ዜለንስኪ: የስንዴ ፕሮፓጋንዳውና እውነታዎችየዓባይ:ልጅ

የዓባይ:ልጅ – Esleman Abay

በአፍሪካን ድህነት ላይ ተማክሎ የአውሮፓው የጥቁር ባሕር Black Sea Grain Initiative መስተጓጎል ብዙ ‘ትራምፔት’ እየተነፋበት ይገኛል። ወደ እውነታው እንግባ ካልን ግን ዩክሬይን ለደሃ ሀገራት እህል በመላክ ከፍተኛ 5 ሀገራት ደረጃ ውስጥ እንኳን የማትገባ መሆኗን እንማራለን..። በአንፃሩ ኬይቭ የሀብታም ሀገራት እህል አቅራቢ መሆኗን እንገነዘባለን። እንደ ኔዘርላንድ፣ ጣሊያን፣ ስፔን፣ ቻይና፣ እና ቱርክ ላሉ ሀገራት ትልቋ እህል ላኪ ሀገር ነች – ዜለንስኪ የሚመራት ሀገረ – ዩክሬይን።

ለኬይቭ አገዛዝ ፕሮፓጋንዳ ማለት ዋነኛው ምርኩዙ ነውና ፕሬዝደንት ዜለንስኪ ለጠ/ሚ አብይ ደውሎ “ልረዳችሁ አልችልም፤ ረሃባችሁን እንዳስታግስላችሁ ከፈለጋችሁ የሆነ ድምፅ ነገር አሰሙልኝ፤” ሲል የሰማነው። እውነታውን ታዲያ ቀጥሎ እንመልከተው፦

እንደ ተ.መ.ድ – UN ሪፖርት ዩክሬይን በእህል ስምምነቱ መሰረት ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ ከላከቻቸው የምግብ ምርቶች ውስጥ፡-
▪️47% የሚሆነው ወደ ስፔን፣ ጣሊያን እና ኔዘርላንድስ እንዲሁም ለመሰል ሀብታም ሀገራት ነው ያደረሰችው።
▪️26% የሚሆነው እንደ ቱርክ እና ቻይና ላሉ “ከፍተኛ/መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገሮች” የላከች ሲሆን
▪️ለታዳጊ ሀገራት ተብሎ የተጓጓዘው ደግሞ ሩብ ያህሉ ብቻ ነበር። ይኸውም 27%ው ብቻ የተጓጓዘ ሲሆን በዋነኝነትም እንደ ግብፅ፣ ኬንያ እና ሱዳን ላሉ ሀገራት ተልኳል ይለናል ሪፖርቱ።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በአፍጋኒስታን፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና የመን ለሚገኙ ተረጂዎች በሚል በ2022፣ ከ 725,000 ቶን በላይ ስንዴ ከዩክሬን በ2022 መቀበሉን ሪፖርቱ ያመላክታል። መዳረሻው የተረጋገጠ ባይሆንም የአለም ምግብ ፕሮግራም በተጠቀሰው አመት ውስጥ ዩክሬይን ግማሹን የስንዴ እህል እንድታቀርብ ነው ያደረገው። ይህ ውሳኔ ይተላለፍ ዘንድ ታዲያ አቅርቦቱ (በአብዛኛው በሩሲያ, በህንድ, እና በብራዚል ወዘተ ሊሟላ ቢችልም፣ የወቅቱ የአቅርቦት ችግር ዋጋውን ሰቅሎት ነበርና ከአገልጋይ – ዘለንስኪ ሸመታው እንዲሆን ሊወስኑ ችለዋል።

የአፍሪካ ዋነኛ እህል ላኪዎች እነማን ነበሩ?

በፈረንግ 2020 የ 4.3 ቢሊዮን ዶላር ስንዴ ለአፍሪካ ያቀረበችው ሀገር ሩሲያ???????? ናት። ወደ አፍሪካ ከገባው የስንዴ ምርት 32.6 በመቶውን የሸፈነችው ሞስኮ ነች።
▪️በ 2020 ደግሞ የ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ስንዴ ለአፍሪካ ያቀረበችው ፈረንሳይ???????? ወደ አህጉሪቱ ከገቡ የስንዴ ምርቶች 21.3 በመቶውን የሸፈነች ናት።
▪️በፈረንጆቹ 2020 የ 1.9 ቢሊዮን ዶላር በቆሎ ለአፍሪካ ያቀረበችው አርጀንቲና???????? ለአህጉሪቱ ከቀረበላት የበቆሎ ምርት 19.5%ውን ሸፍናለች።
▪️2020 ላይ የ 1.6 ቢሊዮን ዶላር በቆሎ ለአፍሪካ ያቀረበችው ብራዚል???????? አፍሪካ ካስገባችው የበቆሎ ምርት 16.4%ውን ሸፍናለች።
▪️እ.ኤ.አ. 2020 ላይ የ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ሩዝ ለአፍሪካ ያቀረበችው ህንድ???????? ስትሆን ከአህጉሪቷ የሩዝ አቅርቦት 17.7 በመቶውን ሸፍናለች…።

አስካሁን የታወቀው እውነታ ይህን እየመሰከረ ባለበት ተጨባጭ ውስጥ ዩክሬይን የምትነፋብን ትራምፔት በምንኛ እንደተቃኘ መረዳት በጣም የሚከብድ ነው። ቮሎድሚር ዜለንስኪ ከሐሽሽ ጋር ያላቸው ቁርኝት እኛን ላይመለከት ይችል ይሆናል፤ ሰውዬው ኮሜዲያን፣ ፋሺስት አሊያም ኢ*ፆታዊ በሽታው የግል ኃጢያቱ ሊባል ይችላል። ግን ይች ሰውዬ ያለመግቢያ ገብታ ማጣፊያው ሲያጥርባት ዛሬ ላይ በደሃ አፍሪካዊያን ስም የነዛችው የስንዴ ፕሮፓጋንዳ አዲሱ የኮሜዲ episode የሚባል አይነት ነው።

የኛ ኢትዮጵያ ደግሞ የነፃነትና የፍትሃዊ ትግል አርማ እንጂ የፋሽስቶችን ወንጀል የመደባበቅ ታሪክም ሆነ ባህል የላትም። አፍሪካዊያን የሚሰጧት ልዩ ቦታ ደግሞ መሰል ፋሺስቶችን ለመፀየፍ ሌላኛው እሴቷ መሆኑ ለማንም ያልተደበቀ ሐቅ ነው።

▪️እስሌማን ዓባይ Esleman Abay #የዓባይልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories