ትንሿ ስፓርታ The Little Sparta – ኤምሬትስ |??

ትንሿ ስፓርታ የኤምሬትስ ተቀፅላ ስያሜ ነው። ስፓርታ እጅግ ዝነኛዋ የጥንታዊ ግሪክ ግዛት መኖሪያ ስትሆን በአራት መንደሮች ጥምረት የተመሰረተች ነበረች። በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ ስትራቴጂክነት እና በተፅዕኖ ፈጣሪነቷም ትታወሳለች።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከስፓርታ ጋር ትመሰላለች። በተለይም በስፋቷ ትንሽ ነገር ግን በተፅዕኖዋ በዙሪያዋ ያሉ ሰፋፊ አገራትን በማስከንዳቷ። “Little Sparta” ትንሿ ስፓርታ ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደጠሯት የሚነገረው የዶናልድ ትራምፕ የመከላከያ ምኒስትር ጄነራል ጄምስ ማቲስ ነበር።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሰነዶች እንዳሰፈሩት ከቅርብ አመታት በፊት በሞት የተለዩት ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን የአገሪቱ መስራች አባት ናቸው። የተባበረችና የበረታች ያደረጋት የኢሚሮች ጥምረት እውን የሆነው በእሳቸው መሪነትና ራዕይ መሰረት በመሆኑ።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አሁን የያዘችውን ግዛት ይዛ ከተመሰረት 50ኛ አመቷ ነው። በሼክ ረሺድ ጠቅላይ ምኒስትርነት የመጀመሪያ ካቢኔዋ የተቋቋመው ልክ በዛሬዋ እለት ታህሳስ 14 1964 አመተ ምህረት ነበር።

ዱባይ የዛሬ ሃምሳ ሶስት አመት (1968) የነበሯት መኪኖች ቁጥር 13 ብቻ ነበር። በ2020 በመላው ኤምሬትስ 3 ሚሊዮን መኪኖች ተመዝግበዋል። አሁን ላይ ግን ከመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያው የሆነውን የጠፈር መንኮራኩር ማምጠቅ ችላለች።
ከአለም ግዙፎች ተርታ በግምባር ቀደምነት የሚመደበው ኤምሬትስ አየር መንገድ ባለቤት ስትሆን፤ ኢቲሃድ፣ ዱባይ ኤሮስፔስ፣ ፍላይ ዱባይ እና ራክ አየር መንገዶችም የሷው ናቸው።

ሰባት ኢሚሬቶችን ያቀፈው ፌዴሬሽኑ አቡ ዳቢ፣ ዱባይ፣ ሻርጃህ፣ ራስ አል-ካይማህ፣ አጅማን፣ ኡመ-አል ቁዋይን እና ፉጃራህ የሚባሉት ናቸው። ሰባተኛዋ ራስ አል-ካይማህ በቀጣዩ አመት የካቲት ወር ላይ ነበር የተቀላቅለችው።
ዲሴምበር 2 ስድስቱ ኢሚሬቶቹ የተዋሃዱበት የኢምሬትስ ብሔራዊ ቀን ነው። ዘንድሮ 50 አመት ሞላው(በ1971)።
ዋና ከተማዋ አቡ ዳቢ ስትሆን በአረብኛው “አቡ” ማለት “አባት” ሲሆን “ዳቢ” ደግሞ “ድኩላ”።
ኤምሬትስ ከሁለት ሀገራት ድንበር ትጋራለች፤ ከሳውዲ አረቢያና ኦማን።
በቆዳ ስፋት መጠን ትልቁ አቡ ዳቢ ሲሆን 67,340 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ሲሆን ትንሹ አጅማን 259 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ነው።

የአገሬው ሰዎች ባድዊኖች ከዛሬ 50 አመት በፊት የባድዊን ህዝቦች የአለማችን ሞቃትና ደረቅ በረሃ ተቋሙመው ግመሎቻቸውን ጭነው አረቢያን በማቆራረጥ ህይወትን መምራት ግድ ይላቸው ነበር። ያኔ የራሳቸው መገበያያ ስለሌላቸው የህንድን ሩፒ ነበር የሚጠቀሙት።
ኤምሬትስ ዛሬ ላይ ለሚሊዮኖች የአለም ዜጎች የእንጄራ ሰበብ ሆናለች።ዛሬውኑ ከአለም ፍጥነት ጋር ከመራመድ ተሻግራ በአለም ፍጥነት ላይም የራሷን አሻራና ተፅዕኖ በትልቁ ወደ ለመፃፍ በቅታለች።
ዛሬ ላይ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ ከአለም 9ኛ ነው። ስራ ለመጀመር ያለው ምቹ ሁኔታ ከአለም 14 ላይ ናት።

ትንሿ ነገር ግን ሀብታሟ ሀገር መሆኗ ይነገራል።
የዓለማችን ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት፣ የንግድ መናኸሪያነትና ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት መገለጫዋ ናቸው። ከወጭ ንግድ ገቢዋ የድፍድፍ ነዳጅ export 45 በመቶውን ይሸፍናል።

ዋነኛ የንግድ አጋሮቿ ውስጥ ህንድ 10%፣ ኢራን 9.9%፣ ጃፓን 9.3%፣ ቻይና 5.4%፣ ኦማን 5%፣ ስዊዘርላንድ 4.4%፣ ደቡብ ኮሪያ 4.1%።
የኤሚሬትስ የነዳጅ ክምችት መጠን አሁን ላይ ከዓለም ስድስተኛ ነው። ኢኮኖሚዋ በቀዳሚነት ኢንዱስትሪ መር ሲሆን 49.8 በመቶ ድርሻ አለው፤ አገልግሎት ዘርፉ 49.2 በመቶ እንዲሁም ግብር 0.9 በመቶ ነው።

በሁሉም ግዛቶቿ የተምር ዛፎች በብዛት የሚገኙባት ስትሆን በአጠቃላይ 40 ሚሊዮን የተምር ዛፎች መኖራቸው ይገለፃል።

በ1998፣ ሻርጃህ የአረቡ አለም የባህል መዲና ተብላ በዩኔስኮ ልትመዘገብ ችላለች። ሻርጃህ ከሌሎች ስድስት የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጋር ድንበር የምትጋራ ብቸኛዋ ኢሚሬት ናት።

ኤምሬትስ የመጪው ዘመን ሚኒስቴር የተባለ መስሪያ ቤት አላት። ሰው ልጅ ድንበር የማይገደበው እውነታ እየጠበቀው ነውና ዜጎች ተፅዕኖውን የሚቋቋሙት፣ ጫናውን እንደ መልካም እድል ተጠቅመው የስራ እድል ማግኘት የሚችሉ ብቁዎች ሆነው እንዲቀበሉት ማስቻል አላማው ነው። መጪው የዲጂታል፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን፣ የሮቦቲክስ…ዘመን ጋር ማጣጣም..።

የመቻቻል ምኒስትር ደግሞ ከአምስት አመት በፊት ያቋቋመች ስትሆን ዜጎቿ ብሎም በግዛቷ የሚኖሩ የተለያዩ አገራት ዜጎች መካከል ያለውን የዘር፣ የሀይማኖትና ባህል ልዩነቶች አቻችሎና አስተባብሮ ለማስቀጠል ያለመ መስሪያ ቤቷ ነው።

በአገሪቱ መስራች የተሰየመው ታላቁ ሼክ ዛይድ መስጂድ በአንድ ጊዜ 41,000 ምዕመናንን ማስተናገድ ይችላል።
ኤምሬትስ 40 ቤተክርስትያናትና ካቴድራሎች ይገኙባታል።

2019 ላይ ፖፕ ፍራንሲስ አቡ ዳቢን የጎበኙ ሲሆን ይህም የአረቢያን ባሕረ ሰላጤ ምድር በመጎብኘትና ቅዳሴ በመፈጸም በታሪክ የመጀመሪያው ሆነዋል።
ኤምሬትስ የ 200 አገራት ዜጎች መኖሪያ ናት። የህዝብ ቁጥሯ 9.7 ሚሊዮን ሲሆን የአገሬው ቁጥር ከአጠቃላዩ 11% ነው። ቀሪው 89 በመቶ የውጪ አገራት ዜጋ ነው።
ህንዳዊ 27%፣ ፓኪስታናዊ 12%፣ ፊሊፒኒ 6፣ ግብፅ 5፣ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የሌሎች ሀገሮች 38 በመቶ ናቸው።

ኤምሬትስ የመቻቻል ምድር የምትባለውም ለዚህ ነው

Dubai, United Arab Emirates
Emirates247
MOI UAE
HABESHA – UAE (online)
The National
Khaleej Times
Gulf News

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories