጀክቶች ላይ ገደብን ያለመጠቀም፡ የትሬዠሪ ሚኒስትሩ ድምዳሜ
ላይ በሚደርሱበት ጊዜ ሚኒስትሩ የጽኁፍ ማረጋገጫ አግባብነት ላላቸው የኮንግረሱ ኮሚቴዎች ሲያቀርቡ
ብቻ፤ ገደቡን ያለመጠቀም በቀጥታ ለሰብዓዊ ፍላጎቶች ጠቀሜታ ያላቸውን ፕሮጀክቶች የሚደግፍ ከሆነ
በንዑስ ክፍል (ሀ)(1) ላይ የተጠቀሱት ገደቦች ተፈጻሚ አይደረጉም፡፡
(መ) ፕሬዝዳንታዊ ስልጣንን ያለመጠቀም፡ ሒደት በሒደት ላይ በመመስረት ስልጣንን ያለመጠቀሙ ለዩናይትድ
ስቴትስ ብሄራዊ ጸጥታ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን የጽኁፍ ማረጋገጫ አግባብነት ላላቸው የኮንግረሱ
ኮሚቴዎች ሲያቀርቡ ፕሬዝዳንቱ በንዑስ ክፍል (ሀ)(1) ላይ የተጠቀሱትን ገደቦች በተመለከተ ስልጣናቸውን
ላይጠቀሙ ይችላሉ፡፡
(ሠ) ማቋረጥ፡ በክፍል 13 ላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶች ከተሟሉ በኋላ ንዑስ ክፍል (ሀ)(1) ተፈጻሚነት
አይኖረውም፡፡
(ረ) ማብራሪያ፡ ይህ ሕግ ከወጣ በኋላ ከ60 በማይበልጡ ቀናት ውስጥ እና በክፍል (መ) መሠረት በንኡስ ክፍል
(ሀ)(1) ላይ የተጠቀሱት እገዳዎች እስከሚ