Deprecated: Creation of dynamic property OMAPI_Elementor_Widget::$base is deprecated in /home/eslemanabaycom/public_html/wp-content/plugins/optinmonster/OMAPI/Elementor/Widget.php on line 41

ትህነግ የከፈተችው የተልዕኮ ጦርነት

ትህነግ የከፈተችው ጦርነት “የተልዕኮ ጦርነት” ስለመሆኑ የተነገረን ገና ከጅምሩ በራሳቸው የትህነግ አመራሮች ነበር..ምንም እንኳን ጦርነቱ “ለትግራይ ሕዝብ” እንደሆነ በተደጋጋሚ ቢነገረንም! እስቲ ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳይ ከዘጠኝ ወራት በፊት ማለትም በ2021/12/26 “The Elephant” ዕትም ላይ “Pertinent Issues on the War in Tigray” በሚለው ርዕስ ሥር ያሰፈረውን አብረን እንመልከት፦

“በአብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስትና የአማራ ተባባሪዎቹ ላልተገደበ የኢሳያስ አፈወርቂ ፍላጎት የትሮይ ፈረስ እየሆኑ ነው፤ እሱንም(ኢሳይያስን ማለቱ ነው) ቢሆን የመካከለኛ ምሥራቅ ሀገራት እንደ ኤጀንት እየተጠቀሙበት ነው። አንድ ነገር ግልፅ ማድረግ እፈልጋለሁ፤ የትግራይ ትግል በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት፣ በአማራ ኃይሎችና ከበስተጀርባ ባሉ በመካከለኛ ምሥራቅ ሀገራት (ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ኢራን) ጥምር ኃይሎች የሚከሽፍ ከሆነ ኢሳይያስ ንድፉን ዕውን የሚያደርግበት በሩ ይከፈትለታል። የአፍሪካ ቀንድ በኤርትራው አምባገናን መዳፍ ሥር ይወድቃል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ አፍሪካና ቀጠናው ይህ አስጊው ሲናሪዮ ዕውን እንዲሆን ይፈቅዱ ይሆን? ምላሹ ‘አይፈቅዱም’ የሚል ከሆነ እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን ነው።”

በእንግሊዝኛ የተቀመጠው ይህን ይመስላል፦

“The Ethiopian state under Abiy Ahmed and his Amhara interlocutors is being used as a Trojan Horse for the unbridled and oversized ambition of Isaias Afewerki, who he himself is serving as an agent of the Middle Eastern countries. I would like to make one thing clear, if the resistance in Tigray is crushed by the combined forces of the Ethiopian federal government, Amhara forces, and their backers in the Middle East (Turkey, UAE, and Iran) the floodgates for Isaias to implement his blueprint will be open. The region of the Horn of Africa will be run as per the dictat of the Eritrean dictator. Is the international community, Africa and the region willing to live with the impending scenario? If the answer to the question posed is no, the time to act is now.”

በዚህ የፃድቃን ማብራሪያ ውስጥ አንድ ያሳቀኝ(ያሳቀቀኝ?) ተቃርኖ አለ። ፃድቃን አብይን በኢሳይያስ የትሮይ ፈረስነት ይከስሰዋል፤ ኢሳይያስን ደግሞ በቱርክ ፣ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስና በኢራን የትሮይ ፈረስነት ይከስሰዋል። የሚያስቀው ፃድቃን ሁለቱንም መሪዎች በትሮይ ፈረስነት ከስሶአቸው እንዳጠናቀቀ ራሱ በተራው የአሜሪካና የአውሮፓ ትሮይ ፈረስ ለመሆን ተማፅዕኖውን ማቅረቡ ነው። የሚሰጠው አገልግሎት ተመሳሳይ ከሆነ አብይንም ሆነ ኢሳያስን ለመተቸት ሞራሉን ያገኘው ከወዴት ነው?

ያም ሆነ ይህ የትግራይን ጦርነት ነገረ-መንስኤን (Cause of the war) በተመለከተ ጦርነቱን አሃዱ ብለው ካስጀመሩ ጄኔራሎች የበለጠ እናውቃለን ማለት ዘበት ነው፤ ጄኔራል ፃድቃን በግልፅ በፅሁፉ…እየተዋጋን ያለነው በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካንና የአውሮፓን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው…ካለን እኛ ሌላ ምክንያት መስጠት አንችልም። በአጭሩ ጦርነቱ የውክልና ጦርነት (Proxy War) ነው። እናም በሌሎች መድረኮች በየሐቲቱ መኸል … እየተዋጋን ያለነው ለትግራ ሕዝብ ነው…የሚሉት ውሸታቸውን ነው። በግልባጩ ትህነግ በ27 የአገዛዝ ዘመኗ በአፍሪካ ቀንድ የምዕራባውያኑን ተልዕኮ እያስፈፀመች ስለመክረሟ ይህ የፃዲቃን ፅሁፍ በቂ ማስራጃ ነው። የዛሬው ጦርነት የማዕከላዊ መንግስት ሥልጣንን በመቆጣጠር ወደ ቀደመው ሁኔታ ለመመለስ የሚደረግ ከንቱ መፍጨርጨር ነው። ምናልባትም ከወቅቱ አውድ ጋር ፈፅሞ የማይጣጣም ጦርነት በማካሄድ ትህነግ በዓለማችን ብቸኛዋ ሳትሆን ትቀራለች?

✍️Getahun hetamo

Share:

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

VK Russian online social media and social networking service
Categories