የአረብ ሊግ አዝናኝ ሁነቶችና ትችቶች – በ – አረቦቹ አንደበት
የመጀሪያውን ሳስቀድምላችሁ። ባለፈው ዓመት ስድስት የአረብ ሀገሮች አረብ ሊጉን በሊቀመንበርነት ለመምራት አሻፈረኝ ማለታቸው የሊጉን ንቅዘት አደባባይ ያወጣ ነበር።
ያኔ፣ ፍልስጤም የመሪነት መብቷን አልቀበልም በማለት ጀመረችው። ሊቢያ ተከተለቻት(ያውም ሊቢያ በወቅቱ አባልነቷ ታግዶ የነበረበት ወቅት ላይ የደረሳትን ዙር)። ከዛም ኳታር እምቢዬው አለች። ኮሞሮስ ቀጠለች፣ ኩዌትና ሊባኖስም እንዲሁ…። ይታያችሁ እንግዲህ!
በዚህ ሊግ “ጀለብያ” ውስጥ ተሸጉጣ መሆኑ ነው፣ ግብፅ አድኑኝ የምትላቸው።
መሪነቱን አልቀበልም የሚለውን ታይቶ የማይታወቅ ክስተት ተከትሎ የአረቡ አክቲቪስት እንደ ጉድ ይፅፍ ገባ። ግብፃዊው ጋዜጠኛ ምን ቢል ጥሩ ነው? ከ 10 ሚሊዮን በላይ ተከታይ አለው። Moataz Matar ይባላል። “የእድሩ ድክመት ነውንጂ አረብ ሊግኮ ሞቷል” አለ።
“We already said, it [the Arab League] is clinically dead, so hurry in burying it… or even bring Israel to preside it,”
ይህ ትንግርት የተከሰተው ኤምሬትስና ባህሬን ከእስራኤል የፈረሙትን ቅርርብ በማውገዝ የሊጉን ውድቀት በመቃወም ነበር ፍልስጤም ፕሬዝዳንትነቷን ለመልቀቅ መጀመሪያ ላይ እንድትወስን ያደረጋት።
ሌላው አረባዊ ተሟጋች ቀጠለ። “ሊቢያ ሊጉን ‘ምሪ’ ከምትሉኝ ይቅርታ ይደረግልኝ አለች” አለና፤ ምክንያቷን አስመልክቶ ደግሞ “ሌላው የሊጉ አባል አልቀብርም ያለው ሬሳ እኔ ላይ የሚወድቀው ‘ምን በወጣኝ!’ ብላ” ሲል የፃፈውን እልፎች ነበሩ የተቀባበሉት።
እኔም አሰብኩትና “ለካ አፍሪካ ህብረት ዝምታን የመረጠው በአስከሬን ላይ ከትችት ይልቅ ፀሎት ይሻላል” በማለት ሳይሆን አይቀርም።
RIP Arab League